Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ኮንዶሚኒየም ፎቅ ላይ የወጣውን ጅብ ለማስወጣት በተከፈተ ተኩስ አንድ ወጣት ቆሰለ

$
0
0

sendek በመስከረም አያሌው

በሐያት ኮንዶሚኒየም ሶስተኛ ፎቅ ላይ ወጥቶ አልወርድም ያለውን ጅብ ለማስወጣት በተተኮሰ ጥይት አንድ ወጣት ቆስሎ ሆስፒታል ገባ።
በህንጻው ላይ የሚኖሩ የአይን እማኞች እንደገለፁት፤ ከትናንት በስቲያ ከምሽቱ አራት ሰዓት ገደማ ወደ ህንጻው በማምራት ሶስተኛ ፎቅ አንድ መኖሪያ ቤት በር ላይ የተኛውን ጅብ ትላንት ለማስወጣት አምስት ጥይቶች ተተኩሰው ጅቡ የተገደለ ሲሆን፤ በአካባቢው የነበረ አንድ ወጣት በነጠረ ጥይት ሆዱ ላይ ተመትቶ ሆስፒታል ገብቷል። ፎቁ ላይ የወጣው ጅብ እስከ ትናንት ከረፋዱ አራት ሰዓት ገደማ ድረስ እዚያው ፎቁ ላይ መቆየቱን የተናገሩት ነዋሪዎቹ ጅቡን እንዳዩት በማስፈራራት ለማስወጣት ቢሞክሩም አልቻሉም። ነዋሪዎቹ ለፖሊስ ስልክ ደውለው ያሳወቁ ሲሆን፤ ፖሊስም “ለአካባቢ ጥበቃ በስልክ ጉዳዩን አሳውቀናል” በማለቱ ጅቡ እዚያው ሊያድር ችሏል።
ጅቡ በህንጻው ላይ እስካለበት ጊዜ ድረስ ፎቁ ላይ የነበሩ ነዋሪዎች ከቤታቸው ሳይወጡ መቆየታቸውን የገለፁ ሲሆን፤ ትናንት ጠዋት ላይም አንዳንድ ወላጆች በዱላ እና በአንዳንድ ነገሮች ጅቡን እየተከላከሉ ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት መላካቸውን ገልፀዋል። ጅቡ በህንፃው ላይ ሌሊቱን ሙሉ በማሳለፉ ከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ ሆነው ማደራቸውን የገለፁት የህንጻው ነዋሪዎች፤ ጅቡ ከቦታው እስከተነሳበት ሰዓት ድረስም እንደልባቸው በህንጻው ላይ ለመንቀሳቀስ መቸገራቸውን ገልጸዋል። በህንጻው ላይ እንዲህ አይነቱ ነገር ሲፈጠር ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን የገለፁት ነዋሪዎቹ፣ በሁኔታው በጣም መደናገጣቸውን ገልጸዋል።
ጅቡ በህንጻው ላይ ሌሊቱን ሙሉ ካሳለፈ በኋላ እስከ ትናንት ረፋድ አራት ሰዓት ድረስ እዚያው የቆየ ሲሆን፤ አራት ሰዓት ተኩል አካባቢ በፖሊስ አማካይነት በአምስት ጥይቶች ተገድሎ ከህንጻው ላይ ሊወርድ ችሏል።n

(ምንጭ፡-ሰንደቅ ጋዜጣ 8ኛ ዓመት ቁጥር 405 ሰኔ 5/2005)


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>