ኀዳር ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ 11 በለሚ አካባቢ የምትገኘው ማሪያም ቤተከርስቲያን በህገወጥ መንገድ ተሰርታለች በሚል ፖሊሶች ለማፍረስ ሲሄዱ ህዝቡ ባሰማው ተቃውሞ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ታውቋል።
ድርጊቱን የተቃወሙ ምእመናን “ቤተክርስቲያኑዋን ማፍረስ አትችሉም” ማለት ሲጀምሩ ፖሊሶች መደብደብ የጀመሩ ሲሆን፣ ህዝቡም በአጸፋው በፖሊሶችና በወረዳው አስተዳዳሪ ላይ ድንጋይ በመወርወር የተወሰኑ ፖሊሶችን አቁስሏል። የወረዳው አስተዳዳሪም ጉዳት ደርሶባቸው አምልጠዋል።
ወደ አካበባው በፍጥነት የደረሰው የፌደራል ፖሊስ፣ በቀጥታ የሃይል እርምጃ በመውሰዱ በርካቶች አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በስፍራው የነበሩ የአይን እማኞች እንደሚሉት ፌደራል ፖሊሶች በተደጋጋሚ ጥይቶችን ተኩሰዋል። ይሁን እንጅ በብረት ዱላ የምእመኑን እግር በመምታት ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል
↧
የቤተክርስቲያንን መፍረስ የተቃወሙት ተደበደቡ
↧