Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Health: ሱስና መፍትሄዎቹ

$
0
0

አንድ ስኒ ቡና ለንቃት ሁለትና ሶስት ድብን ብሎ በመተኛት የካፌይን ተፅዕኖ ሲገለፅ

በተለያዩ አጋጣሚዎች ስራ፣ ጥናትንና በአጠቃላይ ለነቃ ውሎ ስንል ካፌይን ብለን የምንጠራውን ኬሚካል የያዙ መጠጦችንና ምግቦችን እንወስዳለን፡፡ በተለይም የዚህ ኬሚካል በብዛት መገኛ የሆኑትና በደከመንና በዛልን ወቅት ከድብርትና ከዱካክ ወጥተን ነቃ እንድንል የምንጠጣቸው ቡና፣ ሻይና የተለያዩ ለስላሳ መጠጦች ዋነኛ ተጠቃች ናቸው፡፡ ካፌይን አዕምሮን የሚያነቃቃ ሲሆን ከላይ ከጠቀስናቸው መጠጦች በተጨማሪ በሌሎች መግቦች ውስጥ ለምሳሌ በብስኩቶችና በቸኮሌቶች ውስጥ እንደዚሁም በአንዳንድ መድኃኒቶች (ለምሳሌ በራስ ምታት መድሃኒቶችና ማስታገሻዎች) ውስጥ በሰፊው የሚገኝ ነው፡፡ በአገራችንም በተለያየ መልኩ በሚሊዮን በሚቆጠሩ ሰዎች የሚወሰድ ነው፡፡ በብዙ ሰዎች በመወሰዱና በመለመዱም በተለያዩ ባለስልጣናትና የሃይማኖት መሪዎች ዘንድ ሳይቀር በ‹‹እፅ›› መልክ የሚወሰድም ነው፡፡ ነገር ግን ካፌይን መውሰድና ሱስ ውስጥ መግባት ከጤና ጋር ተያይዞ የሚመጡ ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል፡፡
ethiopian coffee
አንድ ስኒ ቡና ከ100 እስከ 150 ሚሊ ግራም ካፌይን በውስጡ ይይዛል፡፡ ሻይ የዚህን ሲሶ ያህል ካፌይን ሲኖው፣ በአንዳንድ መድሃኒቶች ይህንን ያህል ካፌይን የመገኘት አጋጣሚም ሊኖር ይችላል፡፡ በለስላሳ መጠጦች፣ በጣፋጭ ከረሜላዎችና ቸኮሌቶች ውስጥ እንደዚሁም በብስኩቶችና በሻይ ውስጥም በብዛት መኖሩ ህፃናት ልጆችም ሳይቀሩ በቀላሉ ሊወስዱት ይችላሉ፡፡
በዓለም ዙሪያ በአማካይ በቀን ውስጥ ከ80 ሚሊ ግራም በላይ ካፌይን በየቀኑ ይወሰዳል ተብሎ ይገመታል፡፡ ከካፌይን ጋር የተያያዙ አራት አይነት የጤና ችግሮች አሉ፡፡

1. የካፌይን ስካር (ኢንቶክሲኬሽን)
ይህ ስካር የሚጀምረው ከ250 ሚ.ግ በላይ ካፌይን ከተወሰደ በኋላ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዘው የሚታዩ ምልክቶች ጭንቀት፣ የህሊና መረበሽ፣ መቁነጥነጥ፣ መነጫነጭ፣ ማቅለሽለሽ፣ ማላብ፣ የሆድ መረበሽ፣ የሽንት መብዛት፣ እንቅልፍ ማጣትና በእግርና በእጅ ጣቶች ላይ የመወረር አይነት ስሜቶች መፈጠር ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ የተወሰደው ካፌይን ከ1000 ሚ.ግ በላይ ከሆነ የአፍ መኮላተፍ፣ የሃሳብ መደነጋገር፣ የልብ ትርታ መዛባት፣ ወፈፍ ማድረግ፣ የሌለና የማይታይ ብርሃን መታየት ሊከተሉ ይችላሉ፡፡ የካፌይን ብዛቱ ከ10,000 ሚሊ ግራም (10 ግራም) በላይ ካለፈ ግን ድንገተኛ ሞት ሁሉ ሊከተል ይችላል፡፡

