ከሥርጉተ ሥላሴ 07.11.2014 (ሲዊዘርላንድ ዙሪክ)
ጨረሯ ብቻ ደረሰኝ። ምን ደረሰኝ ብቻ አዳረሰኝ። እሷ ግን አትታይም። ስብሰባ ትሆንን? ወይንስ ሰማያዊ አልጋዋ ላይ ተኝታ … ወይንስ ጫጉላ ጊዜ ላይ ትሆን ወይንስ ከባዘቶማዋ ፍራሽ ተኮፍሳ? ክብር ሲወድላት — ደግሞም ሲያምርባትም የለችም። ብቻ የለችም። ግን አለች ትንፋሿ ሀገር ያዳርሳል። መንፈሷ ይሆን የሌለው? ይሆናል። ምን ይሆናል ነው እንጂ። ግን ለምን? … እእ … ለምን …. እ … „ለምን …?“
ጠብቅኳት አልመጣችም። ለእኔ ለእራሱ የላከችው ለብ ያለ ጉድ ነው። ልም ነገር። ስትገርም። ለእናንተስ ይሄው የእኔ ዕጣ ፈንታ ደረሳችሁ ይሆን? … አላውቅም። ቀና ብዬ ፈራ ተባ እያልኩ ተመለከትኳት … „ነገ ሌላ ቀን ነው“ አሃ! ብላ ጽፋለች።
ቀና ብዬ ስመለከት ደግሞ „ይህም ያልፋል“ ብላ ጽፋላች? ጎሽ! አልኩና ተረጋጋሁ። ግን ለምን? አላውቅም። ለመሆኑ ያነብበኩትን እርግጠኛ ነውን? „ ነገ ሌላ ቀን ነው „ ብላ ስለመጻፏ እንደ ገና አዎን እንደ ገና አሻቅቤና ሻቅዬ* ሳዬው ተለውጦ …„የማይቻለውንም መከራ ቢሆን በትእግስት ቻይው“ ብላ ጽፋልኛለች። ወይ ጉዴ ግን … ለምን? አላውቅም። ዝቅ ብዬ እንደ ገና … አዎና እንደ ገና ተመለከትኩኝ።
„ከመከራው በስተጀርባ ክብር አለ“ በማለት ደግማ ጽፋለች። ምን ማለት ነው ይሄ ደግሞ? እሷን ብሎ ትንቢተኛ፤ እሷን ብሎ ስለነገ ራዕይ ተንታኝ – በታኝ … ከደንቀራው ጋር ስትደልቅ ከርማ ብዬ ላኮራፋት ዳዴ ስልላችሁ በአንድ አቅጣጫ የላከችው ጨረር ተባዛ …ሳቀይንስ ተደመረ … ተዳምሮ ተባዛና ተነሰራፋ … ሞቅ አንደ ማለት ዳዳኝ። በጨረሮቹ ልክ የተደረደሩ ትዕይንታዊ ስንኞች ኪነን አንግበው ይታዬኛል። ጠጋ ብዬ ልዳስሳቸው ስል በቅጽበት – ቅጽበት ሆነው እርፍ። … ግን እንደ ገና ተፃፈ። መነጠሬን ከኮሮጆዬ አወጣሁና በጥደፊያ ተያያዝኩት …
አንዱ ምን ይል መሰላችሁ … ወይ ጉድድድድድ …!„የጨለማ ፀሐይ“ ይላል። እ! አልኩኝ … ምን ማለት ይሆን ይሄ? —————ብዬ ሳመናታ እራሱን ቀዬር አድርጎ ፈታልኝ „ህልም“ ሲል … አህ! ብዬ ልቤን አዳመጥኩት። አሁን ወደ ቀጣዩ መልዕክት መሄድ እንደለብኝ ህሊናዬ ማስታወሻ ቢጤ ጫር ጫር አድርጎ ላከልኝ። ቀጣዩ … „የሰማይ ቤት ሸንጎ“ የሚል መጣልኝ። ሃሃ! አልኩኝ። ይህ ደግሞ ምን ይሆን? ብዬ ሳመናታ ሌላ አንድ በአንድ ዘርዘር እያለ ጠብታ ከች አለ ሳገጣጥመው
