Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ውድ ኮሚቴዎቻችን ለውሳኔ ለዛሬ ወር መጋቢት 30 ተቀጠሩ!

$
0
0

ሰኞ የካቲት 30/2007

11042677_921194401265250_2791512484073047742_nውድ ኮሚቴዎቻችን የመጨረሻ የመከላከያ ምስክራቸውን ያሰሙ ሲሆን በፍርድ ቤቱ ቀነ ቀጠሮ መሰረት ኡስታዝ በድሩ ሁሴንን ጨምሮ ውድ ኮሚቴዎቻችን በዛሬው ችሎት በልደታው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ታውቋል፡፡ በማዕከላዊ ምርመራ ወቅት በኡስታዝ በድሩ ሁሴን ላይ በኤግዚቢትነት የተያዘው ላፕቶፕ ማስረጃዎች ለፍርድ ቤቱ ቀርበዋል፡፡ ሙያዊ ምስክርነቱን ለመስጠት በችሎቱ የተገኘው የኮምፒውተር ባለሞያ በላፕቶፑ ላይ 5 ሺ ያክል ፎቶዎችን ያየ መሆኑን፣ ነገር ግን አቃቤ ህግ ያቀረበውን ክስ የሚደግፍ ምንም አይነት መረጃ አለመኖሩንም ተናግሯል። ባለሙያው አክሎም የኡስታዝ በድሩ ሁሴን ላፕቶፕ የይለፍ ቃል (ፓስወርድ) የሌለው መሆኑን የገለፀ ሲሆን በዚህም ማንም አካል የሚፈልገውን ሊያደርግ የሚችልበት ክፍተት መኖሩን ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል። በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ ለመጋቢት 22 ቀጠሮ ከሰጠ በኋላ የኮሚቴዎቻችን ጠበቆች ‹‹ቀን ይጨመርልን›› ሲሉ በጠየቁት መሰረት ለውሳኔ ለዛሬ ወር ለመጋቢት 30 ቀጥሯል።

ፍርድ ቤቱ ከዚህ በፊት ‹‹በሂጃብ ዙሪያና የታራሚዎችን አያያዝ ሁኔታ ያስረዱ› ሲል በቀጠረው መሰረት የማረሚያ ሀላፊው መልሳቸውን በቃል ይዘው የመጡ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ‹‹መልሱ በጽሁፍ ይሁን›› በማለት ለመጋቢት 10 ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ እንዲሁም ከመጋቢት 30 በፊት አቃቤ ህጉ እና ጠበቆቹ ‹‹የማጠቃለያ ንግግር›› (በከሳሽ እና በተከሳሽ መካከል ከውሳኔ በፊት የሚደረግ ንግግር) በቢሮ በኩልም ሆነ በችሎት እንዲያቀርቡ ፍርድ ቤቱ ያዘዘ ሲሆን ኡስታዝ በድሩ ሁሴን ችሎት ላይ በህክምና ዙሪያ ባሰማው አቤቱታ መሰረት ‹‹ማረሚያ ቤቱ በቂ ህክምና እንዲደረግለት ያስደርግ›› የሚል ትእዛዝ በማተላለፍ ችሎቱን አጠናቋል፡፡

በዛሬው ችሎት ላይ በርካታ ህዝበ ሙስሊም የተገኘ ሲሆን የፍርድ ቤቱ ጥበቃዎች ‹‹መታወቂያቹን ካላሳያችሁ ከግቢ አትወጡም›› በሚል ትንኮሳ ሲፈጽሙ የነበረ መሆኑ ታውቋል፡፡

ሕዝበ ሙስሊሙ በጀግኖች መሪዎቹ ላይ የሚሰጥን የሐሰት ፖለቲካዊ ብይን በጭራሽ አይቀበልም! በጽኑም ይታገለዋል!!!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

 

The post ውድ ኮሚቴዎቻችን ለውሳኔ ለዛሬ ወር መጋቢት 30 ተቀጠሩ! appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>