Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Hiber Radio: እስራኤል ከአገሯ በሚባረሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ምትክ ለኢህአዴግ መንግስት የጦር መሳሪያ ለመስጠት እየተደራደረች መሆኑ ታወቀ

$
0
0

የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ሐምሌ 7 ቀን 2005 ፕሮግራም

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

<< …በጎንደር በሰልፉ ላይ እንዳይገኝ ቤት ለቤት ከማስፈራራት፣በዘመቻ ፖስተር ከመቅደድ, እኛን ከማገት እና እንገላለን ብለው ከማስፈራራት አልፈው ጠዋት ሕዝቡ ወደ ተቃውሞ ሰልፉ እንዳይመጣ ወደ ከተማዋ የሚያስገቡና ሰልፉ በሚሄድባቸው አካባቢዎች መጋቢ መንገዶችን በተሽከርካሪ በመዝጋት ለማደናቀፍ ሞክረዋል። ሕዝቡ ይሄን ሁሉ አልፎ ጎንደር ላይ ብሶቱን ለማሰማት ሲወጣ ከ15 በላይ ካሜራ ይዘው ለማስፈራራት ሲቀርጹ ነበር…የመተማ መሬት የጎንደር ነው፣ አሰብ ወደባችን ነው፣ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለመሆን የኢህአዲግ አባል መሆን ግዴታ መሆን የለበትም …> የሚሉ መፈክሮችን ሕዝቡ ራሱ ሲያሰማ ነበር …>>

አቶ ሀብታሙ አያሌው የአንድነት፣ለፍትህና ለዴሞክራሲ የብሔራዊ ም/ቤት አባልና የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት ዘመቻ አስተባባሪዎች አንዱ ከጎንደር ለህብር ከሰጡት ቃለ ምልልስ (ሙሉውን ያዳምጡ)


ሀይሌና ፖለቲካ አብረው መነሳት ከጀመሩ ቆይተዋል። ሀይሌ በሩጫው ጀግና ቢሆንም ምርጫ 97 ተከትሎ ያ ሁሉ ግፍ ሲፈጸም ነገር አበርዳለሁ ብሎ የወያኔ መሳሪያ የሆነው ዕውነት መናገር የፈራው የሽማግሌ ቡድን አባል ነው። ቢያንስ የእሱና የሌሎች ሽማግሌዎች ዝምታ የፕ/ር ይስሃቅ ውሸትና ዝምታ ለብርቱካን ዳግም እስር ለእነ አቶ መለስ ጉልበት ሰጥቷል የሚል አግባብ ያለው ቅሬታ ይቀርባል።በዚህ ሁሉ ግን ሀይሌ ገ/ስላሴ ፕሬዝዳንት ለመሆን በፖለቲካው ዓለም ለመሮጥ ዘንድሬ የቆረጠ ይመስላል ። የሀይሌን ውሳኔና ተከትሎት የመጣውን የሰዎች አስተያየት ቃኝተኛል

<<…በቬጋስ ፍትሕ ካለ በይግባኙ እናሸንፋለን ብዬ አምናለሁ…>> በስራ ማቆም አድማ ላይ ከሶስት ወር ተኩል በላይ ያለ አንዳች ክፍያ ከቆዩና ለስራ አጥ ኢንሹራንስ ይግባኝ ካሉ አሽከርካሪዎች አንዱ ለህብር ከሰጠው ቃለ ምልልስ የተወሰደ

(ዝርዝሩን ከወቅታዊው ዘገባ ያዳምጡ)

ሌሎችም ቃለ መጠይቆች አሉን

ዜናዎቻችን
- በፍሎሪዳ የ17 ዓመቱን ታዳጊ ተኩሶ የገደለው ራሱን ለመከላከል ተብሎ ነጻ መሆኑ በአሜሪካ ሕዝባዊ ተቃውሞ አስነሳ

- ሟች ጥቁር ስለሆነ የተፈጸመበት በደል ነው የሚል ቁጣ ቀስቅሷል

- እስራኤል ከአገሯ በሚባረሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ምትክ ለኢህአዴግ መንግስት የጦር መሳሪያ ለመስጠት እየተደራደረች መሆኑ ታወቀ

- አንድነት ፓርቲ በጎንደርና በደሴ ደማቅ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄደ

- የጸጥታ ሀይሎች በጎንደር ከ15 በላይ በደሴ ከ6 በላይ ካሜራ ይዘው ፍርሃት ለመፍጠር ሲቀርጹ ነበር

- የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲሱ ቦይንግ አውሮፕላን ለንደን ላይ የመጨስ አደጋ ቢገጥመውም መብረሬን አላቆምም አለ

- በጎንደር ከ40 ሺህ በደሴ ከ50 ሺህ በላይ ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ ተቃወመ

- በአዲስ አበባ ሌቦችን “ለመርዳት ሞክርዋል” የተባሉ አቃቤ ህግ እና የፖሊስ አባል ተያዙ

- በአገር ቤት የሙስሊሙ ህ/ሰብ በአገር አቀፍ ተቃውሞ <<ድራማው በቃን!>> አለ

- የአርቡን ተቃውሞ ተከትሎ ከ24 በላይ ወጣቶች በአዲስ አበባ ታስረዋል

– ይግባኛቸው የተደመጠው በስራ ማቆም አድማ ላይ ያሉት የቬጋስ አሽከርካሪዎች በሕግ እኛሸንፋለን የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገለጹ

ሌሎችም ዜናዎች አሉን


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles