Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የማለዳ ወግ …እኔ ፣ እነሱ እና “ቁንጽል ”የሚሉት መረጃ … (ነቢዩ ሲራክ)

$
0
0

የማለዳ ወግ …
እኔ ፣ እነሱ እና “ቁንጽል ” የሚሉት መረጃ …
* ደረቁ የካልድ እንባ
*  ” ለዚህማ ነፍስህንስ ብትሰጥ ምን አለበት! ” እናቴ …

Nebiyu Sirak ሳውዲ ውስጥ በገፋሁት ሁለት አስርት አመታት ከተለያዩ ወገኖቸ ከውስጥም ከውጭም ስደተኛውን በሚመለከት ተጨባጭ መረጃዎች ይደርሱኛል። የሚያመውን ምስል የያዙ መረጃዎችን ከሙያ አንጻር ብቻ ሳይሆን መረጃውን የሚመለከቱትን ወገኖቸን ስሜት እንዳልጎዳ በሚል በጽሁፍ ከመግለጽ ውጭ አልለጥፋቸውም ። መረጃዎችን ይዠ በቅርቤ ወዳለው የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ቀርቤ አሳይቻቸውም አውቃለሁ ። በመብት ጥበቃ አልተጋችሁምና ትጉ ስላቸው ምክሬን አይቀበሉትም።  ይባስ ብለው በአይነ ቁራኛ ያዩኛል ፣ ካንድም ሁለት ሶስቴ ከቆንስሉ ግቢ እንዳትደርስ ተብየም አውቃለሁ !  ነጻ ከሚባለው ኮሚኒቲ ድረስ ዘልቀው የአባልነት መታወቂያየ እንዳይታደስ አድርገው ያውቃሉ ! ” ሃገር ቤት አይገባትም ” የሚባለው ተራና የወረደ ማስፈራሪያ የተለመደ ቢሆንም ሃገር ቤት ስገባ ግን ችግር ገጥሞኝ አያውቅም … ቂም ተቋጥሮብኛልና ዛሬ በተፈታ ድራማ የመንግስ ተወካዮች ለሁለት ወራት ከከባድ ወንጀለኞች ማጎሪያ ወህኒ ስወረወር እንደ ዜጋ መብቴን ለማስከበር ቀርቶ ” የት ነው? “ብለው አልጡቁኝም  … ! ልብ በሉ የማወራው ላይ ላዩን ነው!

ያን ሰሞን በጠራራ ጸሃይ ሜዳ ላይ የወደቀች እህት ወደ መጠለያ አስገቧት ለማለት ወደ ተጠባባቂው የጅዳ ቆንስል ጀኔራል አቶ ሸሪፍ ከይሩ ቢሮ ጎራ ብየ መረጃ ሳቀብላቸው አጠር ያለች ውይይት አድርገን ነበር ፣ ብዙ ከተወያየን በኋላ በተደጋጋሚ ስደውልላቸው ለምን ስልኬን እንደማያነሱ ጠይቄያቸው ” ሁሉን የምታውቅ ይመስልሃል ፣ ግን አታውቅም…ቁንጽል መረጃ ይዘህ ፣ ጉዳዩን ፖለቲሳይዝ እንደምታደርግ ስለምናውቅ አንተባበርህም! ” ሲሉ እንቅጩን ነግረውኝ አዝኛለሁ !  በዋናነት ለዜጎች መብት ማከበር የመንግስቱ ከፍተኛ ሃላፊነትን ተሸክመው ከተቀመጡት ሃላፊ መስማቴን ይህች ሃገር የማናት ? አላልኩም ፣ ሃገሩም ህዝቡም የእኔ መሆኑን ጠንቅቄ አውቃለሁ !   ያም ሆኖ አሁን አሁን ሃገሯ የእኔም ጭምር ሆና የምወዳቸውን ልጆቸን ይዠ እንደ ኩሩ ዜጋ እረፍቴን በሃገሬ ለማድረግ አልታደልኩም! ” የምሰማው ጥሩ አይደለም ፣ ከመጣህ እረግምሃለሁ ፣ ለልጆችህ ኑርላቸው !” የምትለኝ መነኩሴ እናቴ ቃልና ምክሯን ለማክበር ግድ ብሎኝ ሃገር ቤት መሄዱን ሳልወድ በግድ ደጋግሜ ሰርዥዋለሁ! ቀዳሚውን ፈጣሪ ቢያውቀውም ለመሰረዝ ውሳኔ ያደረሰኝ የምሰማውን ማድፈራሪያ ግፊቱን ፈርቸ ሳይሆን  የምወዳት እናቴ በመጨረሻዋ የህይዎት ዘመኗ ላሳዝናት ስለማልሻ እንጅ ” የቆስል ስራውን በማደናቀፍ! ” አለያም “ሽብርተኛ ደጋፊ “የሚል ክስ ተለጥፎብኝ  መታሰር መገረፉን የሚፈራ ልብ ኑሮኝ አይደለም  !  በማምንበት የአረብ ሃገር ስደተኛ ዜጎች መብት ይከበር ተዛማጅ መረጃና ሂስ በመሰንዘሬ  የሚመጣውን ለመቀበል ነፍሴ በጸጋ ልትቀበል ከቆረጠች አመታት አልፈዋል …

