Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

 የግቢዬ ዛፎች –ከተማ ዋቅጅራ

$
0
0

አንድ በእድሜ ባለጸጋ የሆኑ አባት በግቢያቸው 14ት አይነት ዛፍ እየተንከባከቡ ያሳድጉ ነበረ። እነዚህ ዛፎችን አባዝተው ግቢያቸውን ሞልተውታል። የግቢያቸው ስፋት የዛፎቹ ልምላሜና የከለር ድምቀት ላየ ልብን ይማርካሉ። ህይወት ማለት እጽዋት እጽዋት ማለት ህይወት እንድሆነ በግቢው ያሉት ዛፎች ይናገራሉ። የዛፎቹ ልምላሜ ንጹ አየር የሚተነፍሱበት ከፀሐይ የሚጠለሉበት ከፍሬአቸው ምግብ የሚመገቡበት ባጠቃላይ ህይወታቸው ናቸው። በማለዳ  ጠዋት ተነስተው ከዘራቸውን  ይዘው ግቢውን ቃኘት ቃኘት እያደረጉ የደረቁ ቅጠሎችን በከዘራቸው እያራገፉ መሬት የወደቁትን እየሰበሰቡ ግቢያቸውን ከቃኑ በኃላ ነው ወደ ጉዳያቸው የሚሄዱት።

ለመሆኑ አልኳቸው አሁን ግቢዎትን እንደዚ የሞሉት 14ት የዛፍ ፍሬዎት ናቸው ? አልኳቸው።

አዎ አሉኝ ልባቸውን ሞልተው …ወዲያው ግን ክፍት ብሎአቸው ከ14ቱ አንዷ  በለሊት የመጣ ሽፍታ ቆረጣት በእጃቸው እያመለከቱኝ ያችትልህ ስር አላት ግንድና  ፍሬዎቻ ግን የሉም። የቀሩት 13ት ነበሩ በግቢየ የገባው ሽፍታ 9ኝ አስቀርቶ 4ቱን አጠፋው። ይሁን 9ኙ ዋና ዋና ናቸው ብዬም ዝም ብለው የ9ኙን ዛፍ ያለኔ ፈቃድ ማንም እንዳይነካ ፍሬአቸውንም ያለኔ ፈቃድ ማንም እንዳይመገብ ብሎ የሽፍታ ህግ አውጥቶ  ግቢዬን  በመሳሪያ  አጠረው። ግቢዬም በሽፍታ ተወረረ ፍሬዎችንም ያለግዜው ሳይደረሱ በላቸው የዛፎቼን ውበት አጠፋቸው በፊት እንደ ልቤ ተዘዋውሬ የምንከባከባቸው እንደልቤ ከፍሬአቸው የምመገብባቸው በፍቅር የማያቸው ተክሎቼን ድንበር አበጅቶላቸው እንዳልጎበኛቸው አጠራቸው። ድንበሩም ባልከፋ ግን ሽፍታን ማን ያምናል? የሽፍታ  በኅሪ ያው ሽፍታነት ነው ዘረፎ መብላት ገድሎ መኖር። ለዛፎቹ 1,2,3,4,5,6,7,8,9 ቁጥር ሰጣቸው አንድ ላይ አንድ ይኑር ሁለት ለይ ሁለት ይኑር እያለ ለዘጠኙም ተናገረ። የአንድን ሁለት እስከ ዘጠኝ ያሉት እንዲነኩ አይፈቀድላቸውም የሁለትንም እንደዚሁ እያለ እስከ ዘጠኝ ይቀጥላል ለምን ሲባል ሁሉም በራሱ  እንዲኖር ነው ይላል። አንድ ለአንድ ሁለትም ለሁለት ሶስት ለሶስት አራትም ለአራት እያለ ዘጠኙም ስለራሳቸው የመብት ጥያቄ ሲያነሱ ሽፍታነቱ ይመጣና ብረቱን አንስቶ መፍጀት ይጀምራል ምን አገባችሁ ከ1-9 ያሉት የዛፎቹ ባለቤት እኔ ነኝ በኔ ስር እስካላችሁ ድረስ ከኔ ሃሳብ ውጪ ማሰብም መጠየቅም አትችሉም ሃሳባችሁን በኔ ሃሳብ ልክ ስፉት እያለ  ሽፍታነቱን ያሳያል። አንድ በሁለት ለይ ሁለት በሶስት ላይ ሶስት በአራት ለይ ሲነሱ ግን ቁጭ ብሎ  ይስቃል የእርስ በራስ ፍጭቱ ሽፍታው የሚኖርበትን ዘመን ስለሚያራዝመው እንደዚህ አይነቱን ግጭት ይናፍቀዋል የናፈቀው ነገር አልሰራ  አለው እንጂ። ዛሬ 9 ያደረጋቸውን ነገ 19 ሊያደረጋቸው ይችላላ 9ኙ በ9ኝነታቸው እንዲቆዩ አልያም ወደሚፈልጉት ኃሳብ መድረስ እንዲችሉ ሽፍታን ከስሩ ነቅሎ ዳግም እንዳይመጣ ማድረግ ያስፈልጋል። ሽፍታ  በራሱ ህግ በየግዜው አንድ ነገር ብልጭ ስትል ለብልጭታ አዲስ ህግ እያወጣ ግቢውን አመሰው ወይ ግቢውን መምራት አልቻለ ወይ ፍሬውን በአግባቡ መመገብ አልቻለ ብቻ ዘይት እና  ውሃን ለመቀላቀል ይሞክራል  ደግሞም ይላል በኔ ዘመን(በሽፍታው ዘመን) ዘይት እና  ውሃ ሲቀላቀል ታያላችሁ በግቢው ለሚኖረው ነዋሪ በሙሉ የኔን ቃል የመቀበል ግዴታ አለበት የማይቀበል ቢኖር ግን ዘይት እና  ውያ መቀላቀላቸውን ሳያይ ይወገዳል። የሚል የሽፍታ ህግ አጽንቶ ግቢውን አምሶታል። እኔም መልእክቴን ላስተላልፍና  ወደ ተከለለው ግቢዬ ልግባ። በግቢ ውስጥ አንቱ የተባሉ የተከበሩ ሽማግሌዎች አሉ። እግዚአብሔርን ሲያመልኩ በእድሜ የሸመገሉ፣ አላህን ሲያመልኩ በእድሜ የሸመገሉ፣ ዋቄፈናን ሲያመልኩ በእድሜ የሸመገሉ እናንተ በእውቀት የበሰላችሁ ብዙ ፍሬ  ያፈራችሁ አባቶች ስለ  ግቢያችሁ የምታስቡ ስለ ዛፎቻችሁ የምትጨነቁ ስለ ፍሬዎቻችሁ የምትጓጉ አባቶች ስለ  ግቢያችሁ አስቡ ስለ ዛፎቻችሁ አስቡ ስለ  ፍሬዎቻችሁ አስቡ። ግቢ የተባለችው አገር ናት። ስትደሰቱ የምትደሰቱባት ስታዝኑ የምታዝኑባት አርሳችሁ የምታበቅሉባት ነግዳችሁ የምታተረፉባት ተምራችሁ የምታስተምሩባት ደምቃችሁ የምትታዩባት ከደምና ከአጥንታችሁ የተሳሰረች ይህቺ ናት አገርህ።  ዛፎች የተባሉት 9ኙ ክልሎች ናቸው። በእድሜ ከፍ ከፍ የምትሉበት ከራሳቸው ሽበት ከአእምሮአቸውም በሳል እውቀት ከአንደበታቸውም ጠጋኝ ቃላት የሚናገሩባት የሚኖሩበት። አባት.. አባት እናት.. እናት ብለን የምንጠራቸው መኖሪያ፣ ቄዬ.. ቄዬ አድባር.. አድባር የምልበት፣ ሰፈር.. ሰፈር መንደር.. መንደር የምንልበት፣ ጎሳ ..ጎሳ ብሔር.. ብሔር የምንልበት፣ እሷ ናት ክልልህ። ፍሬ የተባሉት ደግሞ ሮጠው ያልጠገቡ፣ ቁልቁለት ዳገቱን ሜዳው ላይ የሚቧርቁ፣ ነገ አባት እናት የሚሆኑ፣ ነገ የሰፈር መሪ፣ የመንደር መሪ፣ የጎሳ መሪ፣ የክልል መሪ፣ የአገር መሪ የሚሆኑ፣ ነገ  ጳጳስ፣ ሼህ፣ አባ ገዳ፣ የሚሆኑ እነሱ ናቸው ፍሬዎች።

