ኢትዮ-ኪክ ኦፍ እንደዘገበው በ2007 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጅማሮው መልካም የነበረው የደደቢት ስፖርት ክለብ በተከታታይ ጨዋታዎች ካስተናገደው ተደጋጋሚ ሽነፈት በኃላ አሰልጣኙን አሰናብቷል።
ክለቡ እንዳስታወቀው በአሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ የስራ ስንብት በሁለቱም አካላት ስምምነት እንደሆነ ቢገልፅም የቡድኑ በፕሪምየር ሊጉ የውጤት መንሸራተት በክለቡ ኃላፊዎች ዘንድ ክፉኛ ያሰቆጣ በመሆኑ በአሰልጣኙ መሰናበት ምክንያት ሆኗል። ክለቡ አዲሱን አሰልጣኝ በነገው እለት እንደሚያሳውቅ የተገኘው የክለቡ መረጃ ያመላክታል።