“ስልጣኔን የለቀኩት በአንዳንድ ብልጣብልጦች እና የሴራና አድማ አካሄድ በሚችሉ ሰዎች ፓርቲው ስለተጠለፈ ነው::’ – አቶ አበባው መሓሪ የመኢአድ ፕሬዚዳንት
“ፓርቲው ወደፊት ለመራመድ የማይችልበት ወደፊትም የማይሻሻልበት ደረጃ ላይ ደርሷል::”አቶ አበባው
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
የመኢአድ ፕረዚዳንት የነበሩት አቶ አበባው መሓሪ ስልጣናቸውን ሊለቁ የቻሉት በገጠማቸው አስገዳጅ የድርጅታዊ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል እንደ አቶ አበባው ደብዳቤ በአብዛኛው የመኢአድ አባላት ከፍተኛ የድምጽ ድጋፍ ከተመረጥኩበት የፕሬዚዳንትነት ቦታ ላይ ድርጅቱ ወደፊት እንዳይራመድ የሚያደርጉ እና ከዚህ በፊት ተሳስረውና ተቆላልፈው በመጡ የውስጥ ችግሮች ለሃገራቸው መስራት አለመቻላቸውን በመጥቀስ ፓርቲው ወደፊት የማይራመድበት አጣብቂኝ ውስጥ መሆኑን ለጠቅላላው ጉባዬ ገልጸዋል::የመኢአድ የውስጥ ችግር በመጪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ላይ ውሃ የቸለሰ ነው ያሉት አቶ አበባው ኢትዮጵያውያን አቤት የሚልላቸው አካል እየጎደለ መሄዱን ጠቁመው በመኢአድ ውስጥ ያለው ችግር ከአቅም በላይ የሆነ ስለሆነ ፍርዱን እና መዝገቡን ለታሪክ በመተው ስልጣናቸውን እንደለቀቁት ከአቅም በላይም እንደሆነ አስረድተዋል::

ከአቅም በላይ ያሉትን ጉዳይ ሲገልጹ … ለየኢትዮጵያውያን ምሁራን ከትግሉ መሸሽ ምክንያቱ የትግሉ መስመር በአንዳንድ ብልጣ ብልጦች እና የሴራ እና የአድማ አካሄድን በሚችሉ ግለሰቦች ስለሚተለፍ መሆኑን መኢአድ ውስጥ ከተከሰተው ችግር እንደተገነዘቡ በደብዳቤያቸው ገልጸዋል::
የአቶ አበባው መሃሪ ፊርማ የሰፈረበትን ሙሉ ደብዳቤውን ከታች ያንብቡት :
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
– See more at: http://satenaw.com/amharic/?p=2462#sthash.hzTc9P9Y.dpuf