በሰኔ1- 1997 በመንግስት በግፍ የተጨፈጨፉ የሰላማዊ ትግል ሰማዕታትን ለመዘከር በአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ጽ/ቤት መርሀግብር ተዘጋጅቷል፡፡ መርሀግብሩ የህዝብ ድምፅ እንዲከበር በመጠየቃቸው በግፈኛው የኢህአዴግ ገዢ ቡድን የተደበደቡ፣የታሰሩና በየአደባባዩ የተገደሉትን ሰማዕታት ከመዘከር ባለፈ ብዙሀን የወደቁለት የዴሞክራሲያዊ ስርአት ምስረታ በኢትዮጵያውያን ህዝባዊ ንቅናቄ እውን እንዲሆን ቃልኪዳናችንን ምናድስበት ይሆናል፡፡ በመሆኑም በሀገራችን ዴሞክራሲያዊ ለውጥ እንዲመጣ የምትሹ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ቅዳሜ ሰኔ1 ቀን 2005 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ በአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ጽ/ቤት በመርሀግብሩ ላይ እንድትገኙ ተጋብዛችኋል፡
አድራሻ፡- ቀበና መድኃኒአለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት
በአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን