Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ተስፋዬ ገ/አብ ገዳ              ከሰመረ አለሙ      

$
0
0

 

ተስፋዬ ገ/አብ ለኤርትራ ነጻነት ታግሎ አገሬ የሚለዉን አገር ነጻ ከወጣ በሗላ በየጊዜዉ ኢትዮጵያን ሰፈር የሚያደርገዉን ቅሌት አስመለክተዉ ብዙዎች ዘግበዉታል በተለይም የተከበሩ የኢትዮጵያ ልጂ ኢንጂነር ዘዉገ አስፋዉ ተስፋዬ ስለሰዬ የማላዉቀዉ የለም ብሎ ሲቀባጥር በምሁር ብእራቸዉ ቢያበራዩትም ግለሰቡ ለእዉቀት ያልታደለ በመሆኑ አሁንም ኢትዮጵዉያን ሰፈር መተናኮሱን አላቆመም። ኤርትራ ዛሬ ምድር ላይ ያለ ችግር ተጠራቅሞ እሷ ላይ እንዳላረፈ ሁሉ ተስፋዬ ግን ለዉጊያ የመረጠዉ ሀገር ይችኑ ኢትዮጵያችንን ነዉ።

Tesfaye Gebreabተስፋዬ ገ/አብ በወጣትነት ዘመኑ በዘመኑ ሀገሪቱ ዉስጥ እንዳሉት ወጣቶች ተምሮ ወይ ተቀጥሮ ሊሰራ ባለመቻሉ በችሎታ ማነሰ ምክንያት ማለቴ ነዉ በወቅቱ በገፍ ልዩ ችሎታ ሳይጠይቅ ሁሉንም ያስተናግድ በነበረዉ በዉትድርና ዘርፍ ዉስጥ ተቀጥሮ ደርግን ሲያገልግል የቆየ ነበር። ችግሩ ዉትድርናዉንም በሀሞተ ቆራጥነት ሊወጣዉ ባለመቻሉ አንዴ በካድሬነት አንዴ በግጥም አንባቢነት የወቅቱን ጌቶቹን ሲያገለግል ቆይቶ የደርግ ዉድቀት አይቀሬ በመሆኑ ዘር አቋጥሮ ወደ ጠላት ጎራ ተቀላቅሎ ለመቀላቀሉ ግን የራሱን የሆን አንካሳ ምከንያት እየሰጠ በየጊዜዉ በመገለባበጥ የሚኖር ኤርትራዊ ነዉ።

ተስፋዬ ገ/አብ ህዋአትን ከተቀላቀለ በሗላ ነብስና ስጋዬ ከህዋአት የተሰራ ነዉ በማለት ከዋናዉ መስራቾቹ በላይ ፊታዉራሪ ሲሆን ገድላቸዉን ሲጽፍም እነሱ በህልም ያልታያቸዉን ገድል እና ጀብድ ቀጥሎ ቀጣጥሎ ጌቶቹን በሚገባ ያስደሰተ ካድሬ ሲሆን ለዚህም ስራዉ ለሱ የማይገባዉን ቦታ በአቶ በረከት እና በአቶ መለስ አማካይነት ተችሮት ያንን የመሰለ ትልቅ ተቋም ምን ያህል እንዳራከሰዉ ከራሱ ከጋዜጠኛዉ ማስታወሻ ኑዛዜዉና አልፎ አልፎ ከሚሰጠዉ ቃለ ምልልስ መገንዘብ ይቻላል። ተስፋዬ ገ/አብ ጠላቶቼ  የሚላቸዉ እነሱ የማያዉቁት እሱ ግን ያቄመባቸዉን በዘመነ ሹመቱ ቁም ስቅል አሳየ፤ቀጣ፤ሞራል ጣለ፤ ከስራ አባረረ ሌላም ሌላም።

በወቅቱ የዚህ ሰዉ ጣራ መንካት መጨረሻዉ ያልተመቻቸዉ ካቅሙ እና ችሎታዉ በላይ የተሸከመዉ ስልጣን ለእሱ የሚመጥን ባለመሆኑ ነገሩን ሁሉ  የልጂ ጨዋታ አደረገዉ መላ ይበጂለት በማለት ረጋ ሊያደርጉት ሲሞክሩ፤ የተለቀቀለት ጥቅማ ጥቅምም ልጓም ሲበጅለት፤ ኤርትራ ጋርም ያለዉ ንክኪ ሲደረስበት እጁ በካቴና ከመግባቱ በፊት ከእሱ ጋር በተለያየ ነገር ትስስር ያላቸዉ ግለሰቦች ነብሰህን አድን ጥቆማ በማድረጋቸዉ ወደ ባህር ማዶ ከእፍኝ ብር ጋር ተሰዶ እስከ ለከፈዉ ልክፍት ጋር አብሮ ይኖራል። እንደዉም አንዳንዶቹ የሻቢያ ሰላይ ነዉ ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ የወያኔ ሰላይ ነዉ የሚሉም አሉ።

ተስፋዬ እንደማንኛዉም ስደተኛ እራሱን እንደማኖር የለከፈዉ ልክፍት አለቅ ብሎት አንዴ ኢትዮጵያዊ አንዴ ወያኒያዊ አንዴ ኤርትራዊ አሁን አሁን ደግሞ ኦሮማዊ ቀጥሎ ደግሞ ምስራቅ አፍሪካዉ ሊሆን ተዘጋጂቷል። ከጂምሩ የዚህ ግለሰብ መላ ማጣት ቀደም ብሎ የተገለጠላቸዉ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ “ተስፋዬ ምነዉ ከኦሮሞ በላይ ኦሮሞ ሆነ መላዉን አጣ” ብለዉ የተናገሩት ለጊዜዉ የሚያስቅ ቢመስልም እሳቸዉ ግን ከንግግራቸዉ ጀርባ ብዙ ነገር በመታዘብ የወረወሩት አስተያየት በመሆኑ በጊዜዉ ሳይሰተዋል እዚህ ላይ ተደርሷል። ተስፋዬ ገ/አብም በዚህ ቂም ይዞ ደጂ በሚጠናበት በኦሮሞ ስብስባ ሁሉ እሳቸዉንና አቶ ቡልቻ ደመቅሳን ከተቀረዉ ኦሮሞ ለማለያየት ሳያጣጥል ያለፈበት ጊዜ የለም።

ብቻ አሁን አሁን ሚዛኑ ቀንሶ የኢትዮጵያ የድር ገጾችም የተስፋዬን ጽሁፍ ወደ ቅርጫት በመጣል ትምህርት እዉቀት ልምድ ያላቸዉ ኢትዮጵያንን በማስተናገድ ላይ በመሆናቸዉ የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ሳያመስግን አያልፍም ። ለወደፊትም አምዳቸዉ ላይ የሚያወጡት ጽሁፎች ሁሉ ኢትዮጵያዊ መስፈርትን የጠበቁ ይሆናሉ የሚል እምነትም ይኖረናል።  እዚህ ላይ የኢትዮጵያ መጽሀፍ አሳታሚዎች ትርፍን ባማከለ መልኩ ብቻ ጸረ ኢትዮጵያ ጽሁፍ ባታስተናግዱ መልካም መሆኑን እየጠቆምን ነገር ግን ከትርፍ በላይ ሀገር የለም በሚል እምነት የተስፋዬን እና መሰሉን  መጽሀፎች ብታሳትሙ በሀገር ፍቅር ስሜት ልባቸዉ የነደደ ዜጎች በድር ገጹ አማካይነት የራሳቸዉን እርምጃ ስለሚወስዱ ትርፋችሁን ቀርቶ ዋናዉን ከማጣታችሁም በላይ በሀገር ክህደት መዝገብ ዉስጥ እንደምትቀመጡ ከወዲሁ ማስገንዘብ እንወዳለን። ቀደም ሲል የደረሰዉ ችግርም ሊደርስባችሁ ስለሚችል ጥንቃቄ ማደረጉ ተገቢ ነዉ እላለሁ። ተስፋዬና መሰሎቹ ታሪክ የሚያጠፋበት ዜጋ የሚያጠባብጡበት መሳሪያዎች እናንተ ከሆናችሁ ታሪክ ይቅርታ እንደማያደርግላችሁ በአጽንኦት ልናስገነዘብ እንወዳለን።

