Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ግንቦት ሰባት ሆይ…. ከሄኖክ የሺጥላ

$
0
0

Henok Yeshitila

Henok Yeshitila


ውድ ወዳጆቼ ሆይ ፣ ዛሬ ተክሌን መሆን አምሮኛል ( ተክሌ ይሻውን ሳይሆን ተክለሚካዔል ሳህለ ማርያምን )። ልጅ ተክሌ መቼም እኔ’ነቴን ለምን ወሰድክብኝ እንደማትለኝ ነው ። እንኩዋን እኔነት ፣ የእኔነት መፈጠሪያ የሆነችውን ሀገርህን ወስደዋትስ የለ ።

የዛሬ ጽሁፌ የሚያጠነጥነው ትልቁንና እና ጠንካራውን ድርጅት ግንቦት ሰባትን ላይ ነው ። እንደውም ጽሁፌን ከማውጠንጠን ማነጣጠር ሳይሻል አይቀርም ( የታጠቀን እንዲያ ነው እንጂ !) ። እና የምወደውን ግንቦት ሰባት ፣ ባልሞትለት እንክዋ የምደማለት ግንቦት ሰባትን ፣ የኔ የምለውን ግንቦት ሰባት ፣ የ አንዳርጋቸውን ግንቦት ሰባት ፣ የብርሃኑ ነጋን ግንቦት ሰባት ፣ የዔፍሬም ማዴቦን ግንቦት ሰባት ፣ የአበበ ገላውን ግንቦት ሰባት ፣ አዎ ስለሱ ነው ።
andargachew
አንተ ግንቦት ሰባት ሆይ ፣ አንተን ካወቅኩበት ቀንና ሰዓት ጀምሮ ትቢት ትቢት ይለኛል ፣ ወያኔ ምን ለማስፈራራት ቢሞክር ፣ ነገራቸው ሁሉ ድንፋታ እንጂ አንዳች ፍርሃት ልቤን ይሁን ሆዴን ቅም አይለውም ፣ ስላንተ ሳስብ አባቱን ከሩቅ እንዳየ ህጻን እፈነድቅአለሁ ፣ ስምህ በክፉ ሲነሳ ፊቴ ደም ይለብሳል ፣ የባንክ ደብተሬ እንኩዋ ዜሮ እያሳየ ስላንተ ስሰማ ምን እንደሆነ ባላውቅም መንዝር መንዝር ይለኛል ፣ ዘርዝር ዘርዝር ይለኛል ፣ ያም ሆኖ አንዳርጋቸው ከታሰረ ወዲያ ላንተ ያለኝ ፍቅር ወደ ንዴት እየሄደ ነው ። ይሄም የሆነው አንዳርጋቸው በመያዙ ሳይሆን ፣ የአንዳርጋቸውን መያዝ ተከትሎ ይህ ነው የሚባል አጸፋዊ እርምጃ ባለመውሰድህ ነው ። ሰማያዊ እንኩዋ ነጭ እርግብ ጭንቅላቱ ላይ አድርጎ ሰላም ሰላም እያለም ፣ እየተገፈተርም ቢሆን ሰልፍ ወጥቶዋል ፣ “የምንገለው ባይኖረንም የምንሞትለት ሕዝብ ግን አለን” ብሎ ይሄው እሳት ከጨበጠ ጋ በ እስክርቢቶ ትግሉን ሀ ብሎ ከጀመረ ቆየ ፣ አረ እንደውም እስክርቢቶ መግዣውን እኔም ተባብሬያለሁ ( በሱም በጣም ደስተኛ ነኝ ) ። ኢንጂነር ይልቃልን ሳስብ ማህታማ ጋንዲ ወይም ማርቲን ሉተር ኪንግ ትዝ አይሉኝም ፣ ምክንያቱ ደሞ፣ ወዳጄ ይልቃል እንደነሱ ጠንካራ አይሆን ይሆን ብዬ ስለማስብ ሳይሆን ፣ መሃተማ ጋንዲና ማርቲን ሉተር ኪንግ መስዋት የሆኑላቸው አይነት ሕዝብ ከጎኑ ስለሌለ ብቻ ። ይልቃል እና ጉዋደኞቹ እንደውም ከማህታማ ጋንዲም ሆነ ከ ማርቲን ሉተር ኪንግም ይበልጣሉ ፣ ለምን ቢባል ፣ የሚታገሉት ስርዓት ምን ያህል ጨካኝ እንደሆነ እያወቁት ትግሉ ውስጥ በአስር ጣታቸው እንደገቡበት ሳስብ ። የብረት ትግል የሚል ነገር ባያነሱም ግን ከብረት ትግል እኩል የሕይወት መስዋትነት እየከፈሉ እንደሆነ ስገነዘብ እውነት እውነት እልሀለው ደግሜ ደጋግሜ አከብራቸዋለሁ ። እንደውም አንዳንዴ ግር የሚለኝ ፣ እነሱ ለተገረፉት ፣ እነሱ ለተሰቃዩት ፣ ” በሰላማዊ ትግል ወያኔ ይወድቃል ብሎ ማስብ ዘበት ነው !” እያልኩ እኔ ራሴ አወራ ነበር ። ግን ቆይቶም ቢሆን የገባኝ ለካ ለሀገር ሲሉ መሞቱን ነው ” ሰላም ” ያሉት እንጂ ትግሉማ መች ሰላም አለው ብለህ ነው ። መቼም በደንብ እንደምታውቀው እኔ ” ወያኔ ባሩድ አሽትተን እንጂ ፣ እርግብ አሳይተን እናሸንፈዋለን ማለት ዘበት የሚመስለኝ ሰው ነኝ ” እንዴት ሸለምጥማጥን እርግብ ሆነህ ትቀርበዋለህ ?

ወደ አብይ ጥያቄዬ ስመጣ ስለ ትግሉ ሳስብ ሆድ ይብሰኛል ፣ መቼ ይሆን ጦርነቱ የሚጀመረው እያልኩ ከራሴ ጋ አወራለሁ ፣ በይበልጥ በግንቦት ሰባት ስም የተገደሉ ፣ የታሰሩ ፣ ከስራ የተፈናቀሉትን ሰዎች ሳስብ ፣ በጣም የዘገየህ ይመስለኛል ፣ ይሄ የኔ ብቻ ጥያቄ እና መብሰልሰል እንዳይመስልህ ፣ ያው እኔ ስለማልፈራ ነው ጥያቄውን የጠየቅኩት እንጂ አሁን አሁን የብዙ ወዳጆቼ ጥያቄ እየሆነ ነው ። መቼ ነው አዲስ አበባ ላይ የወያኔ ባለስልጣን ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገደሉ ሲባል የምንሰማው ? መቼ ነው የወያኔ ባለስልጣኖች ሲንማ-ራስ መቃም የሚያቆሙት ፣ መቼ ነው ከህዝብ ጋ መተራመስ የሚያቆሙት ፣ መቼ ነው ቀን የግንቦት ሰባትን አባላት እና ሌሎች ንጹሃን ሰዎችን ማዕከላዊ ወፌ ላላ ሲገርፍ የዋለ የ ወያኔ ባለስልጣን ማታ አንገቱ ተቆርጦ የምናየው ? መቼ ነው ? የክርስቶስ ዳግም መምጣት እንኩዋ እንዳንተ ውጊያ መጀመር በዙም አልጉዋ-ጉዋ-ንኝም !

መልሱን በድርጊት ትመልሱልኝ ዘንድ ከወገቤ ዝቅ ብዬ እጠይቃለሁ ።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>