ስለ አመጋገብ ስነስርዓት ምክር ብጤ ካሻችሁ ናስር ቻድሊን አድምጡት፡፡ ታሪኩን እህ ብላችሁ ስሙ፡፡ በዚህ የውድድር ዘመን ያልተጠበቀ ነገር እየሰሩ ከሚገኙ ተጨዋቾች አንዱ ነው፡፡ በቶተንሃም ሆትስፐር አይነኬ ሆኗል፡፡ ይህ ይሆናል ብለው የገመቱ ጥቂት ናቸው፡፡ ቻድሊ ከአምናው ይልቅ ዘንድሮ ሸንቃጣ፣ ፈጣን እና ጠንካራ ሆኗል፡፡ የተሻለ ተጨዋች ሆኗል፡፡ ለቡድኑ ይበልጥ ጠቃሚ ከሆኑት አንዱ ነው፡፡ ማውሪሲዮ ፓቼቲኖ አንገብጋቢ ጉዳይ ሲገጥማቸው ከጉድ ያወጡኛል ብለው ከሚከባቸው ተጨዋች ተርታ ተሰልፏል፡፡ የእርሱ ታሪክ የግለሰብ እመርታን የሚገልፅ ነው፡፡ ከእጁ ወጥቶ የነበረን ዕድል መልሶ ማግኘት ችሏል፡፡
ቻድሊ ትኩረቱን ወደ አዲስ አቅጣጫ መርቷል፡፡ በአመጋገቡ ላይ አተኩሯል፡፡ ሃሳቡ የተጠነሰሰው ባለፈው ጁላይ በአንድ የጣልያን የህክምና ማዕከል ነው፡፡ ‹‹ጤናማ በሆነ መንገድ እንዴት መመገብ እንዳለብኝ የተማርኩት እዚያ ነው፡፡ ምክንያቱም ለሰውነትህ በቶሎ እንዲያገግም በተለየ መንገድ መመገብ አለብህ›› ሲል ሆቴል ማራኖን እንዲጎበኝ በቪንሶ ካምፓኒ እና ባለቤቱ ጥቆማ የተደረገለት ቻድሊ አጋጣሚውን ያስታውሳል፡፡ ካሪም ቤንዜማም ወደዚያ ጎራ ብሏል፡፡ ‹‹ደምህን ይወስዱ እና ምን መመገብ እንዳለብህ እና ሰውነትህ ሊቋቋመው የማይችለውን ነገር ይፈትሻሉ፡፡›› በዚህ ምክንያት ቻድሊ አሁን የወተት ተዋፅኦዎችን አይጠቀምም፡፡ ‹‹ከአሁን በኋላ ወተት መጠጣት እንደሌለብኝ ምክር ለገሰኝ፡፡ አልፎ አልፎ ብቻ የአኩሪ አተር ወተት እጠቀማለሁ፡፡ አይብ በጭራሽ አልመገብም፡፡ የምበላው አትክልት እና ፍራፍሬ መጠንም የተወሰነ ነው፡፡ ከምግብ በፊት ፍራፍሬ መብላት ጥሩ ነው፡፡ በተለምዶ ፍራፍሬ የምምገበው ከምግብ በኋላ ነበርር፡ ነገር ግን በቅድሚያ መብላት ጠቃሚ መሆኑን ተምሬያለሁ፡፡ በሳምንት አንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ ስጋ እበላለሁ፡፡ በተረፈ በአብዛኛው የምጠቀመው ዓሳ እና ዶሮ ነው፡፡ ያንን ማድረጌ እንደጠቀመኝ አስባለሁ›› ካለ በኋላ ‹‹የተወሰነ ክብደት ቀንሼያለሁ›› ሲል ያክላል፡፡
