Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ቅዱስ ሲኖዶስ ‹‹እነማን ናቸው ከጀርባዎ ያሉት?›› ሲል ፓትርያርኩን ጠየቃቸው

$
0
0

የሐራ ተዋሕዶ ዘገባ

አቡነ ማቲያስ

አቡነ ማቲያስ


አቡነ ማትያስ÷ የሊቃነ ጳጳሳትንና ኤጲስ ቆጶሳትን ተጠሪነት ለፓትርያርኩ በማድረግ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖት ሕገ ቤተ ክርስቲያን የመጨረሻው ከፍተኛ ሥልጣን ባለቤት የኾነውን የቅዱስ ሲኖዶሱን የበላይነት በፓትርያርኩ የበላይነት ለመተካት ከምልአተ ጉባኤው ጋራ መሟገታቸውን አጠናክረው ውለዋል፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ አመራር ያላትን ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በፓትርያርኩ ዐምባገነናዊ አመራር ሰጪነት በመርገጥ በስም እንጂ በግብር የሥልጣን ልዕልና የሌለው ሲኖዶስ ለመፍጠር እየተጣጣሩ ነው፡፡

ቤተ ክርስቲያን አንድነትን በሚጠይቅና ከፍተኛ የጥንቃቄ ርምጃዎችን በሚሻ የህልውና ጥያቄ ላይ እንዳለች ያጤኑ የምልአተ ጉባኤው አባላት፣ ፓትርያርኩ የልዩነት ነጥቦችን በማክረር ቤተ ክርስቲያኗን ለኹለት ለመክፈል ላደፈጡ ኃይሎች መሣርያ ሊኾኑ እንደሚችሉ ተገንዝቧል፡፡

ልዩነት በተያዘባቸው የመነጋገርያ ነጥቦች ላይ ከሌላ አካል የተነገራቸው የሚመስለውን ብቻ እየተናገሩ አቋማቸውን ከማክረር በቀር ማብራራትና መተንተን በእጅጉ እንደተሳናቸው የተነገረባቸው ርእሰ መንበሩ፣ ‹‹የነበረው ሕግ እንዳይሠራ የማሻሻያ ረቂቁም እንዳይጸድቅ›› የሚመስል ‹‹ሲኖዶሱን የመበተን›› አዝማሚያ እያሳዩ እንደመጡ ተስተውሏል፡፡

‹‹ቅዱስነትዎ በጣም ተቀይረዋል፤ እነማን ናቸው ከጀርባዎ ያሉት?›› ሲል አጠቃላይ ጉዳዩን በሚገባ በማየት በቤተ ክርስቲያኗ እና በቤተ ክርስቲያኗ ላይ ብቻ አጠንጥኖ መሥራት እንደሚገባ አጽንፆት ሰጥቶበታል፡፡
* * *

እነማን ናቸው ከጀርባዎ ያሉት?

የአማሳኞች ዋነኛ ቡድን መሪ የኾነው ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ ሐዲስ÷ ትላንት ተሲዓት ስብሰባው በድንገት ከተቋረጠ በኋላ ምሽት ላይ ፓትርያርኩን አግኝተዋቸው እንደነበር ተናገረ፡፡ እንደ ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ አነጋገር፣ ፓትርያርኩ ከስብሰባው የወጡት ተብረክርከው ነበር፡፡ ‹‹ለማይኾን ነገር አሠቃያችኁኝ›› ብለው እንዳማረሩም አልሸሸገም፡፡ ‹‹የወሰዱት አቋም ታሪካዊ ነው፤ በተለይ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ›› በማለት ‹‹ሲያክሟቸው እንዳመሹ›› የጠቀሰው ሊቀ ትጉሃን ዘካርያስ፣ መንግሥት የማኅበሩ ገንዘብ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ማእከላዊ ካዝና መግባቱን እንደሚፈልግና በዚኽ ጉዳይ የጀመሩትን ጠንክረው እንዲገፉበት አበረታተናቸው ደስ ተሰኝተዋል ብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት በማድረግም በቅስቀሳቸው ሆ ብለው አልነሣ ያሏቸውንና በሸዋ ጳጳሳት በተለይ በአቡነ ማቴዎስ የሚመኩትን የሸዋ የአድባራት አለቆች ከአዲስ አበባ ለማንኮታኮት ማቀዳቸውን ገልጧል፡፡ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን የሸዋ ስብስብ ነው፤ ነገ ጠዋት የሸዋ አለቃ ሲጠፋ የምትገቡበት እናንተ ናችኹ፡፡››


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>