Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በሚኒሶታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለማህሙድ አህመድ ያላቸውን ክብር ገለጹ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) “የትዝታው ንጉስ” በሚል በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ላይ በትልቁ ስሙ የሚጠራው ድምፃዊ ማህሙድ አህመድ በሚኒሶታ ደማቅ የሙዚቃ ኮንሰርት አቀረበ::
Mahmud Ahemed – A day filled with tears
74ኛ ዓመቱን የያዘው አርቲስት ማህሙድ አህመድ ትናንት የቫለንታይን ደይን በማስመልከት በሚኒሶታ በተደረገው የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ያሳየው ብቃት ሙዚቃ ምን ያህል አብራው እንደተፈጠረች የሚያሳይ ነው ሲሉ በስፍራው የነበሩ ኢትዮጵያውያን አድናቆታቸውን ገልጸዋል::

ዛሬ በኮምፒውተር ድምጻቸውን እየሞረዱ የሚወጡት አርቲስቶች መድረክ ላይ ሲወጡ በሚሸማቀቁበት ዘመን ማህሙድ የሚታወቅበትን ከትዝታ እስከ ጉራጊኛ ዘፈኖች በማይቀየር ድምጹ ተጫውቶታል ያለን አንድ የሙዚቃ አዋቂ ይህ ዘመን የማይሽረውን ድምፃዊ በዓይኔ ዳግም ከረዥም ዓመታት በኋላ መድረክ ላይ በማየቴ ደስተኛ ነኝ ብሏል::

ማህሙድ ወደ መድረኩ ሲወጣ ሕዝቡ በከፍተኛ ጩኸትና ፉጨት የተቀበለው ሲሆን እርሱም ደረቱን በሁለት እጆቹ በመያዝ ለሕዝቡ ያለውን ፍቅር ገልጿል::

በሚኒሶታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተለይ ለአንጋፋ አርቲስቶች የሚሰጡት ክብር በአረአያነት የሚጠቀስ ሲሆን ከዚህ ቀደምም በተመሳሳይ ቴዎድሮስ ታደሰ ሲመጣ ክብራቸውን ገልጸዋል::

በሙዚቃ ሕይወት ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የቆየው ማህሙድ አህመድ ባለፈው ሳምንት በኤድመንተን ካናዳም ተመሳሳይ የሆነ ክብር በሕዝብ ዘንድ ማግኘቱን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከስፍራው ጠቁመውን ነበር::

በትናንትናው ዕለት በሚኒሶታ በተደረገውና ናዲ ፕሮሞሽን እና ዲጂ ሶሎ ባቀረቡት በዚህ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ በርካታ ሕዝብ ከመገኘቱም በላይ በመሃሙድ ሥራዎች በ እጅጉ ሲዝናና አምሽቷል::

በዚህ ኮንሰርት ላይ ወጣቱ ድምጻዊ ጃኪ ጎሲም ሥራዎቹን አቅርቧል::

ይህን ታላቅ ኮንሰርት ዘ-ሐበሻ በቭዲዮ አስቀርታዋለች – ሕዝቡ ለማህሙድ ያሳየውን ፍቅርም ይመልከቱበት:: ተከታታይ ቭዲዎችን ለማቅረብም እንሞክራለን::

ዘ-ሐበሻ በአንድ ወቅት ያቀረበችውን የማህሙድ አህመድን ታሪክ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

The post በሚኒሶታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለማህሙድ አህመድ ያላቸውን ክብር ገለጹ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles