Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

አንድ ሚሊዮን የቴሌቪዥን ባለንብረቶች በኤሌክትሮኒክ ዘዴ የባለቤትነት ክፍያ መፈጸም ሊጀምሩ ነው

$
0
0

tv_guideየኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ኤጀንሲ ከዚህ ቀደም ሲሰበስብ የነበረውን የቴሌቪዥን ባለቤትነት ምዘገባና ፈቃድ ክፍያዎችን እንዲሰብስብ፣ ከክፍያ ለሁሉ ኩባንያ ጋር ስምምነት አደረገ፡፡

በዚህ ዓመት ብቻ ከአንድ ሚሊዮን ባለንብረቶች 60 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ እንደሚሰበስብ ይጠበቃል፡፡

መጋቢት 2 ቀን 2007 ዓ.ም. በተደረገው ስምምነት መሠረት ሁለቱን ተቋማት ጨምሮ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሦስትዮሽ ስምምነት ፈጽመዋል፡፡ ከመጋቢት 8 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው የቴሌቪዥን ባለቤትነት ፈቃድና ምዝገባና ዕድሳት ክፍያዎችን በክፍያ ለሁሉ የፋይናንስ ቴክኖሎጂ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በኩል ሲሰበሰብ፣ ዓመታዊ የክፍያ መጠኑ በእያንዳንዱ ቴሌቪዥን 60 ብር ሲሆን ክፍያ ለሁሉ ኩባንያ ከእያንዳንዱ ቴሌቪዥን ክፍያ ላይ ለአገልግሎቱ አሥር ብር እንደሚከፈለው፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስጂያጅ አቶ ብርሃነ ኪዳነማርያም ገልጸዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ የግብይትና የማስታወቂያ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰናይት ኃይሌ እንዳስታወቁት፣ በማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲና በኮርፖሬሽኑ መረጃ መሠረት በአዲስ አበባ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ቴሌቪዥን እንዳላቸው ይገመታል፡፡ በመሆኑም ከእነዚህ ባለንብረቶች በዚህ ዓመት በሚደረግ የዲጂታል ምዝገባ የታሰበው ገቢ ሊገኝ እንደሚችል ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ባለፈው ዓመት ከቴሌቪዥን ባለቤትነት ፈቃድና ምዝገባ 13 ሚሊዮን ብር የሚገመት ገንዘብ መሰብሰቡም ታውቋል፡፡ በዚህ ዓመት 60 ሚሊዮን ብር እንደሚሰበስብ ይጠበቃል፡፡

የቴሌቪዥን ባለንብረትነት ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥ ሒደቱን ወደ ዲጂታል ሥርዓት ለማምጣት የአንድ ዓመት ጊዜ መፍጀቱን የገለጹት ዳይሬክተሯ፣ የቴሌቪዥን ባለንብረትነት ክፍያዎችን በማይከፍሉት ላይ ከገንዘብ ቅጣት ባሻገር እስከመውረስ የሚደርሱ ዕርምጃዎች እንደሚወሰዱ አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከ40 ዓመታት በፊት በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ከባለንብረቶች ዓመታዊ ክፍያ እየሰበሰበ ሲሆን፣ ወደፊት የግል የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በሚመጡበት ወቅት ይህ ሁኔታ ሊለወጥ እንደሚችል አቶ ብርሃነ ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡ በአንዳንድ አገሮች እንዲህ ያለው የባለንብረትንት ክፍያ የሚጠየቀው የመንግሥት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ሌሎች የገቢ ምንጮች የሌሏቸው መሆኑን ታሳቢ በማድረግ እንደሆነ፣ እንደ ቢቢሲ ያሉ የእንግሊዝ የመንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ዋቢ ይደረጋሉ፡፡ በአንፃሩ በኢትዮጵያ ብቸኛው የአገሪቱ ቴሌቪዥን ጣቢያ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ ከማስታወቂያ ከፍተኛውን ገቢ የሚያስገባ ከመሆኑ ባሻገር፣ የባለቤትነት ዓመታዊ ክፍያዎችን በመሰብሰብም አርባ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡

ክፍያ ለሁሉ ኩባንያ በአዲስ አበባ በከፈታቸው 34 የክፍያ ጣቢያዎች የውኃ፣ የኤሌክትሪክ ኃይልና የቴሌኮም አገልግሎት ክፍያዎችን ለመንግሥት በመሰብሰብ ሥራውን የጀመረ ሲሆን፣ በወር 600 ሺሕ ደንበኞችን በማስተናገድ 1.2 ሚሊዮን የአገልግሎት ክፍያዎችን እያስተናበረ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት በአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም አማካይነት ለ20 ሺሕ የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች ቴክኖሎጂ አገዝ ቅርንጫፍ አልባ የባንክ አገልግሎት በሙከራ ደረጃ እየሰጠ ይገኛል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

The post አንድ ሚሊዮን የቴሌቪዥን ባለንብረቶች በኤሌክትሮኒክ ዘዴ የባለቤትነት ክፍያ መፈጸም ሊጀምሩ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>