Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የመድረክ ሰለማዊ ሰልፍ ተጠናቀቀ::

$
0
0

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) :

የመድረክ የወጣቶች ክንፍ ከፖሊስ እና ከፀጥታ አካላት እጅና ጓዋንት ሆኖ የክትትል፤ የኢንተለጀንስ እና የቁጥጥር ስራውን በአግባቡ እንዲሚወጣ ለመግለፅ እንፈልጋልን፡፡ የሚል የህዝብ ግንኙነት ስራ ትዝብት ውስጥ የጣለው የመድረክ ፓርቲ ከገንፍሌ ተነስቶ፣ በኣዋሬ ኣልፎ በየካ ክፍለ ከተማ የሚገኝ ኳስ ሜዳ መጨረሻው ያደረገው ሰለማዊ ሰልፍ ተጠናቀቀ።

10411210_1519465441657186_7328125686046851094_nበዘጠኙ ፓርቲ ላይ የደረሰውን እስር ድብደባ እና እንግልት እንዳላወገዘ የሚነገርለት መድረክ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ሁለት ሺህ የሚጠጋ የኣዲስ ኣበባ ኑዋሪ የተሳተፈበት ሰልፍ በወጣቶች የመድረክ ኣመራር፣ የሴቶች ተወካይ፣ ኣቶ ቡልቻ ሚደቅሳና የወቅቱ የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ዼጥሮስ ባሰሙት ንግግሮች ተጠቃሏል።
ሰለማዊ ሰልፉ የኢህኣዴግ መንግስት ሊያርማቸው የሚገቡ፣ መመቻቸት ያሉባቸው ፖለቲካዊ ምህዳር፣ መወገድ ያለበት የፀረ ሽብር ህግ ፣ ምርጫው ፍትሃዊ እንዲሆን ሊያደረጉ የሚገቡ ስራዎች እንዲሰሩ፣ በየቦታው እያጋጠመ ያለው ዓፈና፣ እስርና እንዲሁም ግድያዎች እንዲቆሙ ጥሪ ቀርበዋል።

የመድረክ ኣመራሮችና ወጣቶች እየመሩት የተካሄደው የሰለማዊ ሰልፉ ዓላማዎች የምያንፀባርቁ መፈክሮች በወጣቶች ኣባላት ተነበዋል። ከመፈክሮቹ

1- ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በነፃና ፍትሐዊ ምርጫ እንጂ በአስመሳይ ፕሮፓጋንዳ፣ በኃይልና በተጽኖ አይገነባም!!
2- የሀገራችን ችግሮች በነፃና ፍትሐዊ ምርጫ በሚገለጽ የሕዝብ ውሳኔ እንጂ በኃይል እርምጃ አይፈቱም!!
3- ከምርጫ በፊት የምርጫ ውድድር ሜዳው የሚስተካከልበት ውይይትና ድርድር እንዲካሄድ አጥብቀን እንጠይቃለን!!
4- በማስመሰያ ምርጫ በየአምስት አመቱ ሕዝብን ማታለልና ሀብቱን ማባከን ይቁም!!
5- የማስመሰያ ምርጫ ለማካሄድ ለሚባክነው የሀገርና የሕዝብ ሀብት ኢህአዴግ ተጠያቂ ነው!!
6- ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ በሌለበት ሁኔታ የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት እውን ሊሆን አይችልም!!
7- ሕዝባችን በ1ለ5 መረብ አፈናና ቁጥጥር ከሚካሄድ የምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ነፃ እንዲሆን እንጠይቃለን!!
8- ያለገለልተኛ የምርጫ አስተዳደርና ያለገለልተኛ የምርጫ ታዛቢ ታአማንነት ያለው ምርጫ ሊኖር አይችልም!!
9- ገለልተኛ የምርጫ ቦርድ በፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ ይቋቋም!!
10- በካድሬዎች የሚከናወን የምርጫ አስፈጻሚነትና ታዛቢነትን አንቀበልም፣ እናወግዛለን!!
11- ነፃ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ታዛቢዎች ምርጫውን በነፃነት የሚከታተሉበትና የሚታዘቡበት ሁኔታ
እንዲመቻች እንጠይቃለን!!
12- በምርጫ ወቅት በታጠቀ ኃይል በሕዝባችን ላይ የሚፈጸም ማስፈራሪያና ወከባን እናወግዛለን!!
13- በሰላማዊ ተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ላይ የሚካሄድ እስራትና ወከባ በአስቸኳይ ይቁም!!
14- ኢህአዴግ በመንግሥት ሀብትና ንብረት የሚያከሄደውን ሕገወጥ የምርጫ ዘመቻ እናወግዛለን!!
15- የጸጥታ ኃይሎች የሕዝብ አገልጋዮች እንጂ ሕዝብን ማስፈራሪያና ማሸማቀቂያ መሆን የለባቸውም!!
16- ያልተሟላ የምርጫ ሥነምግባር ኮድ ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ ለማካሄድ አያስችልም!!
17- ከድምጽ መስጫ ጣቢያዎች የተቃዋሚ ፓርቲ ታዛቢዎችን ማባረር የሕዝብን ድምጽ ለመስረቅ ስለሆነ በአስቸኳይ
እንዲቆም እንጠይቃለን!!
18- የሕዝብን ድምጽ መዝረፍ ዴሞክራሲን መገንባት ሳይሆን መቅበር ነው!!
19- የምርጫ ጣቢያዎች ከአስተዳደር አካላትና ከታጣቂ ሠራዊት ተጽኖና አፈና ነፃ ይሁኑ!!
20- በምርጫ ወቅት በምርጫ ጉዳዮች ፈጣን ውሳኔ የሚሰጡ ነፃና ገለልተኛ ዳኞች በየደረጃው እንዲኖሩ እንጠይቃለን!!
21- ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ማሰር፣ ማሰቃየትና መግደል ሕዝባችን በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የሥልጣን ባለቤት ለመሆን
የሚያካሄደውን ትግል አይገታም!!
22- ሀሳብን የመግለጽ ሕገመንግስታዊ መብታቸውን በመጠቀማቸው የታሰሩ የሕልና እስረኞች በሙሉ በአስቸኳይ ይፈቱ!!
23- በግፍ የታሰሩ ሰላማዊ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት፣ ጋዜጠኞችና የሙስሊሙ ማሕበረሰብ መፍትሔ አፈላላጊዎች በአስቸኳይ ይፈቱ!!
24- የፀረ-ሽብር ሕጉን ለፖለቲካ ዓላማ መጠቀሚያ ማድረግን እናወግዛልን!! ሕገ-መንግሥታዊ መብትን በማይጥስ
ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲሻሻልም እንጠይቃለን!!
25- የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ለገዥው ፓርቲ የሚያሳዩትን ወገንተኝነት በአስቸኳይ ያቁሙ!!
26- ሁሉም ፓርቲዎች በሕጋዊና ፍትሐዊ አግባብ ከመንግሥት በጀት ድጋፍ የሚያገኙበት ሥርዓት እንዲኖር አጥብቀን እንጠይቃለን!
27- በነፃነት የመሰብሰብና የመደራጀት መብታችን ይከበር!!
28- የአንድ አምባገነን ፓርቲ ሳይሆን ትክክለኛ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት እንሻለን!!
29- ኢህአዴግ ለሕገመንግሥትና ለሕግ ተገዥ በመሆን ለነፃ ምርጫ እራሱን እንዲያዘጋጅ እንጠይቃለን!!
30- የሕግ የበላይነት ባልተከበረበት ሁኔታ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት አይቻልም!!
31- የኑሮ ውድነቱና የተጎሳቆለው የሕዝባችን ሕይወት የኢህአዴግ የኢኮኖሚና ማሕበራዊ ፖሊሲ ውጤቶች ናቸው!!
32- በወገንተኝነትና በአድልኦ በሕዝባችን ላይ የሚጫን ግብር በአስቸኳይ ይስተካከል!!
33- በልማት ስም በሕገወጥና ግብታዊ በሆነ መንገድ ሕዝብን ማፈናቀልና ለችግር ማጋለጥ እንቃወማለን!!
34- የመሬት ወረራ ይቁም!!
35- በሙስና የተዘረፈው የሕዝብ ሀብት ለሕዝቡ ይመለስ!! ሙሰኞችም ለፍርድ ይቅረቡ!!
36- የውኃ፣ የማብራት፣ የትራንስፖርትና የስልክ አገልግሎቶች ችግሮቻችን በአስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጣቸው እንጠይቃለን!!
37- የአህአዴግ አገዛዝ በሐይማኖቶች የውስጥ ጉዳዮች የሚፈጽማቸውን ጣልቃ ገብነቶች እናወግዛለን!!
እነዚህ መፈክሮች ለመላ ዓለም ይሰራጫሉ ተብለው ይጠበቃል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>