Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ስለዐባይ መገደብ ጉዳይ እኔም የምለው አለኝ ( ከቃል-ኪዳን ይበልጣል)

$
0
0

The Nile River has become a point of contention between Egypt and Ethiopia.

The Nile River has become a point of contention between Egypt and Ethiopia.


( ቃል-ኪዳን ይበልጣል)
ሰሞኑን ኢትዮጵያውያንን አነጋጋሪ ሆኖ ያለው የዐባይ መገደብ ጉዳይ ነው፡፡ አንዳንድ ወገኖች ሁኔታውን ከቀኝ ከግራ፣ከፊት ከኋላ ሳያዩ ከመለስ ዜናዊ ድንክዮች ባላነስ መንገድ መገደቡ ትክክልና ተገቢ እንደሆነ ሲጸፉና ሲናገሩ ይሰማል፡፡ ይህ ሊደንቀን አይገባም፡፡ የነዚህ ዓይነት ሰዎች አቋም አንድም ግድቡ ስለሚኖረው ኢኮኖሚያዊ፣ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊና በህላዊ ጉዳዮች ባይተዋሮች ናቸው፡፡ ሁለትም “እናቴን ያገባ ሁሉም አባቴ” ነው በሚል እሳቤ ወያኔን ኢትዮጵያዊ መንግሥት አድርገው የተቀበሉ ናቸው፡፡ ሦስትም የስደት ኑሮ ከብዷቸው ከወያኔ ጋር መግባቢያ መሰላል እየሠሩ ናቸው፡፡ ይህን ያልተገነዘቡና የወያኔን የቆረጣ የትግል ሥልት ያልተረዱ ወገኖች ለምን በዚህ ወቅትና ሰዓት የዐባይ መገደብ ጉዳይ አጀንዳ ሆኖ ቀረበ? ብለው ሳይጠይቁና ዕውነታውን ሳይረዱ፣ ዐባይ መገደቡን መደገፍ አለብን ይላሉ፡፡
በሀሳብና በአመለካከት ደረጃ ዐባይ መገደብ የለበትም የሚል ኢትዮጵያዊ ይኖራል ተብሎ አይገመትም፡፡ ጥያቄ የሚነሳው ዕውን ወያኔ ለኢትዮጵያ አንድነት፣ለሕዝቡ ሉዐላዊነት፣ብሔራዊ ጥቅምና ብልጽግና የቆመ ነው? ይህን ግንባታ ለመገንባት የተነሳሳው የኢትዮጵያን ሕዝብ በዐባይ ተጠቃሚ ለማድረግ አስቦ ነው? ወይስ ከኋላው ሌላ ምክንያቶች አሉ? የኢትጵዮጵያን የባሕር በር ፈቅዶ የሰጠ፣የኢትዮ-ኤርትራን ጦርነት ድል በአልጀርስ ስምምነት አሳልፎ የሰጠ፣የአገሪቱን ምዕራባዊ ዳርቻ 1600 ኪሎሜትር ርዝመት፣50 ኪሎ ሜትር ጥልቀት ለሱዳን አሳልፎ የሰጠ፣ከ7 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በላይ ለቱርክ፣ለሳውዲ ዐረቢያ፣ለቻይና፣ወዘተ ባለሀብቶች ለሄክታር በአንድ ዶላር ሂሳብ ለ99 ዓመታት የሸጠ፣የአገሪቱን ታሪክና አንድነት የካደ፣የመነጣጠያ ሕገ-መንግሥት ያዘጋጀ፣ባገሪቱ ካሉ ከፍተኛ ቁጥር ካላቸው ነገዶች መካል አንዱ የሆነውን የዐማራ ነገድ የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸመ አካል ዐባይን በመገደብ እንዴት ኢትዮጵያን ተጠቃሚ ያደርጋል ብሎ ማሰብና ማመን ይቻላል ? በአሁኑ ወቅት ወያኔ እየደረሰበት ያለውን የሕዝብ ተቃውሞ አቋም ለማብረድ የአቅጣጫ ማስለወጫ አጀንዳ አለመሆኑን በእርግጠኝነት እናውቃለን ወይ ? ወደ ውሳኔ ከመድረሳችን በፊት ለእነዚህ ጥያቄዎች ተገቢ መልስ ማግኘት ያለብን ይመስለኛል፡፡
በሁለተኛ ደረጃ ዐባይ ይገደብ አይገደብ ከሚለው መደምደሚያ ከመደረሱ በፊት ለሚከተሉት መሠረታዊ ጥያቄዎች አዎንታዊ መልሶች ማግኘት ያለብን ይመስለኛል፡፡ እነዚህም፡-
1. ኢትዮጵያ ተብላ ለዘመናት በዓለም ካርታ የምትታወቅ አገር ዛሬ በድሮ ወርድና ቁመቷ አለች?
2. የአንድን አገር ምላተ ሕዝብ ተሳትፎ የሚጠይቅን ተግባር ለማከናወን በቅድሚያ ከዕቅድ ዝግጅ እስከ አፈጻጸም ሕዝቡ መሳተፍ የለበትም ?
3. የሕዝቡን ቁሳዊና ኅሊናዊ ሀብት በሚፈለገው ደረጃ ለማግኘት ሕዝቡ የኔ የሚለው የመንግሥት አደረጃጀትና አመራር አለ ብሎ ያምናል?
