ለዘሐበሻ የደረሰው ሰበር መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ ቴዲ አሁንም ከሃገር እንዳይወጣ በመከልከሉ የተነሳ ነገ ቅዳሜ ሊደረግ የነበረው የ አምስተርዳም ኮንሰርት ተሰርዙአል።
የዘሐበሻ ምንጮች አንዳሉት ከሆነ ቴዲ ለምን ከሃገር እንዳይወጣ እንደታገደ ፍርድ ቤት የጠየቀ ሲሆን ፍርድ ቤት ከምንም ነጻ ነህ፤ የትም ሃገር ሄደህ መንቀሳቀስ ትችላለህ የሚል ወረቀት ቢሰጠውም ደህንነቶች ሊያስወጡት ኣልቻሉም። ፓስፖርቱን የቀሙት ወገኖች ዛሬ እንደሚሰጡት ቃል ገብተው የነበረ ቢሆንም ሊሰጠው አልቻለም፥። ሰኞ ሲሄድ ማክሰኞ ና!… ማክሰኞ ሲሄድ ሮብ…ሮብ ሲሄድ ሃሙስ… ሃሙስ ሲሄድ አርብ.. አርብ ሲሄድ ሰኞ እያሉ እያመላለሱት ነው። ፓስፖርቱን የያዙት ደህንነቶች የፊታችን ሰኞ እንሰጥሃለን ብለው ቃል እንደገቡለት የገለጹልን ምንጮች ኣሁንም ሰኞ ፓስፖርቱን ስለመስጠጣቸው ምንም ማረጋገጫ እንደሌለ ለዘበሻ ገልጸዋል።
የቴዲ ባንድ አምስተርዳም ገብቶ የቴዲን መግባት እየጠበቀ ቢሆንም ሊመጣ ባለመቻሉ በከፍተኛ ኪሳራ አየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። እንደደረሰን መረጃ ከሆነ በቴዲ ኣፍሮ ላይ አስካሁን 33 ሺህ ዩሮ ኪሳራ ደርሶበታል።
ቴዲ በሚቀጥለው ሳምንት ቅዳሜ ኖርዌይ የሙዚቃ ኮንሰርት ያቀርባል ተብሏል ፡ ሰኞ ደህነቶች ፓስፖርቱን ከለቀቁለት።
ተጨማሪ መረጃ ካገኘን አናቃምሳችሁኣለን። ከዘሀበሻ ጋር ቆዩ።