ከጳጉሜን 2006 ዓ.ም ጀምሮ ጋምቤላ ክልል፣ መዠንገር ዞን፤ ጎደሬ ወረዳ በተለይ ሜቲ ከተማ ውስጥ ግድያና በአካባቢውም ግጭቶች መካሄዳቸውን የተለያዩ ዌብ ሳይቶችና መገናኛ አውታሮች እየዘገቡ ናቸው።
እንደዘገባዎቹ ከሆነ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፣ ብዛታቸው በውል ያልታወቀ ደግሞ ለከባድ የመቁሰል አደጋ ተጋልጠዋል።
«ግጭቱ የሚካሄደው በአማሮች ላይ ነው» የሚለው መኢአድ ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ የመንግሥት ካድሬዎችና ፌዴራል ወታደሮች እጃቸው እንዳለበት አመልክቷል።
ለመሆኑ ግጭቱ እንዴትና ለምን ተቀሰቀሰ? መንግሥትም ሆነ የክልሉ አስተዳደር ምን እያደረጉ ናቸው?
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