Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ሲሸልስ 4 የደደቢት ተጨዋቾች ሃገሯ እንዳይገቡ አገደች * ቅዱስ‬ ጊዮርጊስ እና ደደቢት በካፍ ክለቦች ጨዋታቸውን ነገ ቅዳሜ ያደርጋሉ

$
0
0

ለአፍሪካ የክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግ የማጣሪያ ጨዋታን ለማድረግ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ አባላት አልጄሪያ ይገኛሉ።

ቅ.ጊዮርጊስ የፊታችን ቅዳሜ ምሽት 12:00 ሰአት ከአልጄሪያው ኤም ሲ ኤል ኤልማ ክለብ የሚያደርገው ጨዋታ የቀጥታ ስርጭቶች በቲቭ እንደሚያገኝ የደረሱን መረጃዎች ያመላክታሉ::
st. George
ሌላኛው የኢትዮጵያ ተወካይ ደደቢት ከሲሸልሱ ኮት ዲ ሆር ጋር ቅዳሜ በ9 ሰአት ለሚያደርገው የካፍ ኮንፌዴሬሽን ጨዋታው ወደ ስፍራው በኬንያ አድርጎ ቢያመራም አራት የደደቢት ክለብ ተጨዋቾች በቪዛ ምክንያት ከሲሺየልስ ተመለሱ መመለሱን ኢትዮ ኪክ ኦፍ ዘገበ::

በየአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የቅድመ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ለማካሄድ ትናንት ወደ ሲሺየልስ ካመራው የደደቢት እግር ኳስ ክለብ 29 የልኡካን ቡድን አባላት መካካል በቪዛ ምክንያት አራት የውጭ ሃገር ተጨዋቾች ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ተደረገ፡፡
dedebit
የሲሺየልስ ኢሚግሬሽን ባላስልጣን እ.አ.አ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ ያዋለውንና በምእራብ አፍሪካ ሃገሮች ዜጎች ላይ ተፈጻሚ እንዲሆን የተደረገው ጥብቅ የጉዞ መመሪያ ባለመከበሩ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ የተገደዱት አዲሱን ጋናዊ ግብ ጠባቂ ጨምሮ የክለቡ ተጨዋቾች ሱሊማና አቡ፣ሞሃመድ አዳሙ፣ሳሙኤል ሳኑሚ እና ጋብርኤልአህመድ ሹኢብ ናቸው፡፡

ከደህንነት ስጋት ጋር ተያይዞ የሲሺየልስ ኢሚግሬሽን ባለስልጣን ባወጣው ጥብቅ መመሪያ መሰረት ከምእራብ አፍሪካ አገሮች ለማንኛውም ጉዳይና ተልእኮ ወደ ሲሺየልስ ለሚያመሩና አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሱ የመግቢያ ቪዛ የሚጠይቁ ተጓዦች በቅድሚያ ህጋዊ ፓስፖርታቸውን ወደ ሲሺየልስ በመላክ ፈቃድ መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
አራቱ ተጨዋቾች ያጋጠማቸውን የመግቢያ ቪዛ ችግር ለመፍታት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዲስ አበባ ከሚገኘው የሲሺየልስ ኤምባሲ ጋር በመነጋጋርና ተጨማሪ የጉዞ ሰነዶች በመላክ እንዲሁም ከኤምባሲው የትብብር ደበዳቤ እንዲጻፍና በተላያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ተከታታይ መልእክቶች እንዲተላላፉ ቢያደርግም በመመሪያው ጥብቅነት የተነሳ ሊሳካ እንዳልቻለ ታውቋል፡፡ ከሲሺየልስ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲመለሱ የተደረጉት አራት የደደቢት እግር ኳስ ክለብ ተጨዋቾች ነገ ከቀኑ 6፡00 ላይ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ይጠበቃል፡

ክለቡ ቌሚ ግብ ጠባቂዎቹ በጉዳት ምክንያት ከቡድኑ ጋር ያልተጓዙ ሲሆን አዲሱ ጋናዊ ግብ ጠባቂ ለቡድኑ ቌሚ ተሰላፊ ይሆናል በሚል ተስፋ የተጣለበትም ቢሆን የሲሸልስ መንግት ህግ መሰረት ደደቢት ጋናዊውን ግብ ጠባቂ ጨምሮ የምህራብ አፍሪካ ተጨዋቾቹን ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ እና ያለ ቌሚ ግብ ጠባቂ ከሜዳ ውጭ ጨዋታውን ያደርጋል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ

“የመጀመሪያ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታችንን ለማድረግ ተዘጋጅተናል”

