ከዶ/ር ዓብይ ዓይናለም
እንስሳትን በተለይም ውሻና ድመትን ወይ ቤት ለማስጠበቅ አሊያም አይጦችን ለማባረር አለፍ ሲልም ደግሞ በሳሎናችን እንደ ጌጥ ማሳደግ የተለመደ ነው፡፡ በአብዛኛው የእንስሳት ባለቤቶች ዘንድ ግን እነዚህ እንስሶች ሊያስተላልፉብን ስለሚችሉት የበሽታዎች መጠንና ስፋት እንዲሁም ስለ ጉዳቶቹ ብዙም አይታወቅም፡፡ ለዛሬ የምናያቸው ከውሾቻችንና ከድመቶች ወደ ሰዎች የሚተላለፉ የጥገኛ ተህዋሳት በሽታዎችን ይሆናል፡፡
ከእንስሳት ወደ ሰው ከሚተላለፉት የጥገኛ በሽታዎች መካከል ዋነኞቹ የመንጠቅ ትል (Hook worm) እና የወስፋት (Ascarids) ናቸው፡፡ ውሾችን በአብዛኛው የሚያጠቋቸው የአስካሪስ ዝርያዎች (Toxocara canis) ሲባሉ ድመቶችን የሚያጠቋቸው ደግሞ Toxocara cati በመባል ይታወቃሉ፡፡ ሁለቱንም የቤት እንስሶች በማጥቃት የሚታወቀው የመንጠቆ ትል ደግሞ በሳይንሳዊ አጠራሩ አንኪሎስቶመም (Ancylostomum) በመባል ይታወቃል፡፡
እነዚህ የወስፋትና የመንጠቆ ጥገኞች በሰው ላይ የምግብና የደም ሽሚያ በማድረግ ተጠቂውን ለተለያዩ ቀውሶች የሚያጋልጡት ሲሆን የሆድ ህመም ከመፍጠራቸውም በተጨማሪ በተለይ በህፃናት ላይ ያላደጉትን እንጭጮቻቸው (Larva) በቆዳ ስርና ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች በመስደድ ተጨማሪ ጉዳት ያደርሳሉ፡፡
የወስፋት ትል (Ascaris)
በውሾ ላይ የአስካሪስ እንቁላሎች በእናትየዋ ማህፀን በኩል አድርገው ለቡችሎቹ ከመድረሳቸውም በላይ እናቲቱ ጡቷን በምታጠባበትም ወቅት ለቡችሎቹ ልታስተላልፍ ትችላለች፡፡ በተቃራኒው የድመት ግልገሎች በበሽታው ሊያዙ የሚችሉት ወይ ከእናትየው ጡት ሲጠቡ አሊያም አካባቢያቸው በጥገኞቹ እንቁላል ከተበከለ ብቻ ነው፡፡
ሰዎች በእነዚህ በሽታዎች ከተያዙም የእነዚህ ጥገኞች እንጭጭ (Larvae) በሰውነት ውስጥ በመዘዋወር የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን በመጉዳት ከጥቅም ውጪ ሊያደርጋቸው አሊያም ደግሞ በአንጀት ውስጥ በሚኖራቸው ቆይታ ከፍተኛ የሆነ የህመም ስሜት ሊያመጡበት ይችላል፡፡ አንዳንዴም አለፍ ሲልም ለህይወትም ሊያሰገኑ የሚችሉባቸው አጋጣሚዎች ይኖራሉ፡፡ በእነዚህ በሽታዎች ተይዞ ተገቢውን ህክምና ያላገኘ ሰው ደግሞ አካባቢውን በጥገኞቹ እንቁላል መልሶ በመበከል በተጨማሪ የበሽታዎቹ መፈጠር ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡
የመንጠቆ ትል (Hook Worm)
የውሻ ቡችሎችም ሆኑ የድመት ግልገሎች በዚህ ጥገኛ ተህዋስ የመጠቃት እድሉ አላቸው፡፡ ይህ ጥገኛ ተህዋስ ከምግብ ጋር አብረው ሲመገቡት አልያም ደግሞ ቆዳቸውን በመብሳት ወደ ሰውነታቸው አሊያም ደግሞ ቆዳቸውን በመብሳት ወደ ሰውነታቸው ሊገባ ይችላል፡፡ የመንጠቆ ትል አንዴ ከእንስሶቹ ሰውነት ከገባ በኋላ መጠኑ እጅግ የበዛ ደም በመምጠጥ ሰውነታቸውን ለደም ማነስ ይዳርገዋል፡፡ በተለይም በዚህ በሽታ የተያዙት ዕድሜያቸው ገና የሆኑ ቡችሎች ከሆኑ ከፍተኛ የሆነ ደም በመምጠጥ ለሞት ሊያበቃቸው ይችላል፡፡ የእነዚህ ሁለት ጥገኛ ተህዋስያን በእንስሶች ውስጥ እጅግ የተለመደ መሆኑና ብዙም ካልዳበረው እንስሳትን የማሳከም ባህል ጋር ተደማምሮ እነዚህን ተላላፊ በሽታዎች በአምክሮ እንድንመለከታቸው ያደርገናል፡፡ በሌሎች አገራት በዚሁ ዙሪያ የተደረጉ አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩትም ውሾችን በተለይም ቡችሎችን የሚያሳድጉ ግለሰቦች ላይ የእነዚህ በሽታዎች መከሰት እጅግ ከፍተኛ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ የህፃናት ከውሾች ጋር የሚኖራቸው የመጫወት ልማድና ቀረቤታ አንጻርም ከአዋቂዎቹ በበለጠ በእነዚህ በሽታዎች እንዲጠቁ ያደርጋቸዋል፡፡
