የ United States ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ ባለፈው ሐሙስ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ የመኖርያ ፈቃድ የሌላቸው የውጭ ሀገር ተወላጆችን ህይወት ሊለውጥ የሚችል የ United States ን የኢሚግሬሽን ፖሊሲን የሚቀይር ውሳኔ እንደሚወስዱ ማስታወቃቸው ይታወሳል። አቶ ተመስገን ተካ የኢሞግረሽን ህግ ባለሙያ ያብራራስሉ።
አዳነች ፍሰሀየ
24.11.2014 23:41
ዋሽንግተን ዲሲ—
የ United States ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ ባለፈው ሐሙስ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ የመኖርያ ፈቃድ የሌላቸው የውጭ ሀገር ተወላጆችን ህይወት ሊለውጥ የሚችል የ United States ን የኢሚግሬሽን ፖሊሲን የሚቀይር ውሳኔ እንደሚወስዱ ማስታወቃቸው ይታወሳል።
ይህ ፖሊሲ የሚመለከተው ከ 11 ሚልዮን በላይ ከሚሆኑት ህጋዊ የመኖርያ ፈቃድ የሌላቸው መጤዎች 5 ሚልዮኖቹን ነው። ውሳኔው በአብዛኛው የሚመለከተው ከላቲን አሜሪካ የመጡትን ቢሆንም ብዙ ኢትዮጵያውያንና ሌሎች አፍሪቃውያንም ተመሳሳይ ችግር እንዳለባቸው አሙን ነውና ስለ አጠቃላይ ይዘቱ እንዲያብራሩልን የኢሚግረሽን ህግ ባለሙያ የሆኑትን አቶ ተመስገን ተካን ጋብዘናል።
አቶ ተመስገን የአለም አቀፍ የንግድ ህግና የኢሚግረሽን ህግ ባለሙያ ናቸው።የአፍሪቃ ነክ ርእሶች አዘጋጅና አቀራቢ አዳነች ፍሰሀየ ናት ያነጋገረቻቸው። ውሳኔው የሚመለከተው የትኞቹን መጤዎች እንደሆነ በማብራራት ይጀምራሉ።