ሽፍታ  ግቢህን ወሮታልና የፈለከውን ላማድረግ የፈለከውንም ለመስራት አትችልም። ምክንያቱም የሽፍታ  ባህሪ ከራሱ ውጪ የሚሰማው ነገር ስለሌለ። ትላንትና 14 ዛፍ የነበርክ የአገሬ ዛፍ ሆይ ዛሬ 9ኝ ሆነኻል ይህ ጥሩ ባልከፋ ነገር ግን ሽፍታ  ነግሶ ባለበት ግቢ ውስጥ ነገ ምን እንደሚልና ምን እንደሚሰራ አይታወቅም እና የግቢ ነዋሪዎች ግቢ ማለት አገር እንደሆነ ጠቅሻለው የማን ግቤ ያልተደፈረ የማን ፍሬ ሳይደርስ ካለግዜው ያልተቀጠፈ የማን ዛፍ ያልተለመለመ የለም ከአንድ እስከ ዘጠኝ ብንሄድ ዘጠኙም ዛፍች  ሃዘን ላይ ናቸው። እህህ…. የማይል የለም። ሽፍታ እስካለ ሃዘን ለቅሶ ችግር ስደት ድህነት ፍቅር ማጣት የደስታ ህይወት ባጠቃላይ ሰላም በግቢህ ውስጥ አይኖርም። ደስታ ሰላም ፍቅር ነጻነት እድገት የምንፈልግ ከሆነ ሽፍታን መጣልና  ማጥፋት አለብን። ሽፍታ  የሚጠፋው በልመና ሳይሆን በሽፍታነት ነው። ሽፍታ  የሚፈራው ሽፍታን ብቻ ነው። እናንተ  ዘጠኙ ዛፎች የናንተ  ሽፍታነት ሽፍታን እስከሚጠፋ  ብቻ  ነው እንጂ ነገ ሽፍታው ከጠፋ  በኃላ እናንተም ሌላ ሽፍታ  እዳትሆኑ አጥብቄ እነግራችኃለው።

 

በዚህ አባባል መልእክቴን ልጨርስ <<<የማትረባ  ፍየል ዘጠኝ ትወልድና

እርሷም ትሞታለች ልጆቿም ያልቁና>>>

እንዳይሆንብን ስለ አገርህ ስትል፣ ስለ አባት እናትህ ስትል፣ ስለ ባል ሚስት ስትል፣ ስለ ልጆችህ ስትል፣ ሽፍታውን በማስወገድ ከፊታችን የተጋረጠውን ጨለማ ገፈን ሰላም የነገሰበት አገር እንመስርት።

 

rtከ-ከተማ ዋቅጅራ 31.12.2014

Email-waqjirak@yahoo.com


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>