(ነገረ ኢትዮጵያ) የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ህዳር 28 ቀን 2007 ዓ.ም ጠርቶት ለነበረው የአዳር ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳ በራሪ ወረቀት ሲበትን በፖሊስ ተይዞ በእስር ላይ የቆየው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ጥፋተኛ ተብሎ የ2 ወር ከ10 ቀን የቅጣት ውሳኔ ተላለፈበት፡፡
ህዳር 24 ቀን 2007 ዓ.ም ‹‹ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ፡- ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› የሚል አርዕስት ያለውና በትብብሩ ፓርቲዎች የተዘጋጀውን የተቃውሞ ሰልፍ መቀስቀሻ በራሪ ወረቀት ሲበትን በአዲስ አበባ በፖሊስ የተያዘውና ‹‹የመንግስትን ስም በማጥፋት›› ክስ ተመስርቶበት ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሲታይ የቆየው አቶ ሲሳይ ዘርፉ ጥፋተኛ ተብሎ ቅጣቱ ተወስኖበታል፡፡
ሆኖም ግን አቶ ሲሳይ በፖሊስ ከተያዘበት ህዳር 24 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ ዋስትና ተከልክሎ በእስር ላይ በመቆየቱ ዛሬ የካቲት 3 ቀን 2007 ዓ.ም የተላለፈበትን የ2 ወር ከ10 ቀን የቅጣት ውሳኔ መጨረሱ ተገልጾ ከእስር እንዲፈታ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡
The post በራሪ ወረቀት የበተነው የሰማያዊ አባል 2 ወር ከ10 ቀን ቅጣት ተበየነበት appeared first on Zehabesha Amharic.