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከምስረታው ጀምሮ በወጣቶች በማመን ከታች ቡድን በማሳግ እና እድል በመስጠት ያምናል፡፡ በዘንድሮው አመትም ይኸው አመኔታ ቀጥሎ በዛ ላሉ ወጣቶች ዕድል መስጠት ተችሏል፡፡
በተለይም አምና በተስፋ ቡድን ሲጫወት የምናውቀውና ዘንድሮ የዋናው ቡድን አባል የሆነው አንዳርጋቸው ይላቅ፤ ባለፈው አመት በቢጫ ቴሴራ አድጎ በዋናው ቡድን ሲጫወት የነበረው እና ዘንድሮ በፕሪምየር ሊጉ ብቻ በግራ መስመር በኩል በመሰለፍ ከአስር በላይ ጨዋታዎችን በቋሚነት መጀመር የቻለው ዘካርያስ ቱጂ ከዚህ በተጨማሪም ባለፈው አመት የከ17 አመት በታች ቡድናችን አምበል የነበረው እና ዘንድሮ ቡድናችን ከአርባ ምንጭ፤ ወልዲያ እና ደደቢት ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይ መሳተፍ የቻለው አቡበከር ሳኒ ለዚህ ምሳሌያችን ተጠቃሾች ናቸው፡፡

እነዚህ ለምሳሌ ያህል የጠቀስናቸው ታዳጊ ተጨዋቾች በሀገር ውስጥ እድል ሲሰጣቸው የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ ቡድናችን በመጪው ቅዳሜ በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ከአልጄርያው ኤም ሲ ኤል ኡልማ ጋር በሚካሂደው ጨዋታ ላይ ቁጥራቸው በዛ ያሉ ወጣቶች እና ለአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ እንግዳ የሆኑ ተጨዋቾች ይሳተፋሉ፡፡
ሰልሃዲን ባርጌቾ፤አንዳርጋቸው ይላቅ፤ዘካርያስ ቱጂ፤ መሀሪ መና፤ዳዋ ሁጤሳን የመሳሰሉ ተጨዋቾች የመጀመርያ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡ይህንን ምክንያት በማድረግም ዘካርያስ ቱጂ እና አንዳርጋቸው ይላቅን በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ላይ በመሳተፋቸው ምን እንደተሰማቸው ጠይቀናቸው ነበር፡፡

ዘካርያስ ቱጂ ” የአንድ ተጨዋች ትልቁ ህልሙ ክለቡን በሊግ እና በአህጉራዊ ውድድሮች ላይ ጥሩ ተሳታፊ አድርጎ ሻምፒዮን መሆን ነው ሁለተኛው ደግሞ ሀገርህን በአለም አቀፍ ውድድሮች መወከል ነው፡፡ እኔ እንደ አንድ ተጨዋች ዘንድሮ በሊጉ ላይ በአብዛኛው ጨዋታዎች ተሰልፌያለሁ፡፡ በዚህም ደስተኛ ነኝ ነገር ግን እንደነ ደጉ ፤ አዳነ እና አሉላ ያሉትን የቡድን ጓደኞቼን ስመለከት ገና ብዙ መስራት ያሉብኝ ነገሮች እንዳሉ ይሰማኛል፡፡ የመጀመሪያውን አሰልጣኞቼ እና የቡድን ጓደኞቼ የሚነግሩኝን እየሰማሁ አሁን የደረስኩበት ቦታ ደርሻለሁ፡፡አሁን ቀጣዩ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታም እኔ የምፈተንበት ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡ ነገር ግን የመጀመርያ ጨዋታዬ እንደመሆኑ መጠን በጥሩ ጤንነት እና ጥሩ ስራን እየሰራሁ በትኩረት በመዘጋጀት ላይ እገኛለሁ፡፡”
አንዳርጋቸው ይላቅ አምና የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሚያዘጋጀው የተስፋ ቡድኖች ጨዋታ ላይ ሲጫወት የነበረ ተጨዋች ነው፡፡እንደ ዘካርያስ ሁሉ አንዳርጋቸውም ታላላቅ ተጨዋቾች የደረሱበት ደረጃ ለመድረስ ጠንክሮ እየሰራ እንደሆነ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ድህረ ገፅ ተናግሯል፡፡

“ትልቅ ቡድን ውስጥ በወጣትነት መግባት ጥሩነቱ ከታላላቅ ተጫዋቾች ጋር እንድትጫወት እና ከእነሱም ብዙ ልምዶችን እንድትቀስም ያደርግሀል፡፡በተለይም ለእኛ ቡድን ውስጥ ለወጣቶች እድሎች በብዛት ስሚሰጡ ወጣቶች የመማርያ ቦታን ያገኛሉ፡፡ እኔም ያንኑ እያደረግኩ እገኛለሁ፡፡ለሚመጣው ጨዋታም ለመጀመሪያ ጊዜ ከሀገር ውጪ ልጫወት ነው፡፡ በዚህ ደግሞ እጅግ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ መጪውን ጨዋታም አሸንፈን ወደ ቀጣዩ ዙር እንደምናልፍ እርግጠኛ ነኝ በማለት ሃሳቡን አካፍሏል፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኤል ኡልማ ጨዋታ በመጪው ቅዳሜ በኢትዮጵያውያን ሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ ሁለት ሰአት ይከናወናል፡፡

The post ሲሸልስ 4 የደደቢት ተጨዋቾች ሃገሯ እንዳይገቡ አገደች * ቅዱስ‬ ጊዮርጊስ እና ደደቢት በካፍ ክለቦች ጨዋታቸውን ነገ ቅዳሜ ያደርጋሉ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>