Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በአማራ ክልል ነዋሪዎች በአገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች መማረራቸውን ተናገሩ

$
0
0

Amharamapየካቲት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በክልሉ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ እና የተለያዩ ቢሮዎች በየእለቱ ጉዳያቸውን ለማስፈጸም የሚመላለሱ ባለጉዳዮች በተለያየ ሰበብ ፈጻሚ በማጣት መቸገራቸውን ድርጅቱ ባዘጋጀው የአስተያየት መስጫ መዝገብ ላይ ማስፈራቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያሳያል።

ከተለያዩ አካባቢዎች ጉዳይ ለማስፈጸም እንደመጡ የገለጹት ቅሬታ አቅራቢዎች በተለይ በስብሰባ ሰበብ ለረዢም ጊዜ መጉላላታቸውን ባሰፈሩት የሃሳብ መስጫ ደብተር ላይ ለማንበብ ይቻላል። አስተያየት ሰጪዎች በዋነኝነት ያነሱት ችግር ባለስልጣኖች በስብሰባ ሰበብ ባለጉዳይ ለማስተናገድ አለመቻላቸውን ሲሆን፣ የብቃት ማነስም ችግርም ተጠቅሷል።

“ለማን ብሶታችንን እንናገር ፣ ጠዋት ስንመጣ ከሰአት ከሰዓት ስንመጣ ጠዋት፣ ቢሮ ኃላፊው የለም፣ ሂደት አስተባባሪው የለም፣ የድርጅቱና የመንግስት ሚዲያ በየመድረኮች ሚናገሩት ሌላ ፣

…የከተማው ህዝብ በመሬት እጦት፣ የመንግስት ሰራተኛው በደመዎዝ ማነስና ፣ተመርቆ ከቤተሰቡ ጋር ቁጭ ብሎ በመቅረቱ የገጠሩ ህብረተሰብ በማዳበሪያ ውድነት ተወጥሮ ፣ በሌትና በቀን የቁም ቅዠት አያሰቃየው አሁን ለማን ነግሮ መፍትሄ ያገኛል? ለመንግስት ቢነግሩ ከወረቀት የዘለለ የተግባር ፍሬ የለውም ኧረ ለማን እንንገረው?አምላክ አይፈጥን እንደሰው!እባክህ ጌታዬ የኢትዮጵያ አምላክ በ2007 ምርጫ ገላግለን ፣ በቸርነትህ መንግስት በዘር በዘመድ አዝማድ በገንዘብ እየተሸበበ በቁማችን እየተጓዝን ተቀበርን፡፡

…..ለአመራሮች በጣም ከፍተኛ የሆነ ስልጠና ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ባለስልጣኖቹ ድሃውን ህዝብ በማንገላታት የታወቁ መሆናቸው በአለም ታውቋል የነሱን ምቾት ካገኙ ለሌላው ምንም ደንታ የላቸውም……

…..ባሁኑ ሰዓት አቤት ባይ ሲበዛ ፍትህ ሰጪ ግን የለም፡፡ለምን ይሆን ህብረተሰቡን የተጣላው?እግዛብሄር ይሆን መንግስት ነው አልገባኝም…….

የሚሉት አስተያቶችን የያዙ ማስታሻዎች ለስሙ በተቀመጡ ያአስተያየት መቀበያ ደብተሮች ላይ ሰፍረው ይነበባሉ፡፡

የገዢው መንግስት ባለስልጣናት ከህዝቡ አስተያየት በመሰብሰብ አገልግሎት አሰጣጣችንን እናስተካክላለን እያሉ ቢናገሩም የአስተያየት ደብተሮችን እንደማይመለከቱ አስተያየት ሰጪዎች ገልጸዋል፡፡

Source:: Ethsat

The post በአማራ ክልል ነዋሪዎች በአገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች መማረራቸውን ተናገሩ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>