ሐራ ዘተዋሕዶ
- የመተዳደርያ ደንቡን ማሻሻያ ረቂቅ ለግንቦቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አዘጋጅቶ የሚያቀርብ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡
- ማኅበሩ በጊዜአዊነት በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር ለመምሪያው የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ተጠሪ ኾኖ አገልግሎቱን በመፈጸም ይቆያል፡፡
- ጠቅላይ ቤቴ ክህነቱ ዘመናዊውን የኹለትዮሽ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ ሥርዐት መከተሉ ማኅበሩ ከፋይናንስ ሥርዐቱ ጋራ የሚጣጣሙ የሒሳብ ሰነዶችን ለመጠቀም ያስችለዋል፡፡
- የኤጲስ ቆጶሳት ሢመት መመዘኛ ሕግ ጸደቀ፤ በመጪው ግንቦት የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እንደሚፈጸም ተጠቁሟል