Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ተንበርክኮ ከመኖር በዓላማ ፀንቶ መሞት ይሻላል!! –በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ

$
0
0

ሕዳር 22 ቀን 2007 ዓ.ም

ዝነኛው ገጣሚና መምህር ኃይሉ ገብረዮሐንስ

መምህር ኃይሉ ገብረዮሐንስ

በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ ዝነኛው ገጣሚና መምህር ኃይሉ ገብረዮሐንስ በስደት ከሚኖርበት አገር ስዊድን( ስቶኮልም ከተማ) ጥቅምት መጨረሻ 2007 ዓ.ም ማረፉን የሰማው በከፍተኛ ሀዘን ነው።

ሃይሉ ገብረዮሐንስ በመምህርነት ሙያው እንደ አንድ ሃላፊነት የሚሰማው ዜጋ ሀገር ወዳድ ትውልድ ለመፍጠር የበኩሉን አስተዋፅኦ አድርጓል። የዚያ ትውልድ ግንባር ቀደም የለውጥ ሃዋሪያ ሰለሆነም የአገር ባለውለታ ነው። በተፈጥሮ ባገኘው ተሰጥኦና በትምህርት ባዳበረው ገጣሚነት ቀስቃሽ ፣አነቃቂ፣ ትምህርታዊ፣ ፍልስፍናዊና ሥነ ጥበባዊ የሆኑ ግጥሞችን በማቅረብ ይታወቃል። ገሞራው ከወጣትነት እድሜው ጀምሮ ለጭቁን ህዝቦች አርነት መውጣት በፅናት የታገለና በተግባር ያስመሰከረ ነው። እምቅ መልዕክት በያዙት ግጥሞቹ የተነሳም ስቃይ፣ ግርፋትና እስር ደርሶበታል።—[ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—

 

Download (PDF, Unknown)

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>