ከበሲሊዮስ ዘዓማኑኤል
“ሚሉሽን በሰማሽ ገበያ በሎጣሽ”….. ይላል ያሀገር ሰዉ ሲተርት! ህዝብ ምን እንደሚላችሁና እንዴትስ ምዕመኑ እንደታከታችሁ በወቃችሁና አፈችሁን ሞልታችሁ ማህበረ ቅዱሳንን ለመዝለፍ….. “አሸባሪ“ ምናምን እያላችሁ ስለማታዉቁትና በልግፅ ስላለገባችሁ ነገር ለመዘባረቅ ባልደፈራችሁ! “የራሷ እያረረ የሰዉ ታማስላለች“ እንዲል አሁንም የሃገር ሰዉ … ደብተሮቹ የሚያስተዳደሩትን ደበርና አጥቢያ በአግባቡ መምራት ተስኗቸዉ ከሙስና ማፅዳት አቅቷቸዉ ሳለ በሚሊዮኖች መንፈሳዊ የትግል ፅናት ለሃያ አራት ዓመታት ሲገነባ የነበረን ማህበር ለማፈረስ ሲዶሉቱና ሲፈርጁ መዋለቸዉ ሲታወቅ አንግት ያስደፋል!
ሲናገሩ ካየኋቸዉ አንዱ ማንነቱን በቅጡ ያለወቀ ደብተራ ቅዱሳን አባቶችን ለማስፈራራት ሲሞከር ማስተወሌ መድረኩ የቱን ያህል የማሰብ ስንኩላን የተሰባሰቡበት እና መነፍሰዊነት በቦታዉ ያልተጋበዘበት የጠምጣሚዎች ስብሰባ እንደነበር ለመረዳት አያደግትም! አንዱ ተናጋሪ ብቻ ትንሽ አመክኖዊነት ያለዉ ይመስላል ነበር … የማህበረ ቅዱሳንን መሪዎች ዘልፎ አብዛኛዉን አባል ለመካከል የሞከረዉ (ገሎ ማዳን ሆነበት እነጂ) … ከሌሎቹ ደናቁርት ደብተራዎች ይሻል ይሆናል! በርግጥ እሱም የተንሸዋረረ አመለካከት አለበት! ንግግሩን ሲያበቃ እንደብዞወቹ በፍርጃና በማስፈራራት ነዉ የዘጋዉ…. ብዙ የኢህዴግ አባልና ደጋፊ የሆኑ የማህበሩ አባላት እንዳሉ ሲታወቅ “በፌደራሊዝም የሚያምኑ” ምናምን እያለ የማያወቀወን በጥራዝ ነጠቅነት ሲቀባጥረና ወጥ ሰረግጥ ነበር! ጠርዝ የመያዝና ፍረጅነት በሽታ የሆነበት ሃገር!
ግን ማህበረ ቅዱሳን ምን አደረጋቸዉ? ምዕመኑን ስላስተማረ? መንፈሳዊ እዉቀት ስለዘራ? ወጣቱን ከዘመናዊ አሰተሳሰብና ከቤተ ክረሰቲያን ቀኖና ጋር አስማምቶ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እንዲያገለግል ስላስቻለ? ከርሳቸዉን ከመሙላት በቀር ለትዉልዱ ምንም አስበዉለትእና ምንም ሰርተዉለት የማያዉቁ፣ ጥምጣም ከማሳመርና በየመንደሩ እየዞሩ ህዝብን ከመበዝበዝ በቀር በመንፈሳዊነት ትዉልድን ማነፅ… ወንጌል በቅጡ መስበክ የማይችሉ… ዛሬ ተነስተዉ አፋቸዉን ሲያላቅቁ ከዉስጣወቹ የሚወጣዉ የክፋትና የአጥፊነት ክርፋት መሆኑ ታየ! ወየዉ….. እኔ ስለናተ አፍረኩ! አባቶቼ ብዬ መስቀል መሳለሜ … ጉልበት መሳሜ ፀፀተኝ! የተሰራን ማጥፋት… የተሰበሰበን መበተን ለነገሩ የአባይ ደብተራ ወጉ ነዉ!