2. ካፌይን ሳይወሰድ ሲቀር የሚከሰት ህመም
በዚህ ጊዜ የህመሙ አይነትና መጠን ከሰው ሰው እንደሚወሰደውና እንዳስለመዱት ብዛትና የልምድ ጊዜ እርዝመት ይለያያል፡፡ የተለመደው ካፌይን ሲቀር ከሚታዩ ምልክቶች መካከል ራስ ምታት፣ ጭንቀት ወይም መደበት፣ ድካም ወይም መፍዘዝ፣ ማቅለሽለሽ ወይም ማስታወክ ሊከተሉ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ካፌይኑ ከቀረ ከ12 እስከ 24 ሰዓታት ውጥ የሚጀምሩ ሲሆን በሁለተኛው ቀን የሚብሱ ነገር ግን በአንድ ሳምንት ውስጥ ተመልሰው የሚጠፉ ናቸው፡፡

3. የእንቅልፍ መቃወስና ጥልቅ የሆነ ጭንቀት
መረበሽ፣ መነጫነጭ፣ መቁነጥነጥ ወይም በአንድ ቦታ ረጋ ብሎ አለመቀመጥን ሊያመጣ ይችላል፡፡ በተለይም የመርበትበትና በሆነው ባልሆነው መደንገጥ ያለባቸው ሰዎች ካፌይን በብዛት ከወሰዱ በኋላ በሽታው ሊነሳባቸው ይችላል፡፡ ስለዚህም በተቻለ መጠን ህመማቸው እንዳያገረሽባቸው ብዙ ካፌዬን መውሰዳቸውን መቀነስ አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ ደግሞ ትልቅ ጭንቀት ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፡፡
በእንቅልፍ ላይ የሚያመጣውን ለውጥ ስናይ ደግሞ ቶሎ እንቅልፍ እንዳይመጣ ካደረገ በኋላ በቀጣይነት ለረዥም ጊዜ መተኛት አለመቻልና በማለዳ ከእንቅልፍ መንቃትን የሚያስከትላቸው ተፅዕኖዎች ናቸው፡፡

የመፍትሄ እርምጃዎች
የካፌይን አጠቃቀምን ለመቀነስ ወይም እስከ መጨረሻው ለማቆም የመጀመሪያ እርምጃው ምን ያህል ካፌይን በቀን እንደሚወሰድ እና በምን አይነት መንገድ እንደተወሰዱ (በመጠጥ፣ በምግብ፣ በመድሃኒት…ወዘተ) እንደሚወስዱ ለይቶ ማወቅ፡፡
ከዚህ በኋላ በአንድ ጊዜ ሳይሆን ቀስ በቀስ የካፌይን አወሳሰዱን በመቀነስ በሳምንታት ውስጥ የሚፈለገው የተሻለ የመፍትሄ ደረጃ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡ ከእነዚህ ጋር አብሮ ካፌይን የሌላቸውን መጠጦችንና ምግቦችን ለይቶ አውቆ እነዚህኑ በምትክ መውሰድን ልማድ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ካፌይን መውሰድ በድንገት በሚቆምበት ጊዜ የሚከተሉትን ህመሞችንና የድብርት ስሜቶች ሲከሰቱ ማስታገሻ መድሃኒቶችን መውሰድ የተሻለ አማራጭ ነው፡፡
ለዚህም ነው አንድ ስኒ ቡና ጥሩ ንቃትን ለመፍጠር ያስችላል፡፡ ነገር ግን ሁለት ሶስት እያልን ስንደጋግም የአንጎላችን የመላመድ ብቃት እየጨመረ ይመጣና በንቃት ከመቆየት ይልቅ ድብን ወዳለ የእንቅልፍ ዓለም ውስጥም ያስገባል፡፡ ይህም የካፌይን ተፅዕኖ ተቃራኒ በሆነ መልኩ የሚፈፅመው ድርጊትም ጭምር ነው፡፡ በአጠቃላይ የካፌይን አጠቃቀማችንን ከምንወዳቸው ምግቦችና መጠጦች አንፃር መጠኑን በመቆጣጠር መቀነስ ሲልም እስከመተው ደረጃ መድረስ እንችላለን፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>