Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ድምፃዊ ፋሲል ደሞዝ በአሜሪካ በዱርዬዎች የደረሰበት ዝርፊያ እና ድብደባ ለክፉ የሚሰጥ እንዳልሆነ ተገለጸ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በዋሽንግተን ዲሲ የገና ገበያ ቆይቶ እየወጣ ነበር:: አካባቢው ዱርዬዎች ወይም በአሜሪካ አጠራር ጋንግ የሚሰባሰቡበት ነበር:: በቅርቡ እንቆቅልሽ የሚለውን አልበም አውጥቶ; እንዲሁም ባለፈው ቅዳሜ በሚኒሶታ የተሳካ ኮንሰርቱን አቅርቦ የተለመለሰው ይኸው ድምፃዊ ፋሲል ደሞዝ ከሱቁ እንደወጣ አይፎን ስልኩን በጆሮው አድርጎ አማርኛ እያወራ በዱርዬዎቹ አጠገብ ሲያልፍ ቋንቋው የውጭ መሆኑን የተረዱት እነዚሁ ዱርዬዎች ለማጥቃት ብርታት ሆናቸው::
fasil demoz
ስልኩን ከጆሮው ላይ የቀሙት እነዚሁ ሶስት ዱርዬዎች ፋሲልን ቡጢና አንዳንድ የሰውነቱ ክፍል ላይ ከመቱት በኋላ ኪሱ ውስጥ በመግባት ከ120 ዶላር የማይበልጥ ገንዘብ ወሰዱበት:: ፋሲል ከድብደባው በኋላ ወደ ቤቱ ያመራ ሲሆን ለፖሊስም ሪፖርት አድርጓል::

ድምፃዊው የደረሰበት ጥቃት ከቀጣይ ኮንሰርቶቹ የማያስተጓጉሉት ከመሆኑም በላይ የደረሰበት ጥቃትም ለክፉ የሚሰጥ አይደለም:: ሆኖም ግን ዱርዬዎቹ አይፎን ስልኩን እና ከ120 ዶላር የማይበልጥ ገንዘቡን ወስደውበታል::


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>