Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ፓርላማው የሚኒስሮች ም/ቤት መመልከት የሚገባው ረቂቅ አዋጅ ላይ መወያየቱ ጥያቄ አስነሳ

$
0
0

parlama
- የአካባቢና የደን ሚኒስቴር ሊቋቋም ነው
- የሁለት ሚኒስቴር መ/ቤቶች ስያሜ ይሻሻላል

በፍሬው አበበ

የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት በውክልና ለሚኒስትሮች ም/ቤት የሰጠውን ሥልጣን ሥር የሚወድቀውን ረቂቅ አዋጅ እንዲያጸድቅ መቅረቡ ጥያቄ አስነሳ።
ፓርላማው በትላንት ውሎው የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ታጥፎ “የአካባቢና ደን ሚኒስቴር” የተባለ አዲስ ሚኒስትር መ/ቤት እንዲቋቋም፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴርን “የከተማ ልማት፣የቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር”፣ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር “የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር”፣ በሚል ስያሜው እንዲቀየሩ የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ ማሻሻያ ውስጥ ቀርቦለት ተወያይቶበታል።
የአንድነት ፓርቲ ተመራጭ የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ ባቀረቡት አስተያየት የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ቁጥር 691/2003 አንቀጽ 34 የፓርላማው ሥልጣን ለሚኒስትሮች ም/ቤት እንዲተላለፍ በአብላጫ ድምጽ መወሰኑን አስታውሰው የፌዴራል አስፈጻሚ አካላትን እንደገና ማደራጀትን በተመለከተ ይህ አንቀጽ “የሚኒስትሮች ም/ቤት አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ደንብ በማውጣት፣ ማንኛውም አስፈጻሚ አካል እንዲታጠፍ፣ ከሌላ ጋር እንዲዋሃድ ወይም እንዲከፋፈል በማድረግ፣ ተጠሪነቱ ወይም ሥልጣንና ተግባሩ እንዲለወጥ በማድረግ ወይም አዲስ አስፈጻሚ አካል እንዲቋቋም በማድረግ የፌዴራል አስፈጻሚ አካላትን እንደገና የማደራጀት ሥልጣንና በዚህ አዋጅ ተሰጥቶታል” በሚል መደንገጉን በማስታወስ ይህን አዋጅ የማጽደቅ ሥልጣን አለአግባብ ወደሚኒስትሮች ም/ቤት የተዛወረ ቢሆንም ህግ በመሆኑ ይህ ም/ቤት አዋጁን ለማጽደቅ ሥልጣን አለው ወይ የሚል ጥያቄ አዘል አስተያየት አቅርበዋል።
ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ በበኩላቸው በተለይ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የሚለው ስያሜ ወደ ከተማ ልማት፣ የቤቶችና የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተቀየረበት አግባብ ግልጽ እንዳልሆነላቸው ተናግረዋል። “ኮንስትራክሽን” የሚለው ቃል ቤቶችንም እንደሚመለት የጠቀሱት ዶ/ሩ ማብራሪያው ላይ ገጠሩንም ለማካተት መታሰቡን መመልከቱን አስታውሰው ይህ ከሆነ መባል ያለበት የከተማና የገጠር ልማት የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ነው ብለዋል።
የአደረጃጀት ለውጥ በዚህ ወቅት ማድረግ ለምን አስፈለገ የሚሉ ጥያቄ አዘል አስተያየቶችና ከዕድገትና ትራንሰፎሜሽን ዕቅዱን ለማሳካት አደረጃጀቶች ከላይ እስከታች ተዋቅረው ርብርብ በሚደረግበት በዚህ ወቅት አዲስ አደረጃጀት መምጣቱ ሥራውን ሊጎዳው አይችልም ወይ የሚሉ ሥጋቶች በም/ቤት አባላት ተንጸባርቀዋል።

ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>