(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ በየቀኑ እየደረሱ ያሉ የመኪና አደጋዎች ቁጥር ከ እለት ወደ እለት እየጨመረ መሄዱ ነዋሪዎችን በከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደከተተ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ይናገራሉ:: በዚህ በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ እንኳ በጊዜው ስለመኪና አደጋዎችና ስለሚወድመው የሰው ሕይወትና ንብረት በተደጋጋሚ ጽፈናል:: አሁን ደግሞ ከአዲስ አበባ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው አራት ኪሎ የድል ሐውልት አደባባይ አካባቢ ከስድስት ኪሎ መስመር ወደ ለገሀር ይጓዝ የነበረ የአንበሳ ከተማ አውቶቡስ ባገጠመው የፍሬን ችግር ከአንድ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ የሁለቱም ተሽከርካሪ ሹፌሮች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል::
በዚህ የመኪና አደጋ በተሳፋሪዎች ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም አደጋው በፎቶ ግራፍ ላይ እንደምትመለከትት በጣም አሰቃቂ ነበር:: ከስድስት ኪሎ ከሚገኘው ቤታቸው ሃገር አማን ብለው ወደ ሥራቸው በማሽከርከር ላይ የነበሩትና ጉዳት የደረሰባቸው አቶ ግርም ጎርፉ የተባሉ ግለሰብ የአንበሳ አውቶቡሱ ድንገት መስመሩን ስቶ በመምጣት እንደገጫቸው ገልጸዋል::
The post በአዲስ አበባ አንበሳ አውቶቡሱ መንገድ ስቶ የቤት መኪናውን ገጨ appeared first on Zehabesha Amharic.