ይህን ሁሉ ማለቴ ያለ ነገር አይደለም ፣ ምሽት ላይ ሁለት ተቃራኒ ክስተትን አስተናግጃለሁና ነው ። አንዱ የቤሩቷን ብርቱላንና በኦማን የአልማዝን አበሳ ባቀረብኩበትየመረጃ ግብአቴ የተበሳጨ ወንድም ” … ደላላ ፣ ቆንስል ፣ መንግስት ምንቴስ እያልክ ፣ ቁንጽል መረጃ ይዘህ መንግስትን ታጋልጣለህ ፣ ገጽታ ታበላሻለህ ” የሚል ሰብዕናን መሰረት አድርጎ መወያየት የማይሻ ፣ ሲያስረዱት የማይገባው ጨካኝ  አጋጥሞኝ ነው …ሌላው ክስተት ደግሞ የዚህ ተቃራኒ መረጃ ሲሆን ” የሳውዲውን ትተህ ለምን ወደ ኦማንና ሊባኖስ ትሔዳለህ ?” ያለኝን አድራሻው የጠፋብኝን ወንድም አግኝቸው ፣ ከዚህ ቀደም የማወረቀውን መረጃ ልኮልኝ በአሳዛኙ ታሪክ ተረባብሻለሁ ! የሃገሬን ገጽታ እንደማላከፋ ፣  ቁንጽል መረጃ እንደማላውቅ ለዛሬው ሞጋቸና ለቆንስል ሸሪፍ ከይሩ ለትናንት ምሽቱ ሞጋቸ ምላሽ ይሆነኝ ዘንድ ሁለተኛውን ክስተት “ጉዳይ  እንዲህ ነው ” ብየ ልጀምረውና በቀጣይ ቀን ዝርዝር መረጃውን ላሳያችሁ ቆርጫለሁ  ! ጀሮ ያለው ይስማ  !

ወጣቱ ካልድ በከዛን ሆስፒታል …
ነገሩ እንዲህ ነው ፣ በሁለት አመት በፊት ገደማ በቀረበ የመረጃ ቅበላየ ” አንዲት እህትና አንድ ወንድም በየመን ሳውዲ የጠረፍ ከተሞች የመኪና አደጋ ደርሶባቸዋል ፣ ከተቻለ በፍርድ ቤት የኢንሹራንሱን ጉዳይ ተከታትላችሁ ጨርሱ ፣ አለያም ወደ ሃገር የሚገቡበትን መንገድ ፍጠሩ! ” ብየ ከሰላ ሂስ ጋር ጽፊ ነበር ። … ያን ጽሁፍ ካቀረብኩ በኋላ አልፎ አልፎ ስለጉዳዩ መረጃ የሚያቀብለኝ ወዳጀ ተጎጅዎች ወደ ሃገር በመላኩ ረገድ የጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት ምንም የሰራው ስራ አለመኖሩን አጫወተኝ ፣ ምንም ማድረግ ስለማይቻለኝ እኔና እርሱ የሚቻለንን ማድረጋችን ከህሊና ጸጸት ድነናል በሚል ብቻ አስረዳሁት ። ከዚያ በኋላ በግል ወደ ጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ዘንድ በአካል ሳይቀር ቀርቤ ለማስረዳት ሞከሬ  ” ጉዳዩ በፍርድ ቤት ተይዟል።፣ እኛ ምንም ማድረግ አንችልም  ” ማለታቸውን አስታውሳለሁ  ! ይህ ከሆነ ታዲታ ቆይቷል …