… „የሞት አደባባይ“ ብሎ ቁጭ። ውይ? ይሄም ደግሞ አለ? በጣም ፈራሁ። ጨነቀኝ። ተዘንፈዘፍኩ – ስላችሁ።አይጣል? መነጠሬን ለማውለቅ ስታገል … እሱ ደግሞ ለካስ ከዓይኔ ላይ ስበት ተፈጥሮለት አሻም እንዳለ ተሰክቶ ቅርት። ሲያናድድ። ተናዳደዱ እባካችሁ ከእኔው ጋር። ማስቲካ! ….ቀጥይ ማለቱ እንደሆነም ገባኝ። በምልክት ቋንቋ … በቃ አሸከረከረኝ እንደ – ዛቢያ። ገና እኮ ነኝ ወደ ሁለተኛው ጨረር አልሄድኩም። መዳህ ታውቃላችሁ ዝም ብሎ ታቱ …ዥግራ … ከወፌ ቆመች ያልተደረሰ … ብልጭ ድርግም በሐመራዊነት … አንተ ደግሞ ምን ልትል ይሆን ብዬ ዳጥም – ላጥም ይዞ ሊፈጠርቀኝ ግብግብ ስገጥምላችሁ …. አምካላችሁ አለ ሰውነቴ የማለውቀው ሆነብኝ። ዖዬ! እኔ ወይንስ ሌላ .. ህም „ተስፋ ይለመልማል“ አይልም መሰላችሁ። ወህ! ተመስገን አልኩኝ። ይሄስ ምን ትርጉም ያስፈልገዋል ብዬላችሁ ወደ ሶስተኛው ጨረር ላዘግም ስሰናዳ ውልብልቢቴን ጨምድዶ ያዝ አደረገና … „ተስፋ ይጎድላል“ አለኛ! እቴ የምን ጭንጫ ነገር ነው የኳረተ …መጀመር እንጂ ፍጻሜ የሌለው ሕይወት … የራስህ ጉዳይ ነው ፈንግጠው! ብዬ ቀጨር መጨሬን ሰባስቤ ስሰናዳ … ያለዬለት የነበረው ቀለም እዬነጠረ እዬነጠረ መውጣት ጀመረ
… አረንጓዴ ~ ቢጫ ~ ቀይ! ዋው፡~! እንኳንም ለሀገሬ አፈር አበቃህኝ ብዬ ጠላታችሁ ድፍት ይበልና ፍግም ብዬ መሬቱን ልስም ስል „ አትቸኩይ! የሀገርሽ ጉድ ገና ነው።“ የሚል መልእክት በስተጀርባዬ …. ደለቀ። ቁጣም ግልምጫም ድንፋታም ተዘልለው – ህም!… አንኳኳ …. እህ አልኩኝና ደግሞ ምን ቀረ ከማርያም መቀነት ወዲያ ስል አራተኛው ጨረር ፊት ለፊቴ በራልኝ … „ሰንደቁ በእግር ብረት ታስሯል“ የሚል መልዕክት ፃፈ … ደሜ ሲንተከተክ ተሰማኝና … እኮ እንዴት?! ስል በድፍረት ያነን የተላከልኝን አራተኛ ጨረር አፋጠጥኩት … አሻቅቤ እያዬሁ በድፈርትና – በወመኔ ቁጣ፤ ፈንግጪው እንዳይለኝ ግን ስሜቴ ተክ — ተክ —- ትር —– ትር —- ብን —- ብን ሲል ነጋሪት ይጎስማል … „እንቅልፋም“ ተብሎ ተጻፍልኝ።
ይህችን ትወዳላች ኧረ እኔ ነኝን እንጉልቻም? ብዬ ያነኑ አራተኛ ጨረር —– ላጣድፈው ፈራ ተባ ስል …. እኔ ትልቁ ችግሬ እንቅልፍ ማጣት ነው። መቼ ተኝቼ የማውቀውን ነው … ይህቺ ብዕር የሚሏት ቀለማም አድብታ ሳለች ነጋ ጠባ ከእርሷ ጋር ነኝ … እያልኩ ስብተከተክ አምሰተኛው ጨረር ከች አለ።„ከዚህስ ወዲያ! … እ¡¡¡“ የሚል በቃለ ስላቅ በትዝበት የቆዘመ ስንኝ ብቅ ጥልቅ እያለ አቅሌን መፈናፈኛ ነሳት። ወይ አይጸድቅ ወይ አይነቀል። ወቼ ጉድ አልኩኝ። ማለት ነበረብኝ። ኧረ ባበቃልኝና ግልግል በሆነ ስል ተተካ ተረኛው፤ „ትራስሽ ምን ግዴ ነው“ ተባለኩኝ። ህም! „እሺ ምን ልሁን? ምንስ ላድርግ? ይነገረኝ“ እያልኩ ወኔዬ ገፍትሮኝ እዬተለማማጥኩኝ ስንተባተብ ስድስተኛው ጨረር „አደብ – በሆደ ሰፊነት- ይመስጠር።“ ሲል ውሽክ ብሎ ፈታልኝ።
