Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Sport: በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ 2 ወሳኝ ጨዋታዎች ይደረጋሉ * ማን. ሲቲ ከባርሴሎና ከባድ ግምት ተሰጥቶታል

$
0
0

manchester city
ከሰዓታት በኋላ የሚደረገው የዛሬው የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ዓለም በጉጉት እየጠበቀው ይገኛል:: በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ እንግሊዙ ማንችስተር ሲቲ ከስፔኑ ባርሴሎና እንዲሁም የጣሊያኑ ጁቬንቱስ ከጀርመኑ ቦሩስያ ዶርትመንድ ይጫወታሉ።

የሲቲ ጠንካራ መሆን ባርሴሎና ለዘጠኝ ተከታታይ ጊዜ በሻምፒዮንስ ሊጉ ሩብ ፍጻሜ ለመግባት በኢቲሃድ ስታዲየም ከባድ ፈተና ይገጥመዋል ተብሎ ይጠበቃል። በዚህ ጨዋታ ላይ የቀድሞው የሊቨርፑል አጥቂ ሉዩስ ስዋሬዝ ከእንግሊዝ ከወጣ ወዲህ የመጀመሪያውን የእንግሊዝ ምድር ጨዋታ ያደርጋል።

የባርሴሎናው አሰልጣኝ ሉዩስ ኢንሪኬ ሙሉ የቡድናቸውን ተጫዋቾች ይዘው ወደ እንግሊዝ ይጓዛሉ። በአንጻሩ በማንችስተር ሲቲ በኩል ያያ ቱሬ በቅጣት በጨዋታው ላይ የማይሰለፍ ሲሆን፣ ጀምስ ሚልነር ከጉዳት መልስ እንዲሁም አጥቂው ዊልፍሬድ ቦኒ በመጀመሪያው ጨዋታ ላይ ይሰለፋል።
city vs barca
የሲቲው አሰልጣኝ ማኑኤል ፔሌግሪኒ ባለፈው ዓመት በደርሶ መልስ በባርሴሎና 4 ለ 1 መሸነፋቸው ይታወሰል። በሌላ ጨዋታ ደግሞ ቦሩስያ ዶርትመንድን የሚያስተናግደው ጁቬንቱስ የመሃል አማካዩ አርቱሮ ቪዳል ከጉዳት አገግሞ ለጨዋታው ይደርሳል።

አሰልጣኝ ጀርገን ክሎፕ ቡድናቸው ቦርስያ ዶርትመንድ በኩል የተጫዋች ጉዳት ባለመኖሩ በሙሉ ቡድናቸው ጁቬንትሱን ይገጥማሉ፡፡

ማን. ያሸንፍ ይሆን?

The post Sport: በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ 2 ወሳኝ ጨዋታዎች ይደረጋሉ * ማን. ሲቲ ከባርሴሎና ከባድ ግምት ተሰጥቶታል appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>