ብዙ ጊዜ ደጋግሞ እንደሚናገረዉ አድአ ተወልጄ አድአ አደኩ የሚለዉ ተስፋዬ ገ/አብ ኦሮሞዎች ከገበያ ሲመጡ ለእናቴ ቅቤ ይሰጡ ነበር ይላል እናቴም ቡና አፍልታ ትጠብቃቸዉ ነበር ይለናል ተስፋዬ (ገዳ)። ማንኛችንም እንደምናዉቀዉ ኤርትራዉያን ኢትዮጵያ ዉስጥ የተሳተፉባቸዉ የመተዳደሪያ ዘርፎች ወይ ሜካኒክ ወይ ንግድ ወይ ዳቦ መጋገሪያ የመሳሰዉ ሁኔታ ሁኖ ሳለ የጣሊያን ስልጣኔ የተጣበቀባቸዉ የተስፋዬ እናት ከኦሮሞ ጋር ያን ያህል የጠበቀ ግንኙነት እንዴት ሊኖራቸዉ ቻሉ? ምናልባት ተስፋዬ አሁን ለሚያከናዉነዉ የኦሮሞ እና አማራን ማጋጨት ስራ መሰረቱን የጣሉት እናቱ ሊሆኑ ይችላሉ ብንል ከምክንያት አንጻር ብዙም የሚያሳማን አይመስለኝም። ምክንያቱም ደብረ ዘይት ከመላዉ ኢትዮጵያ ካሁኗ ኤርትራ ጨምሮ ተደባልቀዉ የሚኖሩባት አገር ሁና እሳቸዉ ግን ከኦሮሞዎች ጋር ብቻ ግንኙነት በመፍጠራቸዉ ነዉ (የመረጃ ምንጭ እራሱ ተስፋዬ ገ/አብ)። እንግዲህ ይህ ሁኔታ በጥልቀት ሲታይ ተስፋዬም የሳቸዉ የስጋ የመንፈስ እና የእምነት ተቀጣይ በመሆ

ኦሮሞና አማራዉን የማፋጀት ኤርትራዊና ወያኔያዊ  ተልእኮዉ የተጠነሰሰዉ በናቱ መምህርነት ሊሆን ይችላል ማለት ነዉ።  በስራቸዉና በኑሯቸዉ ሰልጥነናል በሚል አባዜያቸዉ  ምክንያት ኤርትራዉያን ከኦሮሞች ሲርቁ የተስፋዬ እናት ግን ተስፋዬ እንዳለዉ እንዲህ ያለ መጣበቅ የደረጉበት ምክንያቱ ከዚህ ዉጭ ሊሆን አይገባም።

 

የእናቱን ጉዳይ ስላነሳ ከምክንያት አንጻር ተወያየንበት እንጂ አስፈላጊነቱ እምብዛም አልነበረም። የአባቱ ጉዳይማ በፍጹም ተነስቶ አያዉቅም ከናት ብቻ እንደ ተፈጠረ ሁሉ። እዚህ ላይ ጸሀፊዉ ተስፋዬ ማንኛዉንም የኢትዮጵያ አይኮኖችን( በእድሜ ከአባትነት አልፈዉ አያቱ የሚሆኑትን እንደ ጽሁፉ ባልተገታዉ አንደበቱ አንተ ወይም አንች እየለ ማብጠልጠሉን ያልታዘበ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም እኔ ግን የተስፋዬ እናቴ ተስፋዬን የመሰለ ለስብእና ጠንቅ የሆነ ፍጥረት በተፈጥሮ አስገዳጂነት ቢፈጥሩብንም በኢትዮጵያዊነቴ የሚገባኝን ኢትዮጵያዊ ክብር በአንቱታ መስጠቴ እንዲታወቅልኝ እፈልጋለሁ ልጃቸዉም ለወደፊቱ ከዚህ ትምህርት ያገኛል የሚል ተስፋ ይኖረኛል። መብቱ የእሱ ነዉ ያደቆነ ሰይጣን ግን ሳያቀስ አይገልም የሚባል አባባል አለ።