የጀዛኑ ወዳጀ አድራሻ በመቀየሩ ስለ ወጣት ካልድ የማገኘው መረጃ ተቋረጠ ። ያም ሆኖ ከስድስት ወር በፊት አንደ ሌላ ወንደም ካልድ እስካሁም በሆስፒታል የመኖሩን ፣ ሴቷ እህት ግን ከወራት በፊት ወደ ሃገር ቤት በአሳር በመከራ መግባቷን የጻፍኩትን የተከታተለ የጀዛን ነዋሪ በህዝብ ስልክ ደውሎ ” ማንነቴን አልነግርህም ፣ ካልድ በስቃይ ላይ ነው ፣ ወይ ሃገር ቤት አልገባ ወይ … ” እንዳለ ንግግሩን ሳይቀጥል የሳግ ድምጽ ተከትሎ ስልኩ ተዘጋ  ! ከቦታው የደረሰኝ የዚህ ሌላ መረጃ ባለቤት ስሜት መጎዳቱ ገብቶኛልና ውስጤን አወከው …ደነገጥኩ  ! ያ ሰው ግን ከዚያ ወዲህ ደውሎልኝ አያውቅም ፣ ከዚያ ጊዜ በኋላ በኩባንያ ስራ ምክንያት በተደጋጋሚ ወደ ጀዛን ብሔድም ከስራ ጫና የተነሳ ወደ  ሆስፒታሉ መሄድ ገደደኝ …እናም በቃ የሚወተውት የሚያስታውሰኝ ወዳጀ ርቋልና ካልድን ረሳሁት …

ዛሬ እኩለ ሌሊት ካልድን በሚመለከት አንድ አስገራሚ መረጃ ደረሰኝ ፣ ያ ወዳጀ በኦማን ለአካል ጉዳት ተዳርጋ ሀገር ቤት ለገባችወደ ለአልማዝ እርዳታ ከተሰራጨ የስልክ ቁጥሬን አግኝቶ መደወሉን አጫወተኝና ወደ ጉዳያችን ማወረጋት ጀመርን … ካልድ ስላለበት ሁኔታ ይነግረኝ ገባ ፣ አላመንኩም ፣ ለክፉ ለደጉ በሚል መረጃ አፍቃሬ መሆኔን ያውቃልና ” ተመልከተው!” ብሎ ካልድ ያለበትን ሁኔታ የሚያሳየውን መረጃ ላከልኝ … ተደመምኩ ፣!  የደረሰኝ መረጃ ለ”ቁንጽል መረጃው ” ውንጀላቸው ምላሽ ከመሆን ባለፈ መንግስት በዜጎቹ መብት ጥበቃ ዙሪያ ስለማይተጉ ሃላፊዎችና ጽንፈኛ ደጋፊዎቹ የተንሸዋረረ መረጃ ትቶ እውነቱን ይረዳ ዘንድ ይህ መረጃ ማሳያ ከሆነው ላቀርበው ወደድኩ ! መንግስት እንደ ቀደመው  ማየት ፣ መስማት ካልቻለ ደግሞ እየሆነ ያለውን እስኪያይ፣ እስኪሰማና  እስኪገባው የሚያገባን እንጮሃለን  !  በቃ ! ይህን ነው የምለው  ! …

ምናልባት እናቴ የወጣት ካልድን አሳዛኝ ታሪክ ከተንቀቀሳቃሽ ምስሉ ጋር እያሳየሁ ባጫውታት አሁን አሁን የሚነገራትን እየሰማች  ” ወደ ሃገር አትምጣ ፣ ጊዜው ለልጆችህ ስትል ኑርላቸው !” ! የምትለኝን አትደግምልኝም!  ሰብእናን እንዳስቀድም ኮትኩታ ያሳደገችኝ የእናት ስስት ምክሯን ትታ   ” ለዚህማ ነፍስህንስ ብትሰጥ ምን አለበት!  ” ብላ ተዘጋጅቶም ከሆነ ወደ ገሃነምም ቢሆን መርቃ እንደምትሸኘኝ ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ  …

አዎ  ! የወጣቱን ታሪክ በግርድፍ ከደረሰኝ የወዳጀ መረጃ ተንተርሸ በቀጣይ የማለዳ ወጌ የምናወራው ይሆናል …
Dry tears of Khalid Nebiyu Sirak: http://youtu.be/H5N4KyeWPNo
እስኪ በቃችሁ ይበለን  !

ነቢዩ ሲራክ
ህዳር 6 ቀን 2007 ዓም


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>