የህብር ሬዲዮ ታህሳስ 5 ቀን 2007 ፕሮግራም
< … የህወሃት ካንጋሮ ፍርድ ቤት የይስሙላ የመጨረሻ ውሳኔ ማለቁን ለአቶ ሀይለማሪያም ተነግሯቸው ይሆናል… ኮሚቴዎቹ ግን ቀድሞም ፖለቲካዊ ውሳኔ እንደሚሰጥ… የሙስሊሙ ተወካይ የሆኑትን ጀግኖቹን የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች አስሮ በጎን ከሚመስሏቸው ጋር የሚደረግ ድርድር ግን… >
ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረገው ቃለ ምልልስ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡ)
<…አንድነት ሰሞኑን የሚያካሂደው ተደራጅ ሕዝባዊ ንቅናቄ ነው… የኢትዮጵያ ሕዝብ ተደራጅ ሕዝባዊ ንቅናቄ ሰፊ መሰረት ያለው ነው። ተደራጅቶ የምርጫ ካርድ መውሰድ አለበት ድምጹን እንዳይዘረፍ መጠበቅ አለበት አይን ባወጣ መልኩ ሲዘርፉት አትዘርፈኝም ብሎ መተናነቅ እምቢ ማለት መቻል አለበት …>
አቶ ዳንኤል ተፈራ የአንድነት የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ፓርቲው ስለሚጀምረው ሕዝባዊ ንቅናቄ እና ተያያዥ ጉዳዮች ለህብር ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት )
የአሜሪካ የስለላ ድርጅት(ሲ.አይ.ኤ) የጭካኔ ምርመራ(ቶርች) መፈጸም መጋለጥና ኢትዮጵያን ጨምሮ ተባባሪ አገራት ላይ የነበሩ እስር ቤቶች( ልዩ ዘገባ)
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
ኢትዮጵያና ግብጽ በአባይ ግድብ ጉዳይ የጀመሩትን ድርድር አቋረጡ
የዘጠኙ ፓርቲዎች ትብብር አገዛዙ ከፍርሓት ተላቆ ለህዝብ ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጥ ጠየቀ
ሁለተኛ ዙር የትግል መርሐ ግብር በቅርቡ እጀምራለሁ አለ
የቻይናው ኩባንያና ኢትዮ ቴሌኮም በሁለት መቶ ሚሊዮን ዶላር ክፍአ ተቃቃሩ
ቻይና ለህወሃት አገዛዝ የመከላከያ ሀይልና ለሚሊሺያ ማጠናከሪያ በሚሊዮን የሚቆጠር ድጋፍ ማድረጓ ተቃውሞ ገጠመው
በኢትዮጵያ ያለው ጭቆና በአገሪቱ ላይ የታለመውን ዕድገት እንደማያመጣ ተገለጸ
የቀድሞ የግብጽ ጄኔራል ኢራን ኤርትራ ላይ ወታደራዊ ቤዝ ማድረጉዋ ለአካባቢው ስጋት ነው ሲሉ አስጠነቀቁ
አንድነት ሕዝቡ አስቀድሞ ከተደራጀ ድምጹ ሲሰረቅ መከላከል ይችላል አለ
ለዘጠኙ ፓርቲዎች ሰልፍ ሲቀሰቅሱ በሽንት ቤት ታስረው የነበሩት በህመም ላይ ናቸው
ሌሎችም ዜናዎች አሉ