በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ካምፓስ ዉስጥ የሕወሃት ታጣቂዎች በተማሪዎች ላይ ተኩስ እንደከፈቱ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል። በዩኒቨርሲቲ ዛሬ ትምህርት ያልነበረ ሲሆን፣ በርካታ ፌዴራል ፖሊሶች ካምፓሱን ተቆጣጥረዉታል። ጩኸትና ረብሻም ተሰምቷል።
የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በገጠማቸው የውሀ እጥረት ምክንያት ሲሆን ረብሽ ያነሱት፣ በካምፓስ ዉስጥም ከፍተኛ ግርግር ጩኸትና ተኩስ እንደነበር ታውቋል። በግርግሩም ተማሪዎች እንደተጉዱ በርካታ የፌድራል ፖሊሶች የዩኒቨርሲቲውን ግቢ እንደ ወረሩት ተማሪዎቹንም እየደበደቡና እያፈሱ ወደተለያየ እስር ቤቶች እንደወሰዷቸው ታውቋል ፡፡
ተማሪዎቹ እንደሚሉት ለበርካታ ቀናት ውሀ አጥተው መቸገራቸውን ይህንንም ጉዳይ ለትምህርት ቤቱ ሀላፊዎች ማመልከታቸውን ነገር ግን ችግሩን ሊፈቱላቸው እንዳልቻሉ ተናገረዋል፡፤ ተያይዞም በአከባቢው የሚገኙ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ተማሪዎቹን በመደገፍ አመፁን መቀላቀላቸው ተነገሯል፡፡ አሁን ግርግሩ ቀዝቀዝ ያለ ሲሆን በርካታ የፌድራል ፖሊስ አባላት ከግቢው ውጭ ቆመው ይገኛሉ፡፡
The post በአዋሳ በተማሪዎች ላይ የሕወሃት ሰራዊት ተኩስ እንደከፈተ ተዘገበ appeared first on Zehabesha Amharic.