በሌላዉ ከተስፋዬ ጽሁፍ እና አንደበት ተደጋግሞ እንደተሰማዉ  እናትየዉ በኦሮሞ ቋንቋ እጂግ የተካኑ ከመሆናቸዉም በላይ ተረትና ምሳሌያቸዉም በኦሮምኛ መሆኑን አልፎ አልፎ ሁኔታና አካባቢዉን እያየ ይናገራል። ይህን አባባልም በመሳብ የልጅነት ጊዜዉን ደብረ ዘይት ዉስጥ ከኦሮሞ ልጆች ብቻ እየተጫወተ እንዳደገ እንደ ሰመመን ትላንት እንደሆነ ሁሉ በትዝታ ለኦሮሞ ተሰብሳቢዎች እምባ እየተናነቀዉ ያወራዋል። ዉድ አንባቢ ሆይ እናቱ ኦሮምኛ ተናጋሪ ከሆኑ በልጂነቱ ዉሎዉ ጨዋታዉ ትምህርቱ እድገቱ ከኦሮሞ ልጆች ጋር ብቻ ከሆነ ይህ ሰዉ አማርኛ ተናጋሪዉን እነዲገድልላቸዉ ሌት ተቀን ለሚሰብክላቸዉ ለኦሮሞ ተወላጆች መልእክቱን ለማስተላለፍ የመረጠዉ ቋንቋ እንዴት አማርኛ ሊሆን ቻለ? እሱስ ኦሮምኛ መናገር እንዴት ተሳነዉ? እንግዲህ የታብሎይዱ ተስፋዬ ገ/አብን ተመልከቱልን ነብሱ ወደ ገደል ተጥላ ለመዉጣት ስትጥር ካቡ እንደገና እየተናደባት መልሶ ወደ እንጦሮጦስ ሲልካት።  ተስፋዬ ገ/አብ ደብረ ዘይት ተወልዶ እድገቱ ከኦሮሞ ልጆች ጋር ሁኖ እናቱ ኦሮምኛን አቀላጥፈዉ ተናግረዉ እሱ ግን ኦሮምኛን ካልተናገርከዉ ኦሮሞንና ቋንቋዉን ከእሱ በላይ የሚጠላ እንደሌለ በአጽኖት መግለጽ ያስፈልጋል። ቋንቋ በልጅነት ዘመን በቀላሉ ሊለመድ ይችላል ተስፋዬ ግን ለህዝቡና ለቋንቋዉ ንቀት ስለነበረዉ ሳይለምደዉ ተላልፎታል ከዚሀ ዉጭ ግን ሊሆን አይችልም። የሚያዉቀኝ ሰዉ የለም ወይም ደግሞ ሊደረስብኝ አይችልም  ቅቤ ሰጡኝ እያሉ መወሻከት ተስፋዬን ትዝብት ዉስጥ ከመጣል በስተቀር የሚያመጣዉ ፋይዳ አይኖርም። ተስፋዬ ስለ ኦሮሞ መጻፉም ከኦሮሞ ጋር ባለዉ ፍቅርና ትስስር ሳይሆን በኤርትራ እና አስመሮም ለገሰ በሚሰጡት የዉሸት መረጃ እና ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የሚቻለዉ ሁለቱን ትልቅ ጎሳዎች በማናከስ ነዉ በሚል ሂሳብ ተመስርቶ መሆኑን ማስገነዘብ ያስፈልጋል። እዚህ ላይ ጊዜዉ ረዘመ እንጂ ጀግናዉ አለማየዉ መለስ ከእጁ ፈልቅቆ  ያወጣዉን ሰነድ አያይዞ ማየት ጠቃሚነት ይኖረዋል። በነገራችን ላይ 40000 የኦሮሞ ተዋጊ መሳሪያዉን ሲያስፈቱት ተስፋዬ ከበረከት ስምኦን ጋር ዉስኪ እየጨለጠ ሲያንጓጥጥ ነበር።

ተስፋዬ ደብረዘይት ከተማ ዉስጥ ከደብረ ዘይት ልጆች ጋር ነዉ የኖረዉም የተማረዉም ደብረ ዘይት ደግሞ የወታደር ከተማ ሁና ይህን ተከትሎ በስፋት ቡናቤቶች እና ተጓዳኝ ንግዶችን ለመነገድ ከተለያየ ቦታ የመጡ ነዋሪዎች የሚኖሩባት እንጂ ተስፋዬ ገ/አብ እንደሚለዉ ኦሮሞዎች ብቻ ተመርጠዉ ኢትዮጵያዊነትን የሚጠሉባት የጎሳ ስብስብ አልነበረችም እኔም የደብረዘይት ሰዉ ነኝ ቤተሰቦችም የተለያዩ ጎሳዎች ቅይጦች ናቸዉ። የደብረዘይት፤ የናዝሬት፤ የሻሸመኔ፤ የዝዋይ ነዋሪዎች ተመሳሳይነት አላቸዉ አንድ ዘር የበላይነት ጎልቶ የሚታይባትም ከተማ አልነበረችም። ተስፋዬ  ግን እንዲመቸዉ በዛ መልኩ አቅርቧታል። እሱ ከኤርትራ መጥቶ ለደብረ ዘይት ኦሮሞዎች ቅርበት ሲኖረዉ ከኦሮም ጋር ሲጋቡ ሲዋለዱ ኢትዬጵያን የመሰረቱት አማሮችን ግን እንዲገደሉ ቀጭን ትእዛዝ ይሰጣል ይህ ነዉ ተስፋዬ ገ/