ቅንጣት ታህል መንፈሳዊነት ያልጎበኛችሁ መሆናችሁን በአንደበታችሁ መሰከራችሁ! እናተ ስታነቀላፉ በተኩላ ልታስበሉት የነበረዉን ወጣት ሰብስቦ፣ አስተምሮ፣ ለሃገርና ለቤተክርስቲያን ልማት የቆመን አካል ቂጣ ባሰፋዉ አፋችሁ እየተነሳችዉ መዘንጠላችዉ…ምራቃችሁን ጢቅ ማለታችሁ ያሳፍራል! ከንቱ መሆናችሁንም በገዛ አንደበታችሁ መስመሰከራችሁ! ይልቅስ እዉቀቱና እዉነቱ ኖራቹሁ ቤተ ክርስትያንን የንግድ ቤት አድርገዉ ኪሳቸዉን ከሚሞሉ ሸቃጭ “አገልጋይ ነኝ” ባዮች ብትገላግሉን ምንኛ ቤተ ክርስትያንን በተጠቀመች እኛም ባከበርናችሁ! በዚያ መድረክ አላማችሁ ባንድም በሌላም ምንግድ ምን እንደሆነ ታይቷል…. ማህበሩን ከመንግስት ጋር በማጋጨት ለማፍረስ እንደሆነ ለሁሉም ምእመን ግልፅ ነበር…. እኛም ነቄ ብለናል! ከነቱ ልፋት! መእመኑ ማንን እንደሚመርጥ ያዉቃል … አክበሮቱንም ክብር ለሚገባዉ ይሰጣል!
የልም አትልፉ ማህበሩ ከመንግስት ጋር በፍጹም አይጋጭም! የሃገሪቱን ህግና ደንብን አክሮ ስራዉን ይሰራል…. ማህበሩና አባላቱም ከቅዱሳን አባቶቹን በቀንነት ያገለግላል! …. አባቶቹን አክበሮ …የቤተ ክርስትያንን ስርአትና ቃለ ዐዋዲ ጠብቆ ቅንጣት ታህል ስርአት ሳያዛንፍ ይሰራልና የሚፈራዉ ነገር የለም! ህግ አዋቂስ ከሆናችሁ የቤተ ክርስትያኗን ደንብ አዉቃችሁ እራሳችሁን ባረማችሁ … የምትዘርፉትን ህዝብንም እፎይታ በሰጣችሁት ነበር! ማወቅ ከለባችሁ ደግሞ ማህበሩንም…ቤተ ክርስትያንንም… ምንግሰትንም…ሃገርንም በቅንነትና በታማኝነት የሚያገለግሉ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ አባላትና … ሚሊዮን ደጋፊዎች አሉት! እረፉት እንጊደህ የተገባ ባይሆንም ሺዎች የማህበሩ አባላት ኢህዴግን ተቀላለቀለዉ አየሰሩ ነዉ! ሌላዉና በጣም ልታዉቁት የሚገባዉ ጉዳይ… እዉነቱን ለመናገር በርካታ የኢህዴግ አበላትና መሪዎች ከናተ ከሆዳም ደብተሮቹ ይልቅ ማህበሩን ቀርበዉ ያወቁታል… ያከብሩታል! በትምህርት ቤት ደጃፍ ያለፉ አባላት የሞሉት የሙህራን መድረክ የሆነ ማህበር ስለሆነ!
ከሁሉ የሚያሳፍረዉ “መናፍቅ” ለሚለዉ ትርጉም ማግኘት ተስኗቹህ የፖለቲካ ተንነታኔ ለመስጠት መመከራቸሁ ነዉ! እስኪ የፖለቲካዉን ትርከት ለፖለቲከኞቹና ለተማሩት ትታችሁ መናፍቅነታችህን ላስመሰከራችሁበት ምንፍቀናችሁ ትርጉም አብጁለት! ቤተ ክርስትንን እና ሃገርን በታማኝነት የሚያገለግልን ማህበርን እነደ ይሁዳ አሳለፎ ለመስጠጥ (ለማፍረስ) ከመዶለት…. አባላቱን እነደ አይሁድ “ይሰቀሉ… ይሰቀሉ!” ከማለት የተሻለ ምንፍቅና ከቶ ከየት ሊመጣ?