4. ዐባይን ለመገደብ የታሰበው በዕውነት ለልማት ታስቦ ነው? ወይስ የሰሜን አፍሪካ ሕዝብ አመጽ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይሸጋገር የአመለካከት ለውጥ ለመፍጠር ነው?
5. ዐባይ ይገደብ ከተባለስ መገደብ ያለበት ቦታ የት ቢሆን ነው ለሕዝቡ ዕከል ተጠቃሚ፣ለግድቡ ደህንነት አስተማማኝ የሚሆነው?
6. ዐባይን ያህል ግዙፍ ግድብ ከመገደብ መካከለኛና ዝቅተኛ ግድቦችን መገደብ የበለጠ ውጤታማ መሆን አይቻልም ነበር ወይ?
7. የጣና በለስን ፕሮጀክት ዘርፎና አውድሞ ቤንሻንጉል ጉምዝ ላይ ከሱዳን ደንበር የቅርብ ርቀት ላይ ይህን ያህል ግዙፍ ግድብ ለመገደብ የታሰበው ዕውነት የኢትዮጵያን ሕዝብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሌሎች አማራጭ ቦታዎቸ ጠፍተው ነው ? ወይስ በግንባታው ሊጎዳ የተፈለገ አካባቢ አለ?
8. ከለጋሽ እና አበዳሪ መንግሥታና ድርጅቶች በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም ያገኘውን ብድርና ዕርታ በሙስና የወያኔ አባሎችን ተጠቃሚ ያደረገ አመራር መሆኑ እየታወቀ ለግድቡ ሥራ ከሕዝብ የሚሰበሰበው ገንዘብ ለተባለለት ዓላማ ስለመዋሉ ምን ዋስትና አለ?
9. የዐባይ ገባር ወንዞች በአመዛኙ ከጎጃም፣ከጎንደር፣ከሰሜን ሸዋ እና ከወሎ የሚነሱ ናቸው፡፡ ግድቡ እንዲሠራ የተፈለገው ከእነዚህ ክልሎች ብዙ እርቆ ነው፡፡ በግድቡ መሠራት ምክንያት እነዚህ የዐባይ ገባር ወንዞች ባለመብት የሆኑ አካባቢዎች በገባር ወንዞቹ ላይ የመጠቀም መብታቸውን አይከልልም ወይ?
ለእነዚህና መሰል ጥያቄዎች ተገቢ መልስ ሳንሰጥ፣ ዐባይ ይገደብ ወይም አይገደብ ብለን አቋም መያዝ ተገቢም ትክክልም አይመስለኝም፡፡ ለእነዚህ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ ሳንሰጥ በስሜት ዐባይ ይገደብ ብንል ሁለት መሠረታዊ ስሕተቶችን እንሠራለን፡፡ አንድ ለወያኔ ዕድሜ ማራዘሚያ እንሆናለን፡፡ ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ድጋፍ ትምህርት መቅሰም ያለብን ይመስለኛል፡፡ በወያኔ አመራር የኢትጵዮያ ብሔራዊ ጥቅምና የሕዝቡ መብት ይጠበቃል ብሎ ማሰብ ሸንበቆ ያፈራል ብሎ እንደማመን ይቆጠራል፡፡ ሁለት የተቃውሞው ጎራ ይከፋፍላል፡፡ በዚህም ተጠቃሚው ወያኔ ይሆናል፡፡
በሌላ በኩል የዐባይ መገደብ አለመገደብ የተቃዋሚው አጀንዳ ሊሆን አይገባም፡፡ የመገደቡም ሆነ ያለመገደቡ አጀንዳ የወያኔ ነው፡፡ ተቃዋሚው ድምፅ ሊሰጥ፣ሐሳብ ሊያቀርብ በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ መኖሩ እየታወቀ፣ በጠላት አጀንዳ ውስጥ ገብቶ የራሴ የሚለውን መጣል ተገቢም ትክክልም አይሆንም፡፡ ለምን በወያኔ አጀንዳ ራስችን እንጠምዳለን?
ተቃዋሚ ሲባል የመጀመሪያ ተግባሩ የሚቃወመው አካል የሚሠራቸውን አገርና ሕዝብ ጠቀም ያልሆኑ ተግባሮች በመረጃ ማጋለጥ ነው፡፡ የዐባይ መገደብ በተቃዋሚው አመለካከት ተገቢ ከሆነ የጀመረው አካል ይግፋበት፡፡ አንድ መንግሥት ነኝ ያለ አካል መሥራት የሚገባውን ሥራ መሥራቱ እንደ ልዩ ተአምር መታየት የለበትም፡፡ የተቃዋሚው ትኩረት መሆን ያለበት የሚሠሩ ሥራዎች በትክክል አገርና ሕዝብ ጠቀም መሆናቸውን በማረጋገጥ፣ጎጅ የሆኑትን ተግባሮች ማውገዝ ነው፡፡ ሲያቅድ ፣ሲጠነስስ ሕዝብ እንዲመክርበት ያላደረገ፣ሕይዎት የሚያስጠይቅ ጉዳይ ሲገጥመው ድረሱልኝ ሲል ፣ጥና ጠሪ መሆን ከተቃዋሚ የሚጠበቅ አይመስለኝም፡፡ መሆን ያለበት የሚቃወመው አካል ችግር ሲገባ፣ለችግሩ መውጫ አማራጭ ሐሳብ ይዞ ሕዝብ እንዲከተለው ማነሳሳት ነው፡፡
ቸር ይግጠመን!


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>