ታቦተ ጽዮንን አስመልክቶ በቅዱስ ፓትርያርኩ መግለጫ እንደተሰጠበት አስመስሎ በሰሞኑ ሲናፈስ የነበረው ወሬ ፍጹም የፈጠራ ወሬና አሉባልታ መሆኑን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት ህዳር 6 ቀን 2007 ዓ.ም በወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡ የሐሰት ወሬው ምንጭ ዘመኑ በወለደው ኢንተርኔት አማካኝነት የተናፈሰ ሲሆን ጽሑፉ ሙሉ በሙሉ ሐሰትና እርስበርስ የሚጋጭ አንድም እውነታ የሌለው ከመሆኑም በላይ የቤተ ክርስቲያንንና የሀገርን ሰላም ለማወክ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ሴራ መሆኑን መግለጫው አስታውቆአል፡፡ በተጨማሪም ይህንን የፈጠራ ሐሰተኛ ወሬ ወደ ጎን በመተው ምዕመኑ የተለመደውን ታሪካዊ የኅዳር ጽዮን በዓል በቅድስት ከተማ በአክሱም ጽዮን በመገኘት እንዲያከብሩም ጥሪውን አስተላልፎአል፡፡ የተከበራችሁ አንባቢዎች ከቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት የተሰጠውን ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡
↧