ቻድሊ ለቅድመ ውድድር ዝግጅት ወደ ቶተንሃም የተመለሰው ቤልጅየም ከዓለም ዋንጫው ውጪ ከሆነች ከ17 ቀናት በኋላ ነው፡፡ ነገር ግን ማረጋገጥ የሚፈልገው ነጥብ ነበር፡፡ ‹‹በቶተንሃም ያልተሳካ ዓመት ካሳለፍኩ በኋላ ወደ ተሻለ ብቃት የተሸጋገርኩት በስነ ልቦና ጠንካራ ስለነበርኩ ነው›› በማለት ሀቁን አምኖ ይቀበላል፡፡ ባለፈው ጃንዋሪ ስዋንሲ ሲቲ እና ኦልምፒያኮስ ሊያስፈርሙት ጥረት አድርገዋል፡፡ ነገር ግን ባለፈው ክረምት የትኛውንም ጥያቄ ላለመስማት ቁርጥ አቋም ያዘ፡፡ በክለቡ ቆይቶ ለቦታው መፋለምን መረጠ፡፡ ‹‹ይህንን የመሰለ ክለብ መልቀቅ አልፈለግኩም፡፡ የምለቀቅ ቢሆን እንኳን በኋላ በር ሾልኬ መውጣት ፍቃዴ አይደለም››
ፖቼቲኖ እያንዳንዱ ተጨዋች እራሱን የሚያሳይበት ዕድል እንደሚሰጠው ለቻድሊ ነገረውታል፡፡ ቤልጅየማዊው የሚፈልገውም ያንን ነበር፡፡ ‹‹ከእረፍት በኋላ አዕምሮዬን ነፃ ማድረግ እና ተመልሼ ልምምዴን መስራት ፈለግክኩ፡፡ በቀጥታ ያመራሁት ወዶ ልምምድ ነው፡፡ በተቻለኝ መጠን ሸንቃጣ እና ፈጣን ለመሆን ጥሬያለሁ፡፡ ከሁለት ሳምንታት በኋላ በውድድር ዘመኑ ለመጀመሪያ ጊዜ የመጫወቻ ዕድል ተፈጠረልኝ፡፡ አጋጣሚውን ልጠቀምበት ፈለግኩ፡፡ ደግሞም አደረግኩት፡፡››
ቻድሊ ፈታኙን የፖቼቲኖ የቅድመ ውድድር ዝግጅት ሲቀላቀል በቂ ዝግጅት አድርጎ ነበርር፡ በክረምቱ ያደረገው የማጠናሪያ ስራ ጠቅሞታል፡፡ ቻድሊ ስለ ጤና እና የአካል ብቃት የሚያወራው በተመስጦ ነው፡፡ በሰሜን ለንደን በሚገኘው የውድ ግሪን ቤተመፅሐፍት ግቢ የቶተንሃም ሆትስፐር ፋውንዴሽን ወደ 2 ሺ ለሚጠጉ የአካባቢው ነዋሪዎች የጤና ምርመራ ሲያደርግ በቦታው ተገኝቶ ነበር፡፡ ‹‹ሰዎች እራሳቸውን ሲጠብቁ መመልከት ያስደስታል፡፡በየጊዜው ክትትል አለማድረግ የሚያስከትለው ጣ ማወቅም መልካም ነው›› ሲል አስተያየቱን ይሰጣል፡፡
ባለፈው ክረምት ፖቼቲኖ ቡድኑን ያሰሩ የነበረው ልምምድ ያን ያህል አልከበደውም፡፡ ከዚህ ቀደምም ቢሆን ጥሩ አትሌት የነበረው ተጨዋች አሁን ይበልጥ ብቁ ሆኗል፡፡ ‹‹ከባድ ነበር›› ሲል ቻድሊ አጋጣሚውን መለስ ብሎ ያስታውሳል፡፡ ‹‹ነገር ግን ተመችቶኛል፡፡ ምክንያቱም ሰውነቴ ተላምዶታል፡፡ ሰውነትህ የሚቋቋመው ከሆነ የበለጠ ጠንካራ ትሆናለህ፡፡ ምንም እንኳን ረዥም የሚባል የቅድመ ውድድር ዝግጅት ባይሆንም የተሳካ ጊዜ አሳልፌያለሁ፡፡ ተጨማሪ ሁለት ሳምንታት ልምምዱን ሰርቼ ቢሆን ኖሮ የበለጠ እበረታ ነበር፡፡ ነገር ግን ያንን ያህል ዝግጅት ማድረጌ በራሱ ጠቅሞኛል፡፡
