(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ ሐሙስ በአዲስ አበባ ዓለም ባንክ ስልጤ ሰፈር በርካታ ቤቶች መፍረሳቸውን የዓይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ በፎቶ ግራፍ አስደግፈው ገለጹ::
እንደ ዘጋቢዎቻችን ገለጻ ከሆነ ቤታቸው የፈረሰባቸው ወገኖች መሄጃ አጥተው ሸራ ወጥረው የተቀመጡት እነዚሁ ወገኖች በድጋሚ ቤታቸው ፈርሶባቸዋል::
ቤታችን ለምን ይፈርሳል በሚል ጥያቄ የሚያቀርቡትን የመንግስት ደህንነቶች እያስፈራሩ መሆኑን የገለጹት ዘጋቢዎቻችን ቤቶቹ እየፈረሱ ያለው ካርታ የላቸውም በሚል ምክንያት ነው ተብሏል:: እንደዘጋቢዎቻችን ገለጻ ከሆነ መንግስት ከ2003 በፊት የተሰሩ ቤቶች አይፈርሱም በሚል ቃል የገባ ቢሆንም ቃሉን ሳይጠብቅ ከዛ በፊት የተሰሩ ቤቶችም ፈርሰዋል::
በአሁኑ ወቅት ቤታቸው የፈረሰባቸው ወገኖች በችግር ላይ እንደሚገኙም የደረሰን መረጃ ያመለክታል::