ማህበረ ቅዱሳን ህንፃ መስራቱ ይህን ያህል ያንገበገባቸዉ አረ ለምን ይሆን ግን!? ህንፃ ቢሰራ በአባላት መዋጮ ነዉ! ተማሪዉ ሆዱን አስርቦ የቁርሱን ዳቦ ሸጦ፣ ሰራተኛዉ የቤተሰቡን ጉሮሮ ዘግቶ አንጀቱን አስሮ በጠራቀማት ፍራንክ ህንፃዉ እንደተገነባ ለናተም ግልፅ ነዉ! እንደናተ የቤተ ክርስትያን ህንፃ አሰሪ ኮሜቴን አስቸግሮ አልያም ከኮሚቴ ጋር ተመሳጥሮ ከህዝበ ዘርፎ ኪሱን የሞላ አባል አለነበረም ወደፊትም አይኖርም! አንድ ደብተራ ዱንቡሎ ባለወጣበት ሁኔታ ለምን ማህበሩ ህንፃ ሰራ በሎ ይህን ያህል መጨነቁ የድንቁርናችሁንና የክፋታችሁን ልክ ያሳያል! ሌላዉ ህንፃዉ የተሰራዉ እናተ እንደ ምታድሩበት የመቃብር ቤት ከቤተ ክርስትያን መሬት ተቆርሶ ሳይሆን ሚሊዮን ብሮች ፈሶበት ከግለሰብ በተገዛ መሬት ላይ ነዉ! እና ምናችሁ ተነካና ነዉ ይን ያል ግብግብ ያላችሁት? መስራት ያልቻለችሁትን ስረቶ ስላሳያችሁ?
ለነገሩ “ደብተራ …የልማት ደንቃራ” እንደምተባሉ እናተም ታዉቀታለችሁ! ከእሁድ እከ እሁድ… ከወር እሰከ ወር በአል ነዉ፣ ግዝት ነዉ …. ዉግዝ ነዉ እያላችሁ ሀገሬዉን አሳንፋችሁ በድህነትና በረሃብ ስታሳክኩት የኖራችሁ መሆኑን ዛሬ እነዴት ተዘነጋችሁት?! “ሰማይ አይታረስ ንጉስ አይከሰስ” የሚል ቢሂል ፈጥራችሁ ህዝብን ስታስጨቁኑና አብራችሁ ስትበዘብዙ ኖራችሁ ዛሬ በየት በኩል ዞራችሁ ነዉ የዲሞክራሲና የፌደራሊዝም ሃዋርያ የሆናችሁት? መሰራት የሚችሉ ስታዩ አይናችሁ ደም ለበሰ! ህንፃ መስራት ጥምጣም እንደ ማሳመር ቀላል ይመስላችሁ ይሆናል… ተሳሳታችሁ! ፆም መዋልና ማደርን ይጠይቃል…. ከዛም አልፎ ለትዉልድ ሃሳቢ ሞሆንን … በለዕራይ መሆን ይጠይቃል! ዘኬ ቤት ተጎልቶ ከርስ ከመሙለት የተሻለ ሃሰብ ያስፈልጋል… አጉል ሚሲጢር ልታሶጡኝ ነዉ እንጂ በሚያሳፍር መልኩ ሆደሞች ለመሆናችሁ ምስክሩ በየሰንበቱ ደጀ ሰላም ዳቦ ስትቃሙ… ለፍርፋሪ ብላችሁ በመቛሚያ የምትዣለጡት ምን ያህል ወጣቱን ምእመን እደሚያሸማቅቀዉ ባወቃችሁት! አመታዊ ግብር አለተከፈለም ብላችሁ ስነቱን ደሃ ያለፈትሃት እንዲቀበር… ስንቱንስ ደሃ የመቃበር ስፍራ አሳጣችሁት?! በሚሊዮን የሚቆጠሩ የኦርቶዶክስ አማኞች ሃማኖቱን ትቶ ሌሎች የእምነት ተቛማትን እንደተቀላቀለ እስታቲክስኩን ማን ባስረዳችሁ?!…. ይህ ሁሉ ታዳያ በናት አሳፋሪ ስራ፣ዳተኝናትና ምዝበራ ነዉ! ለአሳፋሪ ስራችሁ መቼ ጆሮ አላችሁና ትሰሙታላችሁ?! ግመል እየዋጣችሁ ትንኝ ማጥራቱ የተለመደ ግበራቸሁ ሆኖ እነጂ የጭቃ ጅራፋችሁን ለማጮህ ባለደፈራችሁ ነበር! ሆዳችሁ አመላካችሁ እንደሆነ ክርስቲያኑ ብቻ ሳሆን ሌላዉም ወገን ያወቀዉ ጉዳይ ከሆኖ እንዴት እነዳቃችሁ ባወቃችዉ ምንኛ መታደል ነበር!