ቻድሊ የሚናገረው በተለሳሰለ አንደበት ነው፡፡ ነገር ግን ከአንደበቱ የመወጡት ቃላት ጥረቱ ፍሬያማ ከሆነለት ሰው የሚደመጡ እና እርግጠንነት የሚነበብባቸው ናቸው፡፡ በ2013 ቡድኑን የተቀላቀሉ ተጨዋቾች በሙሉ ከወጣባቸው ዋጋ ተመጣጣኝ የሆነ እንቅስቃሴ እያሳዩ ነው ማለት አይቻልም፡፡ የትኛውም ተጨዋች ጋሬት ቤልን ሊተካ አይችልም፡፡ ነገር ግን ለቻድሊ ዝውውር የወጣው 7 ሚሊዮን ፓውንድ ውጤታማ ይመስላል፡፡
ተጨዋቹ ቶተንሃምን የተቀላቀለው ቦስቲቭ ማክላኒን ስር የተጫወተበትን ኤፍ ሲ ትዋንቴ ለቅቆ ነው፡፡ የቀድሞ አለቃውን ‹‹ጥሩ አሰልጣኝ›› ብሎ የሚገልፀው ተጨዋች በቀያዩ የውድድር ዘመን በእርሳቸው የሚመራው ደርቢ ካውንቲ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ አድጎ በተቃራኒ እንደሚገጥማቸው ተስፋ ያደርጋሉ፡፡ የማጥቃት እንቅስቃሴን በሚያቅዱበት መንገድ ፖቼቲኖ እና ማክላረን በተወሰነ መልኩ እንደሚመሳሰሉ ቢያንምንም ቻድሊ ይህን ለመሰለው የአካል ብቃት ዝግጅት እንግዳ ነው፡፡ ወዶታልም፡፡ ‹‹በሆላንድ የዚህን ያህል ጠንካራ ልምምድ አንሰራም ነበር፡፡ በአካል ብቃት ላይ የተመሰረተው ነገር ያን ያህል አስፈላጊ አልነበረም፡፡ የተለየ ነው፡፡ በዚህ መንገድ ልምምድ መስራታችን ይጠቅመናል፡፡ ከሌሎች ቡድኖች የተሻለ የአካል ብቃት እንዲኖረን ያደርጋል፡፡››
ለጊዜው የሚታወቀው ይህን ያህል ነው፡፡ ቻድሊ ከአብዛኞቹ ተጨዋቾች በተሻለ የአካል ብቃት ላይ ይገኛል፡፡ አዲስ የአመጋገብ ስርዓት በመከተሉ በክለቡ ለመቆየት በመወሰኑ እና አዲሱን ስርዓት በፀጋ በመቀበሉ ፖቼቲኖ የሚፈልጉት አይነት ተጨዋች ሆኗል፡፡ መመሪያዎችን ያከብራል፡፡ ታትሮ ይሰራል፡፡ ከኳስ ጋር እና ያለኳስ በቂ ጥረት ያደርጋል፡፡ ወደተቃራኒ ቡድን የፍፁም ቅጣት ምት ክልል ሰብሮ በመግባት ጎሎችን ያስቆጥራል፡፡ ከወዲሁ በፕሪሚየር ሊጉ ብቻ ሰባት ጎሎችን በስሙ አስመዝግቧል፡፡ ከእርሱ የበለጠ ጎል ማስቆጠር የቻለው የመስመር ተጨዋች ኤደን ሃዛርድ ብቻ ነው፡፡
በዩሮፓ ሊግ ጨዋታ ኤኢኤል ሊማሶልን ሲገጥሙ ተቀይሮ በመግባት የውድድር ዘመኑን የመጀመሪያ ጨዋታ ያደረገው ቻድሊ በኦገስት 24 ኪውፒአርን በሜዳቸው ሲያስተናግዱ በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ተካተተ፡፡ ጨዋታውን በግራ መስመር ላይ ሆኖ የጀመረው ቤልጅየማዊ ወደ ፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን ሰብሮ እየገባ ሁለት ጎሎችን አስቆጠረ፡፡
