Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ለ3 ቀናት ከቤኒን ወደ ናይጄሪያ በአውቶቡስ የተጓዙት ደደቢቶች ከብዙ እንግልት በኋላ ነገ ዎልቭዝን ይገጥማሉ

$
0
0

449221-thumb-250x200ኢትዮኪክ ኦፍ እንደዘገበው የኢትዮጵያው ደደቢት ከረጅም የጉዞ ድካም እና እንግልት በኃላ ትላንት ናይጄሪያ ደርሷል። የቡድኑ አባላት ወደ ናይጄሪያ ለመጓዝ በረራቸው ሌጎስ የነበረ ቢሆንም በረራው ቤኒን ከደረሰ በኃላ የቡድኑ አባላት ከቤኒን ብዙ ኪሎ ሜትሮችን በአውቶቡስ የሶስት ቀን መንገድ ተጉዘው ጨዋታው የሚደርጉበት ከተማ በሰላም ትላንት ከሰአት ደርሰዋል።

ደደቢቶች እንደዚህ አይነት የእንግልት ጉዞ ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም፤ እንደሚታወሰው በመጀመሪያው የማጣሪያ ዙር ጨዋታቸው ወደ ሲሸልስ ሲጓዙ በኬንያ አድርገው ጨዋታ የሚደረግባት ሲሸልስ ሲደርሱ በድካም ተንገላተው እንደነበር ይታወሳል ። ጨዋታውን ሲሸልስ ላይ ካደረጉም በኃላም ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ በበረራ ችግር በሚል አንድ ሳምንት ጉዞው ፈጅቶባቸዋል።

ይሁንና ደደቢቶች በመጀመሪያው ዙር ያጋጠማቸውን የጉዞ መንገላታት ተቌቁመው ተጋጣሚያቸውን ከማጣሪያው ውጪ አድርገዋል።

በሀሉተኛው ዙር የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን የማጣሪያ ጨዋታ ነገ የናይጄሪያው ዋሪ ዎልቭስ በዋሪ ሲቲ ስታዴየም ደደቢትን ያስተናግዳል።

ዋሪ ዎልቭስ ለኢትዮጵያው ደደቢት ትልቅ ግምት ሰጥተዋል ፤ ጨዋታውን ደጋፊዎቹ በስታዲየም ተገኝተው ተጨዋቾቹን እንዲያበረታቱ ጥሪ አቅርበዋል።

በተለይም የክለቡ ቃል አቀባይ ለSL10.ng ድህረ ገፅ እንደተናገሩት የኢትዮጵያው ደደቢት ጨዋታውን አገሩ ላይ ሲያደርግ ከ35 ሺ ያላነስ ተመልካቾች ይኖሩታል ፤ እኛ ደግሞ ከ20ሺ ያላነሰ ደጋፊ ጨዋታውን ተገኝቶ ተጨዋቾቹን ቢያበረታታ የተሻለ ውጤት እንዲኖረን ያችላል ብለዋል።

የጨዋታው ኮሚሺነር ጋናዊው ሲሆኑ ጨዋታውን የሚመሩት ሁሉም ሶማሊያውያን አልቢተሮች መሆናው ነው የድህረ ገፁ መረጃ የሚያመለክተው።

 

The post ለ3 ቀናት ከቤኒን ወደ ናይጄሪያ በአውቶቡስ የተጓዙት ደደቢቶች ከብዙ እንግልት በኋላ ነገ ዎልቭዝን ይገጥማሉ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>