04.01.2014
ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/
ህማማት – ጸንሶ
ዕንባውን – አፍሶ
መስቀል ረገመ – በደም ተለውሶ
በበላሃሰቦች ኪዳኑ – ተረግጦ።
እህ! – እህህ –ህህህ —ህህህ – ህህህ
ሆይ! አለህን!? – አለህን በቤትህ? – አለህ!?!
እንሆ ——- ዘመን ተገርድሶ
ቀዬውን ተወርሶ – ጢሶ – ጢሶ ——
በትዕቢት – ተጥሶ፤
ፋሽስቱ – ቀስሶ
ዕምነት – ተቆራርሶ
ሽበት – ባት – ተውሶ፤
ቀኑም አለቀሰ – መስቀሉን – እያዬ
ዘመንም አነባ – ቁም ስቅሉን ስላዬ፤
መርገምትን – አምጦ – እግዚዖታን አዋዬ።
ከልቡ በቅላለች – በላይ እንደ ገና
ዘለቀች ተጣራች መንፈሰ – ገናና
…. ንጥር – ዬአውራ -
አዳር – ለባንዴራ።
የታሪክ ማህደር – በደም የተቃኘች
ሰንደቁ ናትና ደምቃ – የታተመች።
አጠናት ከልቡ – የኪዳን ህይወቱን
ይሞቃል ጠረኑ – ድፈረትም ያባቱ፤
የጥንት —– የጥዋቱ
የእናት ሀገር ሃብቱ።
ትናንትን አዳምጦ – በቃኝን አስጊጦ
ነፃነት …. አምጦ – አምጦ – አምጦ -
ዓርነት …… ተጠምቶ – ተጠምቶ – ተጠምቶ -
ተማግዶ – ተማግዶ – ተማግዶ -
ካለ‘ ርህራሄ ተወጋ ——- በዘንዶ፤
ለባዕቱ – ደምቶ – እራሱን ሰጥቶ
ብሩህ ቀን ሰንቆ – ሰላምን ተመኝቶ
እናቱን አላቀ ትውልድ – ታሪክ ሠርቶ።
ሥጦታ – ለቅድስት እናት ለእሙሃይ ይሁንልኝ።
‘ ይህቺ ምልክት አንድ ፊደል „እ“ መዋጧን ታመለክታለች። ከትህትና ጋር፤
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።