Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ለዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ ለምትገኙ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በሙሉ -ከኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል (CREW)

$
0
0

ኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል (CREW)

CREWላለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል ስለ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ዘርፈ ብዙ ችግሮች ምንነት ማህበረሰቡን ግንዛቤ ለማስጨበጥ በየዓመቱ የአለም አቀፍ የሴቶችን ወር ምክንያት በማድረግ በመጋቢት ወር ላይ ጉባኤ በማዘጋጀት  ሴቶችን  በሚመለከቱ በተለያዩ  ርዕሰ ጉዳዮች  ላይ ምሁራን ጥናታዊ ጽሑፎችን እንዲያቀርቡና፣ ለችግሮቹ መፍትሔ እንዲጠቁሙ በማድረግ ማህበረሰባችንን ግንዛቤ ለማስጨበጥ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ሴቶች በማህበራዊ፣ በኤኮኖሚና በፖለቲካ የሚደርስባቸውን ችግሮች በተለይም የተሻለ ኑሮ ፍለጋ በአረብ አገራት ተሰደው ስላሉ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች መብትን አስመልክቶ በየጉባኤዎቹ ሰፋ ያለ ትምህርታዊ ውይይቶች አካሂዷል።

ዘንድሮም የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል ለ፬ኛ ጊዜ የሚካሄድ ዓመታዊ ጉባኤ  አዘጋጅቷል፡፡ የዚህ  የ፬ኛው የኢትዮጵያ ሴቶች ጉባኤ መሪ ቃል የህዝባዊ ማህበራት ሚናና  የ2015 የኢትዮጵያ  ምርጫ  ነው።(THE ROLE OF CIVIL SOCIETY IN THE UPCOMING 2015 ETHIOPIAN ELECTION)

እንደሚታወቀው ሕዝባዊ ማህበራት ለአንድ ሀገር የዲሞክራቲክ ሥርዓት ምሥረታ ምሰሶ ናቸው፡፡ በሀገራችን ሰብአዊ መብት ለማስከበር በቆሙ ሕዝባዊ ድርጅቶች ላይ ማዕቀብ የጣለው በ2009 የወጣው ሕግ (The Charities and Societies Proclamation) ጸድቆ ተግባራዊ በመሆኑ ስለ ሰብአዊ መብቶችና የሴቶች መብት የማስከበር ስራ መስራት የማይቻልበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን፡፡

ስለዚህም ጉባኤው ስለሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መጠበቅና የመጻፍ፣ የመደራጀትና የመሰባሰብ መሠረታዊ  መብቶች በሌሉበት አገር ምን ዓይነት ምርጫ ይካሄዳል? በሚለው ጥያቄ ላይ የሚያጠነጥን ጥልቅ የሆነ ወቅታዊ ውይይት የሚካሄድበት ሲሆን፣ ምሁራን ጥናቶቻቸውን የሚያቀርቡበት በመሆኑ በዝግጅቱ ላይ የሁላችሁም መገኘትና ተሳትፎ ወሳኝ ነው። ስለዚህ ውድ ወገኖቻችን በዝግጅቱ ላይ በመገኘት የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታደርጉ በአክብሮት ተጋብዛችኋል።

ዝግጅቱ የሚካሄድበት ቦታ በSILVER SPRING SHARATON HOTEL ሲሆን

ቀኑ፦ ቅዳሜ MARCH 7, 2015 ነው፡፡

አድራሻው፦ 8777 GEORGIA AVENUE SILVER SPRING MD, 20910 ሲሆን ከመስብሰቢያ ሆቴሉ ጀርባ ነፃ የመኪና ማቆሚያ አለ፡፡

ሰዓቱ፦ ከጥዋቱ 9AM እስከ 5PM ነው፡፡

የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል

The post ለዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ ለምትገኙ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በሙሉ -ከኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል (CREW) appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>