Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በደብረ ማርቆስ የሰማያዊ እጩ የእስር ትዕዛዝ ወጣባቸው

$
0
0

debrezeytበምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ማርቆስ ከተማ ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ለተወካዮች ምክር ቤት የምርጫ እጩ ሆነው የቀረቡት አቶ ሳሙኤል አወቀ በፖሊስ የእስር ትዕዛዝ እንደወጣባቸው ታወቀ፡፡

የህግ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሳሙኤል አወቀ ከዚህ ቀደም ‹የዳኞችን ስም በማጥፋት› ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ገልጸው፣ አሁን በፖሊስ የወጣባቸው የእስር ትዕዛዝ መሰረቱ ምን እንደሆነ በውል ማወቅ አለመቻላቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ አስረድተዋል፡፡

‹‹አንድ የምርጫ ተወዳዳሪ ያለውን የኢሚውኒቲ መብት ረስተው ጉዳዩን በውል ባላወቅሁት ሁኔታ የእስር ትዕዛዝ ማውጣታቸው እኔን ከፖለቲካው ለማግለል ነው፡፡ አሁን ለስራ ጉዳይ ባህር ዳር ነኝ፡፡ በዚሁ ጉዳየን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች አስረድቼ በስልክ አውርተውበታል፡፡ አግባብ አለመሆኑንም አምነዋል፡፡ ግን እኔ ላይ ጫና ለማሳደር ትዕዛዙ እንደወጣ አውቄያለሁ›› ብለዋል አቶ ሳሙኤል፡፡

የወጣው የእስር ትዕዛዝ ‹‹በፖሊስ ታሰሮ እንዲቀርብ›› የሚል መሆኑን የገለጹት አቶ ሳሙኤል፣ በቀጣይ የፍርድ ቤት ቀጠሯቸው በስም ማጥፋት ለቀረበባቸው ክስ መከላከያ ማቅረብ እንደሚችሉ እየታወቀ ታስሮ ይቅረብ መባላቸው መሰረቱ ግልጽ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

The post በደብረ ማርቆስ የሰማያዊ እጩ የእስር ትዕዛዝ ወጣባቸው appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>