በተፈጥሮዬ ጮኽ ብሎ መነገር አይሆንልኝ። ግጥሜ አይደለም። ፊታውራሪ በር እንኳን ከልጅነት እስከ እውቀት አንድ ቀን ሰለቀችኝ – ቡጢዋን እልቻልኩትም ብሎ ችሎት ገትሮኝ አያውቅ፤ እንደተመሰጋገን ይሄው አለን። ግን ነገር ግን የአሁን አቤቱታ ቁሮ እንጂ የእኔ ማንነት አይደለም እያልኩ ብቻዬን እያወጋሁ እጄን ከግራ ወደ ቀኝ … ከቀኝ ወደ ግራ ሳወራጭ — ላችሁ … መንፈሴ መሳሪያውን ሲያቀባበል – ልተኩስ — ተሰማኝ … „ዛሬ! ዛሬ! ዛሬ! ቁረጭ – ምረጭ! ለህዝብ ጠቀም ተግባር ሰባራ ሰንጣራን ከባህር ከገደል ጠቅልለሽ ከነዲሪቶው ጣይ … በይ! በይ!“ በማለት ወጥሮ ሰንጎ ለምን አይዘኝም መሰላችሁ።
„እሺ ምን ልሁን ? ፈወስ … ምንድን ላድርግ?“ እያልኩ እጅግ በሚያባብል በቁልምጫ ህሊናን ዘና አድርጎ የጫጉላ ሽርሽር በሠረገላ ፈሰስ – ፈርሰስ በሚያደርግ ድምጽ ትህትናን አጋብቼ በክብር አሽሞንሙኜ ቀና አልኩ። አዎን በተጠንቀቅም ጸጥ ረጭ ብዬ ቆምኩኝ። እንደባንዴራው። ከዛ አዎን ከዛማ ሰባተኛውን ጨረር ተላከ። እንዲህም ይላል፤ በጉልህም ኮቢውም ብራናውም ፈቅደውለት ተጥፏል። ይበል … „የተግባር ስንቅና ትጥቅ ይኑርሽ“ በማለት የጉዳዩን አናት በዕለተ ሰንበት ጸበሉን ትእዛዝ አሳወቀችኝ። ይሁን! እሺ! ብዬ ልሰግድ ጎንበስ ስል እርገት ወረደ … ሰባቱም በአኃቲ ድምጽ … „ቁረጪ! ትውልዳዊ ድርሻሽን ለመወጣት“ ብለው ሲናገሩ … በእነሱ ቅኔዊ – ቃናዊ ድምጽ መጉላት ጉልበታምነት መሰለኝ … ከዙፋኗ ብቅ አለችና ብርኃኗን በመቁንን ሰደድ አደረገችልኝ። „እንዴት ነው ነገሩ ለብም አለደረገኝ። ከአንጀቴም አልደረሰም የብርኃን እናት ክብርት ልዕልተይ — ስላት …“—„በተስተካከለ ሙላት ለመኖር ሆኖ መገኘት“ በማለት ከልቧ አዎን ክልቧ …. አ – ሽ – ካ – ካ – ች
በመጨረሻ ትናንት 06.111.2014 ምን አስቦ ምን እንደከወነ በጸጋዬ ራዲዮ ፕሮግራም ማወቅን ትሻላችሁን? እንግዲያውስ www.lora.ch. Aktuelle Sendung Radio Tsegaye ያዳምጡ ዘንድ በአክብሮት አሳስባለሁ። ለውዶቼ – የእኔዎቹ መሸቢያ ሰንበት።
“አድርገህልኛልና ለዘላለም አመስግንሃለሁ።”
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።