አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ብሔራዊ ምክር ቤት ዛሬ ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ በመሰብሰብ የስራ አስፈጻሚውን የ10 ወር ዕቅድ መርምሮ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁንና በተጓደሉ የኤዲቶሪያል ቦርድ አባላት ምትክ ምርጫ ማካሄዱን የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ለፍኖተ ነፃነት ገለጹ፡፡
እንደ አፈ ጉባኤው ገለጻ የዲሲፕሊን ጥሰት የፈጸሙ የፓርቲው የብሔራዊ ምክር ቤት አባላት ጉዳይ ላይ ምክር ቤቱ ሰፊ ውይይት ካካሄደ በኋላ በሥራ አስፈጻሚ በኩል ወደ ዲሲፕሊን ኮሚቴ እንዲመራ በመወሰን ስብሰባው መጠናቀቁን አፈ ጉባኤው ለፍኖተ ነፃነት ዝግጅት ክፍል ገፀዋል፡፡