ለማኝኛቸዉም ህንፃዉ የተሰራዉ ለቤተ ክርስትያን አገልግሎት፣ ለመፍሰዊ ተልኮ እንጂ እናተ እንደምታስቡት ለከነቱ አላማ ወይም ደግሞ ለፖለቲካ ዱለታ አይደለም! ለፖለቲካ ጨዋታዉ መች ሌላዉ መድረክ ገና ተነካና? እናተ ቤተ ክርስትያንን ንቃችሁ እንዳስናቃችኋት … ደፍራችሁም አንደአስደፈራችሃት ማህበሩና አባላቱ ቀለዉ ቤተ ክርስትያንን አያቀሏትም! የቅዱሳን በዐት…. የፀሎት ዋሻ መሆኗን አብዝተዉ ይመሰክራሉ!
ሙሁራን አባላቱ ማታ ማታ መሰብሰባቸዉም ቀን ለስጋቸዉ ሲደክሙ ዉለዉ ለሊቱን ቤተ ክርስቲንን ለማገልጋል እንጂ እናተ በትንሿ መሰቢያችሁ እንደበሰለሰላችሁት ፖለቲካ ለመዶለት አይደልም! ለነገሩ ምን ታረጉ እናተ ካገልግሎት ሰዓታችሁ ሳይቀር እሰረቃችሁ ድራፍት ቤትና ገሮሰሪ ስትጋፉ አይደል ምታመሹት?! እንግዲዉም እወቁት አባለቱ ቀን በተለያዩ ስራዎች ሲደክሙ ይዉሉና በአዳር መርሃ-ግብር ደግሞ እንዲያ ያብከነከናችሁን የመሃብሩን ስራዎች ይሰራሉ! ለነገሩ መጎናጸፍያ አንዠርግጎ ሉካንዳ ቤት መሰለፍ፣ መስቀል ወድሮ ማኪያቶ ማንቃርር፣ ቀሚስ እየጎተቱ ቢራ መጋጨት ሞያዉ ላደረገ የደብር አሰተዳዳሪ፣ ክህነቱን ንቆ በዘማዊነት እራሱን ላዋረደ ካህን የክፋት ህሊናዉ ያቀበለዉን ከማዉራት፣ በየመደረኩ አደርባይነቱን ከማሳየት እና ከማሽቃበጥ በቀር የተለየ ነገር አይጠበቅም! ለሁለት ጌታ መገዛት ሆዳሞች ግበር ነዉና!
በጣም ያሰቀኝ…. ቆይቶ ደግሞ ያሰቀቀኝ ነገር ስለምርምርና ጥናት በምሬት ሲያነሱት የነበረዉ ነገር ነዉ…. ጉድ ነዉ መቼም እቺ ቤተ ክርስትያን ስነቱን ገለቱ ሰብስባ ይዛለች?! ኋላ ቀርንነታችሁ የቱን ያህል እንደሚያንገበግባችሁ በይፋ የተነገራችሁት! ጥናትና ምርምር የሚደረገዉ ቤተ ከርስትንን ለመጥቀም እንደሆነም አታዉቁም! በበጎ ፍቃደኝነት የሚጠናዉ ጥናት በአማካሪ ተቛማት ቢሰሩ ስነት ስነት ሚሊዮን በሮች ሊያሶጡ እንደሚችሉም አታዉቁም! ከዘመኑ ጋር ለማራመድ…. ሰራን በቅድ/በፕላን ለምመራት… በሚሰሩ ስራዎች ላይ ክትትል ለማድረግ… የልማት ስራዎችን ዉጤትና ስኬት ለመገመገም ጥናትና ምርምር ያስፈልጋል ጎበዝ! ይኼን የማታዉቁ ጉዶች ናችሁ ቤተ ክርስትንን እነመራልን ብላችሁ የተኮለኮላችሁት?! በእዉነት ስለናተ አፈረኩኝ!
