የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ (አወጋን) አመራሮች በዛሬው እለት እንደገለጹልኝ ከሆነ የደቡብ ወሎ ዞን የደህንነት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ፍትዊ ግደይ ወረኢሉ ከተማ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ የአቶ ፍትዊ ባለቤት ባሉበት በአወጋን አባላት በጥይት መገደላቸው የታወቀ ሲሆን አቶ ፍትዊ የደቡብ ወሎን ሠው በከፍተኛ ሁኔታ ሲያስሩ ሙስሊሙን «ፅንፈኛ»፣ ክርስቲያኑን «የድሮ ስርዓት ናፋቂ» በማለት በወሎ ክፍለ ሐገር ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የወሎ ሙስሊምና ክርስቲያንን ለመከፋፈል የሞከረ ግለሠብ እንደነበረ የተገለፀ ሲሆን የአቶ ፍትዊን ግድያ ተከትሎ በወረኢሉ ከተማ ፍተሻው በከፍተኛ ሁኔታ መጠናከሩን ለመታዘብ መቻሉን አመራሮቹ ይገልፃሉ።
በመጨረሻም የአቶ ፍትዊ ግደይ ግድያ ለሌሎች የህወሓት አመራሮች እና ጀሌዎች ትምህርት ይሆን ዘንድ የሟቹን ግለሠብ በሞተበት ሠዓት የተነሳውን ፎቶ ከነሙሉ መረጃው በድህረ ገፆች እና በማህበራዊ ሚዲያዎች እንደሚለቀቅ አስታውቀዋል።
~~ሁኔ አቢሲኒያ~~
The post በአማራ ክልል የደቡብ ወሎ ዞን የደህንነት ቢሮ ሀላፊ አቶ ፍትዊ ግደይ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ተገደሉ፤ appeared first on Zehabesha Amharic.