(ዘ-ሐበሻ) የዋይሊ ቴክሳስ ፖሊስ ኢትዮጵያዊቷ አልማዝ ገብረመድህን ከአንድ ወር መጥፋት በኋላ አስከሬኗ መኪናዋ ውስጥ እንዳለች፣ ኩሬ ውስጥ ገብቶ መገኘቱን ተከትሎ የአደጋውን ምክንያት በጥቂቱ ይፋ ማድረጉን አድማስ ራድዮ ከአትላንታ ዘገበ::
አድማስ ራድዮ መርማሪዎቹን ጠቅሶ እንደዘገበው አደጋው የደረሰው በሌላ ጥፋት ወይም በሌላ ኃይል ሳይሆን በተፈጠረ ጥቂት የአነዳድ ስህተት ነው። ኩሬው አካባቢ አሳሳች ምልክት ነበር በዚያ ተሳስታ ወደ ኩሬው ሳትነዳ አልቀረችም ነው የሚለው።