አብ አሙቼ።

ተስፋየ ገ/አብ የኦሮሞ ኔት ዎርክ በተባለዉ ቴሌቭዢን ቃለ መጠይቅ ተደርጎለት “ከቲፒለፍ ጋር ምን አጣላህ” ለሚለዉ ጥያቄ የቀለጠፈዉ መልሱ ጠያቂዉን ለማስደሰት “ከቡርቃ ዝምታ መጽፈህ በሗላ ህወአት ጤና አልሰጠኝም በዚሁ ካገር ጥዬ ወጣሁ” ይላል። እስቲ ይህን አባባል ታአማኒነቱን ከምክንያት  እና ከእዉነት ማእዘን እንመርምረዉ። ያለመታደል ሆነና በደርግ መላ ባጣ አሰራር  ኢትዮጵያ በሁለት ክፉ ጠላቶቿ እጂ ወደቀች (ሻቢያ እና ወያኔ) ብዙም ሳይኬድ ሻቢያ ተበልጦ ሙሉ ቁጥጥሩን ህዋቶች ወሰዱት። እነዚህ ድርጅቶች  የፍልስፍናቸዉ መሰረት የሆነዉ ኢትዮጵያን በዘር መከፋፈል ፤አማራዉን ማዳከም፤ ማጥፋት፤ሀገሪቱን በጎሳ መከፋፈል፤የኦርቶዶክስ  ሀይማኖት የስርአቱ አካል በመሆኑ ማፈራረስ ዋናዉ ሲሆን የዚህ ዘርፍ ደግሞ በተለያዩ ሁኔታዎች ላይ ይንጸባረቃል። እነዚህ የስርአቱ መመሪያዎች ዛሬም ድረስ በመተገበር ላይ ይገኛሉ ተስፋዬም ካድሬ በመሆኑ ዋናዉ ስራዉ ይህን ማስፈጸም ነዉ። ተስፋዬ ግን ህወአትን የአማራ ድርጅት በማስመሰል  ጠያቂዉን ሲያጃጂል ከቡርቃ ዝምታ በሗላ ነዉ ይለዋል በጣም ቀላላ መልስ የጭንቀት መልስ። ይህ መልስ ተስፋዬ  አቅጣጫ ማሳያዉ እንደተወናበደበት ከማሳየቱም በላይ የአእምሮዉ ሚዛን ምን ያህል እንደ ተዛባ ለማመላከት አዳጋች አይሆንም።   የቡርቃ ዝምታም ወገንን ከወገን ማናከስ የስራ ድልድሉ እና የተመሰገነበት ስራዉ በመሆኑ በህወአት ቤት በርታ ያሰኘዋል እንጂ  የሚያጣላዉ ነገር በፍጹም ሊኖር አይችልም። ተስፋዬ ግን ትርፍ አገኝበታለሁ ኦሮሞዎችን አጃጂልበታለሁ በማለት ይህን ከሚዛን የቀለለ ምክንያት ሰጥቷል። እዚህ ላይ ጠያቂዉ ብዙ ነገር የሚያዉቅ ሁኖ ሳለ በተስፋዬ ከሳሽነትም ወደ እስር የተወረወረ  ሁኖ እያለ  የተስፋዬም ምክንያት ተረት መሆኑን እያወቀ የተስፋየ መልስ ለእሱ ፖለቲካ ጠቃሚነት አለዉ ብሎ በመገመቱ ሲያልፈዉ የተስፋዬ መልስ ግን  ከአንድ ህፃን ልጂ የማይጠበቅ እንዳልሆነ ከጠያቂዉ የፌዝ አስተያየት መገንዘብ ይቻላል።  ተስፋዬ በኦሮሞ ስብሰባ  ዜግነቱን ለመቀየር በተደረገዉ ስነስርአት ላይ አስተዋዋቂዉ እንዳለዉ ተስፋዬ “በእዉቀት የተጎዳ ቢሆንም ጥሩ ጸሀፊ ነዉ” ብሎ ደረጃዉን መድቦት አልፏል።  አስተዋዋቂዉ እንዳለዉ ተስፋዬ የሚያስበዉን ከመናገሩና ከመጻፉ በስተቀር ከእሱ ከወጣ በሗላ በሌሎች ንግግሩ ወይም ጽሁፉ መመዘኑ ብዙም የሚያሳስበዉ ሰዉ አይደለም መታደል ነዉ በእዉነት።

መልካም ገና እና አዲሰ አመት

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

እንግዲህ ደጋፊዎቹ ለጥቃትም ሆነ ለእርማት በዚህ ድረሱኝ መልካም ገና እና አዲሰ አመት።semere.alemu@yahoo.com

 

 

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>