Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Sport: ባርሴሎና ለሁለት ዓመታት ከተጫዋች ግዥ ታግዷል

$
0
0

የባርሴሎና ፕሬዚዳንት ጆሴፕ ማሪያ በፊፋና ዓለም አቀፉ የስፖርት ፍርድ ቤት ውሳኔ መበሳጨታቸውን በክለቡ ድረገፅ ላይ አስታውቀዋል፣

ዳግም ከበደ

ባርሴሎና የዓለም አቀፉን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ህግ ጥሷል በሚል የተጫዋች ዝውውር እንዳይፈፅም ለሁለት ዓመታት የተጣለበትን ማዕቀብ ወደ ዓለም አቀፉ የስፖርት ፍርድ ቤት በማቅረብ ይግባኝ ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ አድርጎ የፊፋ ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን አዟል። ባርሴሎና ከ18 ዓመት በታች ተጫዋቾችን አስፈርሟል በሚል በሁለት የዝውውር መስኮቶች ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ እንዳያስፈርም እገዳ ተጥሎበታል።
suarze barcelona
የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር ፊፋን ውሳኔ ባለመቀበል ይግባኝ ያለው ባርሴሎና አሁንም ውሳኔው እንዲጸና በፍርድ ቤቱ ተወስኗል።ፍርድ ቤቱ ይግባኙን ውድቅ በማድረጉ ቡድኑ እስከ ጎርጎሮሳውያኑ ጥር 2016 ድረስ እገዳው ይጸናበታል። ባርሴሎና ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ተጫዋቾችን አስፈርሟል በሚል ለሁለት ዓመታት ተጫዋቾችን እንዳያስፈርም ከመደረጉም በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ተወስኖበታል።
ዓለም አቀፉ የስፖርት ገላጋይ ፍርድ ቤት የወሰነውን ውሳኔ ተከትሎ የባርሴሎና ፕሬዚዳንት ጆሴፕ ማሪያ ባርቱሙ በክለባቸው ላይ የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ክለብ ፊፋ ለሁለት ዓመታት ተጫዋቾች ግዥ እንዳይፈፅም ማገዱን ተከትሎ ትልቅ የፍትህ በደል ተፈፅሞብናል ሲሉ በክለባቸው ድረ ገፅ ላይ ገልፀዋል።
ባርሴሎና ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት ልጆችን ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ተገቢ ባልሆነ መልኩ በማስፈረሙ ስህተት ፈፅሟል በሚል በፊፋ መወንጀሉ ስሀተት መሆኑንና የተላለፈው ውሳኔም ተገቢ አለመሆኑን ነው ፕሬዚዳንቱ የተናገሩት። ባርሴሎና የላማሲያን አካዳሚ በመባል የሚታወቅ ወጣት ተጫዋቾችን ስልጠና በመስጠትና ወደዋናው ክለብ በማዘዋወር እንደሚጠቀም ይታወቃል። በላማሲያ አካዳሚ ሊዮኔል ሜሲ እና አንድሬ ኢኒየስታን የመሳሰሉ በእግር ኳሱ ውስጥ ተፅእኖ መፍጠር የቻሉ ተጫዋቾችን አፍርቷል።
ክለቡ የተጫዋቾች ግዥ ላይ እንዳይሳተፍ ከታገደ በኋላ ለአውሮፓ ከፍተኛው የእግር ኳስ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቢልም ቅሬታው በድጋሚ ውድቅ መሆኑ የክለቡ አመራሮችን አበሳጭቷል። በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ክፉኛ የተበሳጩት የክለቡ ፕሬዚዳንት በክለቡ ድረ ገፅ ላይ የተወሰነውን ውሳኔ አብጠልጥለውታል። « ዛሬ ፍትህ ተነፍገናል። ትልቅ ፍትሃዊነት የጎደለው ውሳኔ ዛሬ በክለባችን ላይ ተወስኗል ፣ ውሳኔው ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ህፃናትና ቤተሰቦቻቸው፣የክለቡ አባላት፣እንዲሁም መላው እግር ኳስ አፍቃሪ ላይ የተፈፀመ በደል ነው» በማለት ምሬታቸውን በክለባቸው ድረ ገፅ ላይ አስፍረዋል።
አሁን ያለው የተጫዋቾች ስብስብ ክለቡን በእግር ኳስ ደረጃቸው ከፍተኛ ከሚባሉ ክለቦች ተርታ የሚያስመድበው ቢሆንም ውሳኔው ባርሴሎና ላይ ተፅእኖ ይፈጥርበታል። ወደፊት ሊያጋጥም በሚችል የተጫዋቾች ጉዳት ወይም የአቋም መውረድ ክለቡ የተጫዋቾች ግዥ ላይ ለመሳተፍ የሚገደድባቸው ሁኔታዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ። በላሊጋው ላይ ያለው የበላይነትና ተፎካካሪነትንም እንዲያሽቆለቁል ሊያደርገው ይችላል።
በፍርድ ቤቱ ውሳኔ የተበሳጩት የክለቡ ፕሬዚዳንት ጆሴፕ ማሪያ በተደጋጋሚ ፊፋ ፍትሃዊነት የጎደላቸው ውሳኔዎችን እንደሚወስን ነው የሚናገሩት።« በተደጋጋሚ ፊፋ የሚወስናቸው ውሳኔዎች ተገቢነት የሌላቸውና የተጋነኑ መሆናቸውን ለማስረዳት ሞክረናል። ሆኖም ግን እራሱ ፊፋና ፕሬዚዳንቱ ህጉን በድጋሚ ቢያጤኑትና እግርኳሱን ከሚረብሽ ድርጊት ቢቆጠቡ ለእግር ኳሱ ወዳጆች መልካም ነው» በማለት በተጫዋቾች ዝውውር ላይ ያለውን ህግ በድጋሚ ማየት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>