Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ህዝብ ያለው ድምጽ ነው፤ ግን ይህን ድምጽ የሚሰበስበው ማን ነው?

$
0
0

ዊት ሰለሞን

በአዲስ አበባ በታላቁ ኑር መስጊድ ለመቶ ምናምን ግዜኛ ጨዋው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ድምጹን አሰምቷል፡፡የታሰሩት ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ፣መጅሊሱ ከመንግስት ተጽእኖ እንዲላቀቅ ወዘተ ጠይቀዋል፡፡ተቃውሞው ከተጀመረ ሶስተኛ ዓመቱን ይዟል፡፡

bbnደርግ አሸንፎ በመምጣቱ ምንም ነገር እንደማያቅተው የሚያምነው ኢህአዴግ አሁንም በጫካው ህግ የሚመራ በመሆኑ ለህዝቡ ጩህት በራሱ መዝገበ ቃላት ተገቢ ነው ያለውን ምላሽ ሰጥቷል፡፡ከፍተኛ ዝና እና ተቀባይነት የነበራቸውን ሰላም ፈላጊ ተደራዳሪዎች በአንድ ምሽት ለቃቅሞ በማሰር
‹‹ሽብርተኛ››ብሏቸዋል፡፡ርህራሄ አልባ በሆኑ ታጣቂዎች ደም እንደ ጅረት ፈሷል ኢህአዴግ ላለፉት ሶስት ዓመታት የሰጠው ምላሽ ሀይል የተቀላቀለበት ነበር፡፡ህዙ ግን ድምጹን ከማሰማት አላመነታም፡፡
በእኔ እምነት ‹‹መንግስት የለም ወይ››በማለት ህዝብ ጥያቄ ሲያቀርብ ኢህአዴግ አለሁ ያለው በመግደል፣በማሰርና በማሰቃየት ብቻ ነው፡፡ኢህአዴግ ከዚህ የዘለለ ምላሽ ለመስጠት ጠረጴዛ ስቦ የሚቀመጥበት ወኔ ወይም አፈጣጠር የለውም፡፡

ዛሬ በኑር መስጊድ ከጁምዓ በኋላ ድምጻቸውን ያሰሙ አማንያን ትንፋሻቸውን ሞልተው ባሎኑን ወደ ሰማይ ለቀውታል፡፡ ይህ በኢህአዴግ ጆሮ ሊደርስ ያልቻለ ድምጽ በአገሪቱ በሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጆሮ የሚደርስበት ወሳኝ ወቅት ላይ የደረሰ ይመስለኛል፡፡ከዚህ ቀደም አንድነትና ሰማያዊ ባደረጓቸው የተቃውሞ ሰልፎች ባወጧቸው መግለጫዎች መንግሰት የወሰዳቸውን እርምጃዎች ኮንነዋል ፡፡ታሳሪዎቹንም የእምነት ጀግኖች በማድረግ አሞካሽተዋል፡፡

ምርጫ በኢትዮጵያ መንግስት የሚቀየርበት መንገድ ለመሆን እስካሁን ባይታደልም ተቃዋሚዎች ይህንን ድምጽ በመሰብሰብ የሙስሊም ኢትዮጵያዊያኑን ጥያቄ እንዴት እንደሚመለከቱትና በለስ ቢቀናቸው ምን እንደሚያደርጉ በግልጽ በማስቀመጥ ይህንን ሀይል የለውጥ አካል በማድረግ ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ይሰማኛል፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>