እሰቲ አይናችሁን ከፍታችሁ ተመልከቱ … ዛሬ አለም ዘምኗል …. ቴክኖሎጂዉ ረቛል…. እንመራሀለን የምትሉት ምእመን በርቀት ጥሏቹሁ ኼዷል! እናተ ግን ዜሬም ቁራሽ በለመናችሁበት …. የቆሎ ተመሪነት ዘመናችሁ ላይ ቆማችሁ ባረጀና ባፈጀ አስተሰባቸሁ ህዝበን ለመምራት ትፈልጋለችሁ! ሌሎች የእመነት ተቋማትን እስኪ ተመለከቱ የቱን ያህል የዘመኑ መሆናቸዉን! በየ አድባራቱ ህንፃ ገንብቶ ሱቅ እያከራዩ ግበር የማከፈልበት የሃገር ሃበት መመዝበር…. አልያም በየ ንግሱ ጃንጥላ አዘቅዝቆ የምእመናን ኪስ ማራቆት ዘመናዊነት ከመሰላችሁ ተሳሰታችኋል! አለያም ከቤተ ክርስቲን በዘረፋችሁት እና የንስሃ ልጆቻችሁን ቁም ስቅል አሳይታችሁ ሰልቫጅ አዉቶ ሞበል ግዝቶ ልታይ ልታይ ማለቱ አይደልም የቤተ ክርስትያን እደገት! ይልቁንስ የቤተ ክርስትያንን ታሪክ በማጥናትና ለአዲሱ ትዉልድ በማሰተማር ለመጨዉ ዘመን ማሸጋገር፣ ቤተ ክርስትያን እንደ ተቛም ያለባትን ችግርና ፈተናዎወች መርመሮ የመፍትሄ አቅጣጫ በማዉጣት ስርአትና ተዉፊቷን አጽንቶ ለማኖር አሰተዳደራን ማዘመን፣ በዙሩያዋና ቡወስጧ የተሰባሰቡ ምእመናን ከመንፈሰዊዉ ስራ በተጨማሪ ያለቸዉን አቅም ጉለበትና ሃበት በማዋጣት ህዝብ የሚጠቀምበትን አገልገሎት ማስፋትና ማደረስ እንዲቻል ማሰተባበር በተገባ ነበር፡፡ ይሁናና ዶሮ ብታልም ጥሬዋን እነዲል የሃገር ሰዉ…. ጥሬ ነገር ከመቛጠርና እንቶ ፈንቶ ከማዉራት እለፋችሁ ሙሁራንን ተንጠራርታችሁ ለመዝለፍ መነሳታችሁ የጠፋታችሁ ሁሉ ጥፋት ነዉ!
ማህበረ ቅዱሳንና አባለቱን በፖለቲካ ለመክሰስ ከመነሳታችሁ በፊት እራሰችሁን መረምሩ! ወደ ማህበሩ የቀሰራችሁትን ጣት እራሳችሁን ተመልከቱበት! አፄ ቴድሮስ ለቀደሙት ደብተሮች በማያገባቸዉ እየገቢ ሲያስቸግሩ እንደተናገሩት እናተም በቅንነት ቤተ ከርስትያንን የሚያገለግል ማህበር ከመወነጀላችሁ በፊት በየጥመጣመቸሁ ስር ያለዉን ቆሮቆር የወረረዉን የረጀ አሰተሰበችሁን አፅዱ! ማፍረስ እንጂ መገንባት ዳገት ለሆነባችሁ ደበተሮች ከራሳችሁ ጥቀም አስበልጣችሁ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ፍላጎት ለማየት ሞክሩ! አላመችሁ ግልፅ ነዉ! ማህበሩን በማፍረስ ቤተ ክርስትያንን እና ምእመኑን ያለ ሃይ ባይና ለምን ብሎ የሚጠይቅ በለለበት ለመዝረፍ ነዉ! ይህ ደግሞ አይሳካም! የማህበሩ የበላይ ጠባቂ የማያንቀላፋዉ ትጉህ እረኛ ልዑል እጊዚያብሔር ነዉና!
ለሁሉም ማህበሩን ለቀቅ ….አርጋችሁ በትችሉ በትብር ለመስራትና ቤተ ክርስቲያንን ለማገለግል ሞክሩ ከልሆነ ግን እነተከበራችሁ ከነጠመጣማችሁ ሰንበቱ!
እስቲ ለሁሉም ልቦና ይስጣችሁ! አሜን!