ከእንስሶቹ ሰገራ ጋር ተቀላቅሎ የሚወጣውን እንቁላል በሆነ አጋጣሚ ወደ ሰዎች አፍ ከገባ በቀጥታ ወደ አንጀት በመውረድ ይፈለፈላል፡፡ በዚያም በዛ ያሉ እንጭጮች (Larvae) ይፈጠራል፡፡ እነዚህ ላርቫዎችም ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች በመጓዝ ‹‹ቪዘራል ላርቫ ማይግራንስ›› (visceral larva migrans) የሚባል በሽታ ያስከትላሉ፡፡ ይህ ሁኔታ በሰዎች ላይ ሲከሰትም የጉዳቱ መጠን የሚለካው በተጎዱት የሰውነት ክፍሎች መጠን ይሆናል፡፡ በአብዛኛው ይህ በሽታ ‹‹Soft organs›› የሚባሉትንና እንደ አይን፣ አዕምሮ፣ ጉበትና ሳንባን የሚያጠቃ ሲሆን በምላሹም ቋሚ የሆነና የማይድኑ የአይን፣ የነርቭ ወይም የሌላ ችግር ያስከትላል፡፡
የመንጠቆ ትልም በሰዎች ዘንድ ልክ እንደ ወስፋት በአፍ ውስጥ በመግባት በሽታን የሚያመጣ ሲሆን ከዛ በተጨማሪ ግን በቀጥታ ቆዳን በመብሳትም ጭምር በበሽታው ሊያሲዝ ይችላል፡፡ ይኼኛ 㜎ፅገኛ 㗹㜎ነጽ ቆዳን በሽጾ በሚገባበጽ ጊዜ በቆዳ ሽር ረጅም መንገድን 㜎ሚጓዝ በመሆኑ ‹‹ኩታኒየስ ላርቫ ማይግራንስ›› (Cutancous larva migrans) በመባል ይታወቃል፡፡ የዚህ አይነት የቆዳ ስር የላርቫ እንቅስቃሴ በተጠቂው ግለሰብ ላይ በተከታታይ የማሳከክ ፀባይ ያለው ሲሆን ቀጥ ያለ መስመር ያላቸውና ያመረቀዙ ቁስሎችንም የላርቫውን መንገድ ተከትለው እንዲወጡ ያደርጋል፡፡ አንዳንዴ ወደ ውስጠኞቹ የአካላችን ክፍሎች ድረስ በመዝለቅ በተለያዩ የአካል ክፍሎቻችን ላይ ተፅዕኖዎችን መፍጠር የሚችል ሲሆን አንጀት ድረስ በመዝለቅ አንጀታችን ላይ የመቆጣት ስሜት እንዲፈጠር ማድረግ ይችላል፡፡
መከላከያዎቹ
ከውሻና ከድመት ተነስተው ሰዎችን የሚያጠቁት አብዛኞቹ በሽታዎች በተለይም ከላይ የተጠቀሱት የጥገኛ ተህዋስያን በሽታዎች በቀላሉ የግል ንፅህናን በመጠበቅ፣ ውሻና ድምቶቻችንን ተገቢውን የሆነ ፀረ ተህዋስያን መድሃኒቶችን በፕሮግራም በተከታታይ እንዲያገኙ በማድረግና ለድመቶቻችን መፀዳጃ የምናስቀምጣቸውን አሸዋ የተሞሉ ካርቶኖች ሰዎች በተለይም ህፃናት የማይደርሱበት ቦታ በማስቀመጥ መከላከል ይቻላል፡፡ ሌላው ደግሞ ተገቢ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው የውሻና የድመትን ሰገራ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው የውሻና የድመትን ሰገራ በአግባቡ ማስወገድ ነው፡፡ ይህም ከጊዜ ብዛት በአካባቢ ላይ ተቀምጦ በዝናብና በንፋስ አካባቢውን የበለጠ እንዳይበክለው ይረዳል፡፡
አንዲት ሴት የአስካሪስ (ወስፋት) ጥገኛ ትል በቀን እስከ 100,000 እንቁላል የምትጥል ሲሆን በዚህ በሽታ የተጠቁ ውሾች ባሉበት አካባቢ ምን ያህል እንቁላል ሊኖር እንደሚችል ግምቱን ለአንባቢ ትቼዋለሁ፡፡ እነዚህ እንቁላሎች አንዴ አካባቢውን ከበከሉት ለዓመታት በዛው የሚቆዩ በመሆኑ በአካባቢው የሚገኙ ሰዎችን ለረጅም ጊዜ የጉዳቱ ሰለባ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡ ቡችሎች፣ የድመት ግልገሎች እርጉዝ እና የሚያጠቡ እንስሶች በእነዚህ ጥገኛ ተህዋስያን የመጠቃት ዕድላቸው ከፍተኛ በመሆኑና አካባቢንም በስፋት የሚበክሉት እነሱው በመሆናቸው የፀረ ጥገኛ ተህዋስያን ህክምናው በእነዚሁ እንስሳት ላይ ቢደረግ የተሻለ ውጤት ማግኘት ይቻላል፡፡ ለዚህ ደግሞ የእንስሳት ሐኪሞች አስተዋፅኦ እጅግ የጎላ በመሆኑ ለደንበኞቻቸው ተገቢውን የምክርና የማሳወቅ ስራ መስራት ይኖርባቸዋል፡፡