በተክሉ አባተ
ስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ከተሾሙ እነሆ ሁለት ዓመት ሊሞላቸው አራት ወራት ገደማ ይቀራቸዋል:: ቅድመና ድኅረ ሹመታቸውን ተከትሎ የውይይትና የክርክር መድረኮች በኢትዮጵያም በውጭውም ዓለም ተከፍተው ነበር:: የአምስተኛው ፓትርያርክ የብፁዕ አቡነ ጳውሎስ ድንገተኛ ሞት አንዳች ለውጥ ለቤተ ክርስቲያኗ ያመጣ ይሆናል ብለው የገመቱና የተመኙ ብዙዎች ነበሩ:: ሁለቱ ሲኖዶሶች እርቅ ሊያወርዱ እንደሚችሉ ተተነተነ:: ዳሩ ግን የእርቁ ሂደት ሳያልቅ ምርጫ ተደረገና ብፁዕ አቡነ ማትያስ በወሳኝ ድምጽ እንዳሸነፉ ተነገረ:: መንግስት ከነበሩበት አስመጥቶ እንዳሾማቸው:: እርሳቸውም ነጭ ልብስ እንደማይለብሱና የቅንጦት ኑሮ እንደሚጸየፉ: ቤተ ክርስቲያን ያጣችውን ክብርና ተሰሚነት እንደሚመልሱ ተናገሩ:: «ይህን ማን አየው» በሚል ተስፋ አዲሱ ፓትርያርክ የለውጥ ሐዋርያ ሊሆኑ እንደሚችሉ ቅር እያላቸውም ቢሆን የገመቱ ነበሩ: -- [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—