(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ ኖቬምበር 4 ቀን 2014 ዓ.ም በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ በደረሰ ቃጠሎ አንድ ሰው ተቃጥሎ መሞቱን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ:: ዛሬ በዩኒቨርሲቲው የደረሰውን ቃጠሎ የሕወሓት አመራሮች የሚቆጣጠሩት ራድዮ ፋና “በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ አዲ-ሀቂ ካምፓስ የሚገኝ አንድ የወንድ ተማሪዎች መኖሪያ (ዶርም) ህንፃ ላይ ቀለል ያለ የእሳት ቃጠሎ ደረሰ” ሲል መዘገቡና ቃጠሎውን ማሳነሱ ብዙዎችን እንዳስቆጣም ታወቀ::
የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከመቀሌ በፎቶ ግራፍ አስደግፈው እንደዘገቡት ቃጠሎው በመንግስት ሚድያዎች እንደተዘገበው ቀለል ያለ ሳይሆን የሰው ሕይወት የጠፋበት በመሆኑ ሚዲያዎቹ በተለይ “ቀለል” ያለ ሲሉ ቃጠሎውን መግለጻቸው ከቃጠሎው በስተጀርባ የሆነ ነገር እንዳለ ያሳያል ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ::
የዘ-ሐበሻ የመቀሌ ተባባሪ ካነጋገራቸው ተማሪዎች መካከል እንደ ራድዮ ፋና ያሉ የሕወሓት ሚዲያዎች የ እሳት ቃጠሎ ትንሽ እንደሌለ ሁሉ ቃጠሎውን “ቀላል” ሲሉ መዘገባቸው አስገራሚ እንደሆነና ተቃጥሎ ከሞተው ተማሪ በስተጀርባ ምን እንዳለ ማጣራት እንደሚያስፈልግ ጠቁሟል::
የመቀሌ ከተማ የፖሊስ ፅህፈትቤት ተወካይ ኮማንደር ጌታቸው ገብረህይወት በቃጠሎው ምክንያት በሰው ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱን ነው ቢያስረዱም በቃጠሎው አንድ ተማሪ ሰውነቱ ተቃጥሎ መሞቱን የዓይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::
የቃጠሎውን ፎቶዎች ይመልከቱ:-