ከዚያ በኋላ የሚያቆመው አልተገኘም፡፡ ‹‹የመጀመሪያ ጨዋታዬ በእጅጉ ጠቅሞኛል፡፡ ሁለት ጊዜ ኳስ እና መረብ ማገናኘት መቻሌ በራስ መተማመኔን አሳድጎታል›› ሲልም የውጤታማነቱን ምክንያት አካፍሏል፡፡ ነር ግን የሚናውን ‹‹ምስጢር›› ለማውጣት ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ በአጭሩ ብዙ እንቅስቃሴ እና ሩጫ እንደሚያስፈልገው ገልፅዋል፡፡ በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት የመጀመሪያ ጨዋታ ቼልሲን አስተናግደው 5-3 ሲያሸንፉ ዳኒ ሮስ ሁለተኛውን ጎል ከማስቆጠሩ በፊት ቻድሊ የሞከረውን ኳስ የጎሉ ቋሚ መልሶበታል፡፡ አምስተኛውን ደግሞ እራሱ አስቆጥሯል፡፡
በኦገሰት ቻድሊ አሰልጣኝ ፖቼቲኖ በሚመርጡት 4-2-3-1 ፎርሜሽ ከአጥቂ ጀርባ ካሉት ሶስት ቦታዎች አንዱን ለማግኘት ብርቱ ፉክክር ማድረግ ነበረበት፡፡ ጊልፊ ሱጉርሰን ተሸጠ፡፡ ልዊስ ሆልትሊይ በውሰት ተሰጠ፡፡ ቻድሊ ከፍተኛ ጥረት በማድረጉ ከአሮን ሌነን፣ አንድሬስ ታውንለሰንድ እና ኤሪክ ላሜላ ቀድሞ የመጀመሪያ ተሰላፊ መሆን ቻለ፡፡ ከስፐርስ የአጥቂ አማካዮች በበርካታ ጨዋታዎች ላይ በመሰለፍ የሚቀድመው ክርስቲያን ኤሪክሰን ብቻ ነው፡፡ ለዚህ ስኬቱ ቅድሚያውን የሚወስደው ያለኳስ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ውጤታማ መሆኑ ነው፡፡ ፖቼቲኖ በሚመርጡት የአጨዋወት ዘይቤ በሜዳው የላይኛው ክፍል ፕሬስ ማድረግ እጅጉን ይበረታታል፡፡ ኳስ በተነጠቁ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ሰከንዶች እንዴት ፕሬስ እንዲያደርጉ እንደታዘዙም ያብራራል፡፡ ‹‹በጥሩ የአካል ብቃት ላይ እገኛለሁ፡፡ በዚህ የውድድር ዘመን በአብዛኞቹ ጨዋታዎች ላይ ተሳትፌያለሁ፡፡ አሰልጣኙ በእኔ ላይ እምነት አለው፡፡ ይህም በራስ መተማመኔን አሳድጎታል፡፡››
ማንኛውም በመሻሻል ላይ ባለ ቡድን ውስጥ የሚገኝ ሰው እንደሚሰማው ሁሉ ቻድሊ ደስተኛ መሆኑ በግልፅ ይነነባል፡፡ በእርግጥ የደስታው ምንጭ የቡድኑ ውጤት ብቻ አይደለም፡፡ ከቡድን ጓደኞቹ ጋር ጥሩ ውዳጅነት መስርቷል፡፡ ያም ቢሆን ሁሌም ቢሆን የሚያሻሽለው ነገር አያጣም፡፡ ምክንያቱም ልቆ መገኘት ይሻል፡፡
The post Sport: የአሰልጣኙን ቀልብ የገዛው ቻድሊ ምስጢር appeared first on Zehabesha Amharic.