(ከኢየሩሳሌም አርአያ)
ልኡል ገ/ማርያም የተባለ የሕወሐት አባልና ዳኛ በከፍተኛ ወጪ በመንግስት እየታከመ መሆኑ ታውቋል። በዶ/ር ታዬ ወ/ሰማያት፣ በቅንጅት አመራሮችና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ እድሜ ልክና ሞት የፈረደ ነው።
ዙቤር የተባለ ሃብታም የገዛ ጓደኛውን በውሻ እያስነከሰ በጥይት ደብድቦ ከገደለው በኋላ ጉዳዩ የቀረበው ልዑል ዘንድ ነበር። የፈርደበት 6 አመት በማለት ሲሆን ከፍተኛ ገንዘብ ተቀብሎ ይህን ፍርድ ተብዬ እንዳስተላለፈ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ያስታውሱታል።
ይግባኝ የተጠየቀበት ዙቤር 22 አመት ፍርድ እንደተላለፈበትም ይታወሳል። ገዢው ፓርቲ ፖለቲካዊ ነክ ክሶችን በቀጥታ የሚመራው ወደ ልዑል ሲሆን አስቀድሞ ምን ፍርድ መስጠት እንዳለበት ተያይዞ ይነገረዋል። ዳኛ ተብዬው ልዑል ገ/ማርያም በልጆቹ እናት ላይ 5 ሴቶች በመወሸሙ ባለቤቱ ፍቺ ፈፅማለች። ባለፈው አመት በጠና በመታመሙ ወደ ደቡብ አፍሪካ ተልኰ ከፍተኛ ህክምና የተደረገለት ሲሆን ለህክምናው 550ሺህ ዶላር ወጪ እንደተደረገ ተረጋግጧል። የስኳር ህመምተኛ የሆነው ልዑል በዘመኑ በሽታ ሳይለከፍ አይቀርም የሚሉ የቅርብ ምንጮች ቀደም ሲል የተደረገለት ህክምና በቂ ለውጥ ሊያመጣለት ባለመቻሉ በአሁኑ ወቅት ታይላንድ ባንኮክ በህክምና ላይ እንደሚገኝ ማረጋገጥ ተችሏል።
በባንኮክ 7 ወሩ ሲሆን እስከአሁን 4ሚሊዮን 200ሺህ ብር ወጪ እንደተደረገለት ታውቋል። መንግስት አንድ የጠ/ፍ/ቤት ዳኛ እንኳ በአገር ውስጥ እንደማያሳክምና እንደማይረዳ እናውቃለን ያሉ የቅርብ ወገኖች ለሙሰኛውና ፍርደ ገምድሉ ልዑል ገ/ማርያም ይህን ያክል ወጪ መደረጉ አሳዛኝ ነው ብለዋል።
The post መንግስት የሕወሓት አባሉን ዳኛ ልኡል ገ/ማርያም በከፍተኛ ወጪ እያሳከመ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.