Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Health: በትዳሬ ውስጥ ምንም ዓይነት ፀብና ግጭት አለመኖሩ ችግር ይኖረው ይሆን?

$
0
0

Young couple in bed, looking away from each other
አንዳንድ ጊዜ በትዳሬ ውስጥ አንድ የሆነ የጎደለ ነገር ይኖር ይሆን ስል አስባለሁ፡፡ ምክንያቱም እኔና ባለቤቴ ፈፅሞ ተጣልተን (ተደባድበን) አናውቅም፡፡ አይደለም መደባደብ ተጨቃጭቀን እንኳን አናውቅም፡፡ በእርግጥ ሁለታችንም የመጣነው እጅግ በጣም ወግ አጥባቂና ሃይማኖተኛ ከሚባሉ ቤተሰቦች ሲሆን ሁለታችንም አባትና እናቶቻችን ሲጨቃጨቁም ሆነ ሲደባደቡ አላየንም፡፡ በብዙ ነገር ተስማምተን እንኖራለን፡፡
በእርግጥ እውነት ለመናገር ትዳራችንና የፍቅር ግንኙነታችን በጣም ፍቅር የተሞላበት የሚባል አይደለም፡፡ ከዚህ ይልቅ ፀጥ ያለ…. የተረጋጋና ጥንቃቄ የተሞላበት ነው ቢባል ይበልጥ ይገልፀዋል፡፡ ለመሆኑ ውድ አማካሪ የሆነ ያጣነው ነገር ያለ አይመስልህም?
ሰፈር/
ዮዲት ነኝ ከ/ወሎ

ውድ ዮዲት፡- ግምትሽ ትክክል ነው፡፡ አ ዎ ን በትክክል ይኖራል፡፡ አንቺና ባለቤትሽ የፈለገውን ያክል የተጣጣማችሁና ፍፁም አብራችሁ የምትሄዱ ብትሆኑም እንኳን ሁለት የተለያያችሁ ሰዎች መሆናችሁን መዘንጋት የለባችሁም፡፡ ምናልባት ነገረኛ ላለመባል እየፈራችሁ ካልሆነ በቀር በየቀኑ አንድ ቤት ውስጥ እየኖራችሁ አንድም ቀን ተጣልተን አናውቅም ማለት የማይመስል ነገር ነው፡፡

እኔ በበኩሌ ፈፅሞ አንጋጭም የሚሉ ጥንዶች ‹ጥንቃቄ የተሞላበት የፍቅር ግንኙነት›› (Careful loving) ውስጥ ናቸው ነው የምለው፡፡ ከሁለት አንዳቸው ወይም ደግሞ ሁለቱም ማንኛውም አይነት ግጭት ወይም ፀብ የፍቅር ግኑኝነታችንን ይጎዳል ብለው ይሰጋሉ ፡ ፡ በዚህ የተነሳ በሚችሉት አቅም ሁሉ ፀብን ሲሸሹ ይኖራሉ፡፡ የዚህ ውጤቱ ታዲያ ህይወት ህይወት የማይሸት ደባሪ (አሰልቺ) የሆነ ትዳር ይሆናል፡፡

አንቺም እራስሽ የትዳር ህይወታችሁ ያን ያክል ፍቅር የተሞላበት ነው የሚባል አይነት እንዳልሆነ ነው የገለፅሽው፡፡ ነገር ግን ማወቅ ያለብሽ ነገር ንዴት፣ ቁጣ ሃዘን፣ ብስጭት….. ወዘተ ያሉትን አሉታዊ ስሜቶች በመውስጣችን አምቀን ስንይዛቸው ፍቅርና ርህራሄ እንዲርቁን እናደርጋለን፡፡ አንቺና ባለቤትሽም እነዚህን የፍቅርና ርህራሄ ስሜቶቻችሁን በደግነታችሁ እየገደላችኋቸው ነው፡፡

እንደ ገለፅሽው አንቺም ሆንሽ ባለቤትሽ የመጣችሁበት ቤተሰብ በአሁኑ ስብዕናችሁ ትልቅ ተፅዕኖ አሳድሮባችኋል፡፡ ብዙ ጊዜ እንደሚታወቀው ቁጥጥር ከሚያበዙ ወይም ወግ አጥባቂና በጣም ሃይማኖተኛ ቤተሰብ የሚወጡ ልጆች እንደ እንዴት ቁጣ …. ወዘተ ያሉ አሉታዊ ወይም ቅዱስ ያልሆኑ ስሜቶች ሃጢያት እንደሆኑ እየተነገራቸው ነው የሚያድጉት፡፡ ፍርሃትም እንደዚያው ሃጢያት ነው ይባላል፡ ፡ የእምነት ማጣት ምክልት ነውም ይባላል፡፡ በዚህ የተነሳ ባለቤትሽ የሚያናድድሽን ነገር እንኳን ቢያደርግ አንቺ የተሰማሽን ስሜት አምቀሽ ትይዥዋለሽ፡፡ ይህ ነገርም በየጊዜው እየተደጋገመ ሲሄድ በመጨረሻ ውጤቱ ታማኝነትና መቀራረብ የራቀው ትዳር ይሆናል፡፡

በእርግጥም መልካሙ ነገር አንቺም ሆንሽ ባለቤትሽ ችግሩን ተረድታችሁ ለውጥ ለማምጣት ፍላጎት አላችሁ፡፡ ለዚህ ደግሞ ሁሉንም ስሜቶቻችሁን በግልፅነት ለመጋራትና ትዳራችሁን መልሳችሁ እንደ አዲስ ለመገንባት ለራሳችሁ ቃል ግቡ፡፡ ጤናማና ደስታ የተሞላበት ትዳር ለመገንባት የሚረዱ ፅሁፎችን አንብቡ፡፡ የተለያዩ ትምህርታዊ ገለፃዎችን ተከታተሉ፡፡ ከ ሁሉም በላይ ግን ትዳራችሁን በየዕለቱ የሚከሰቱ ግጭቶችንና አለመግባባቶችን መቋቋም ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁንስ እያንዳንዷ ግጭት አልፋችሁ ወደ ፍቅራችሁ በተመለሳችሁ ቁጥር ፍቅራችሁ የበለጠ እያደገ እየጠነከረ እንደሚሄድ ሙሉ እምነት ይኑራችሁ፡፡

ይህ ጽሁፍ በቁምነገር መጽሄት ላይ ታትሞ ወጥቷል::

The post Health: በትዳሬ ውስጥ ምንም ዓይነት ፀብና ግጭት አለመኖሩ ችግር ይኖረው ይሆን? appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>